“አትገባም አሉኝ” ልጅ ሚካኤል በአዲስ አልበም መጣ

አርቲስት ሚካኤል ታዬ (ልጅ ማይክ) በሂፓፕ (hip hop) የሙዚቃ ስልት በሚጫወታቸው ጣፋጭ ሙዚቃዎች ይታወቃል። እነሆ የመጀመሪያ አልበሙን ካወጣ ከአምስት ዓመታት ቆይታ በኋላ አትገባም አሉኝ የሚል 15 ሙዚቃዎችን የያዘ አልበም ይዞ መምጣቱን በሼክ አላሙዲ ናኒ ህንፃ በአሚዩዚንግ ፕሮሞሽን አዘጋጅነት በተሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ለተጠሩት ሚዲያዎች እና ጋዜጠኞች ይፋ አድርጓል፡፡

የሂፓፕ ሙዚቃን በኢትዮጵያ ከሱ በፊት ሌሎች አርቲስቶች መጀመራቸውን ገልፆ እነሱን በመከተልም እሱ ሙዚቃውን መቀላቀሉን ልጅ ሚካኤል በዚሁ ጋዜጣዊ መግጫ ገልጧል፡፡

በ1995 በአዲስ አበባ የተለያዩ የትምህርት ቤት ፕሮግራሞች ለይ መድረክ በመምራትና የሂፓፕ ስልት ሙዚቃዎችን በመዝፈን የጀመረው አርቲስቱ በ2008 ዓ/ም የሰራው የሂፓፕ አልበም ከህጻን እስከ አዋቂ ተቀባይነትና ተወዳጅነት አትርፎለት ነበር።

አልበሙ ከወጣ በኋላ በተለያዩ የሀገራችን እና የአለማችን ከተሞች በመዘዋወር ስራዎችን በማቅረብ የሀገሩን የሂፓፕ ስልት ያስተዋወቀ ሲሆን ከተለያዩ የሀገር ውስጥ እና የውጭ ሀገር ታላላቅ አርቲስቶች ጋር የሰራቸው ነጠላ ዜማዎች ደግሞ የዝናውን ማማ እንዲቆናጠጥ ረድተውታል።

አርቲስቱ በተሰጠው ጋዜጣወዊ መግለጫ አዲሱ አልበም ለመስራት የሁለት አመታት ጊዜ እንደወሰደበት በመጠቆም በይዘቱም ካለፈው የተሻለ ነው ብሎ እንደሚያምን ለጋዜጠኞች ገልጧል።

ይሄ “አትገባም አሉኝ” የተሰኘው አልበም የፊታችን ማክሰኞ በገብያ ላይ የሚውል ሲሆን ግጥምና ዜማ ከአርቲስቱ በተጨማሪ እዩኤል ብርሀኑ ሲሳተፍ፤ ዮናስ ነጋሽ ደግሞ ሙዚቃውን አቀናብሯል። አቀናባሪው በቅርቡ የሰራው “ሸግዬ ሸጊቱ” የሚለው ሙዚቃው በህዝቡ ውስጥ ተወዳጅነትን ያስገኘለት ሲሆን ሙዚቃ የጀመረው በልጅነቱ እንደነበረ ተገልጧል።

Kumneger Media
Kumneger Media
Kumneger Media is a News and Entertainment Website & Channel. Kumneger Media in addition to News and Entertainment it is the hub of Politics, Movies, Drama, Music, Comedy, Documentary and More!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe