“ሮፍናን” በኮክ ስቱድዮ አፍሪካ

ኢትዮጵያዊዉ የኤሌክትሮኒክስ ሙዚቃ ኮከብ “ሮፍናን” በኮክ ስቱድዮ አፍሪካ ዉስጥ በድምፃዊነት አና በፕሮድዩሰርነት እንደሚሳተፍ ተገለጸ፡፡
በጉጉት የሚጠበቀዉ የኮክ ስቱድዮ አፍሪካ የሙዚቃ ዝግጅት አዲሱን ፕሮግራሙን ከጥር 2011 ዓ.ም. ጀምሮ በቴሌቪዥን በመላው አፍሪካ እና በኢትዮጵያ የሚተላለፍ መሆኑን አሳወቀ፡፡
ከበላዉ አፍሪካ ሀገራት በተለያዩ የሙዚቃ ዘርፎች ላይ የሚሰሩ አርትስቶችን አንድላይ በማምጣት የሚታወቀዉ አዲሱ ፕሮግራም፤ ከኢትዮጵያ አዳዲስ ድምፃዊያንን እንደሚያሳተፍ አስታዉቋል፡፡ ባልተለመደ መልኩ ኮክ  ስቱድዮ አፍሪካ ታዋቂዉን ኢትዮጵያዊ የኤሌክትሮኒክስ ሙዚቃ ኮከብ የሆነዉን ሮፍናን እንደ ድምፃዊም ፕሮድዩሰርም ሆኖ እንደሚሳተፍ ገለጸ፡፡ በፕሮግራሙ ልምድ አንድ አርቲስት ሁለቱንም ሚና ሲጫወት
ለመጀመሪያ ጊዜ ነዉ፡፡ ሮፍናን በፕሮግራሙ ላይ ከዛምቢያ ራፕ አርቲሰት ሼፍ 187 ጋር በመተባበር የሙዚቃ ቅንብራቸዉን በጋራ ያስተላልፋሉ፡፡ ድምጹን፣ ግጥሙን፤ ዜማዉን፤ እንዲሁም የኢትዮጵያ ባህላዊ ዜማ ቅንብር ከማበርከቱም ባሻገር ሮፍናን ሁሉንም የሙዚቃ ቅንብሮችን ፕሮድዪስ እንደሚያደርግ ተገልጽዋል፡፡
ፕሮግራሙ በሚቀዳበት ወቅት ሮፍናን ስለ አርቲስት ሼፍ 187 አድናቆቱን ሲገልጽ “እኔ የፈጠራ አርቲስት ነኝ ስለዚህ ከኢትዮጵያ የባህላዊ መሳሪያዎች አምጥቼ የሙዚቃ ቅንብሩ ዉስጥ አስገብቼዋለሁ፡፡ የዛምቢያን የሙዚቃ መሳሪያዎችም አካተናል፡፡ የሙዚቃ ቅንብራችን ሰፊ ነዉ፤
እንደምትወዱትም እርግጠኛ ነኝ፤ ከሼፍ 187 አብሬ መስራቴን በሙዚቃ ስራዬ እንደ ትልቅ ልምድ አድርጌ እቆጥረዋለሁ፡፡ በጣም የሚገርም አርቲስት ነዉ፤ ከአንድ ሁለት አመት በኋላ ትላልቅ መድረኮች ላይ እንደምናየዉ አምናለሁ” ሲል ተናግሯል፡፡
የኢትዮጵያን ባህላዊ ሙዚቃን የማቀነባበር ልዩ ችሎታዉ የሚታወቀዉ ሮፍናን በኢ.ዲ.ኤም (EDM) ሙዚቃ አይነት ለመስራት የመጀመሪያዉ ሲሆን ዘሬ ከአፍሪካ የወጡ የሙዚቃ ልዩ የፈጠራ ችሎታ ካላቸዉ አፍሪካዉያን እንዱ እንደሆነ ይታወቃል፡፡ “ነፀብራቅ” የሚባለዉ አልበሙ
ከተለቀቀ በኋላ በኢትዮጵያ የመጀመሪያ የኤሌክትሮኒክስ የሙዚቃ ስልት ዘፈኖች በማቀነባበር የሚታወቀዉ ዲጄ፤ ገጣሚ እና የሙዚቃ ፕሮድዩሰር በመሆን የሚታወቀዉ ሮፍናን በኢትዮጵያ በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ የኤሌክትሮኒክ ሙዚቃ አልበሙን በመልቀቅ ታዋቂ እንዲሆን አስችሎታል፡፡ ሮፍናን ስለ ኤሌክትሮኒክ ሙዚቃ ፍቅሩ ሲገልጽ “ቴክኖሎጂ የፈለግከዉን መሆን እንድትችል ያስችልሃል፡፡ የኤሌክትሮኒክ ሙዚቃ የእኔን ትዉልድ የሚወክል አድስ የሙዚቃ ስታይል ነዉ፡፡ እኛ አፍሪካዉያን ባህላችንን የሚያሳዩ የተለያዩ የሙዚቃ መሳሪያዎች እና ቋንቋዎች ስላሉን በኢ.ዲ.ኤም ድምጽ እንድንፈላሰፍ ያስችለናል፤ ይሄ ልክ እንደ አዲሱ የጃዝ ሙዚቃ ነዉ፤ ስለዚህ ለኔ በጣም ይመስጠኛል” ሲል ተናግሯል፡፡
በአዲሱ የኮክ ስቱድዮ አፍሪካ ምዕራፍ ከ25 በላይ የሚሆኑ ከሰሃራ በታች የወጡ ልዩ ተሰጥኦ ያላቸውን አርቲስቶችና ፕሮድዩሰሮች መካከል ሮፍናን አንዱ ሲሆን፤ ሌሎች አርቲስቶች ከኢትዮጵያ፤ ኬንያ፤ ዩጋንዳ፤ ታንዛንያ፤ ዛምቢያ፤ ዚምባቡዌ፤ ናሚቢያ፤ ሞዛምቢክ፤ ናይጄሪያና
ደቡብ አፍሪካንም እንደሚሳተፉ ተገልጽዋል፡፡ የፕሮግራሙ አላማ በኢንዱስትሪው ያሉ ልዩ አፍሪካዊ አርቲስቶችን፤ የሙዚቃ ቅንብራቸዉን
በአፍሪካ የሚገኙ የሙዚቃ አፍቃሪ ለሆኑ ተመልካቾች እና ለዓለም ለማድረስ ነዉ፡፡
ሮፍናን በኢትዮጵያ የዲጄነት ሞያ “ሮፍናን” በኮክ ስቱድዮ አፍሪካ እንዲያድግ ልዩ አስተዉጾ አድርጓል፡፡ በቅርቡ “Get To Work” ተብሎ የሚታወቀዉ የጉራጌኛ ስሌት ያለዉ ተወዳጅ ሙዚቃዉ በአለም አቀፍ መድረኮች እዉቅና እንዲያገኝ ከማድረጉም ባሻገር “Africa To The World” ተብሎ የተሰየመዉን የMajor Lazer’s የሙዚቃ ሲዲ ዉስጥ እንዲካተት ተደርጓል፡፡ የአልበሙም መለቀቅ ተከትሎ የኢትዮጵያ ሙዚቃ ላይ አድስ ጣእም በመምጣቱ በለዛ 2018 የሽልማት መድረክ ላይ የአመቱ አልበምን ጨምሮ ሶስት ሽልማቶችን ለማግኘት በቅቷል፡፡
ኮክ ስቱዲዮ የውድድር ይዘት የሌለው የትብብር ሙዚቃ ዝግጅት ሲሆን ከተለየዩ የአፍሪካ ሀገራት የሚወጡ የሙዚቃ ተሰጥኦዎችን በማገናኘት እና በማክበር ላይ ይሰራል፡፡ ለአዳዲስ አርቲስቶችም ከተለዩ አህጉር በቀል እና አለም አቀፍ የሙዚቃ ዝግጅት ባለሞያዎች ጋር የመስራት
እድልን ይሰጣል፡፡ አርቲስቶቹ ከተለያየ የሙዚቃ አይነት፣ ዘመን እና ክልል የተውጣጡ ሲሆኑ ጥንድ ጥንድ በመሆን ትክክለኛ አፍሪካዊነት
ያለው እና ዘመናዊ የሆነን ድምፅ፤ ሙዚቃዎችን በማጣመር እንዲሰሩ ይደረጋል፡፡ አርቲስቶቹ ፕሮዲውሰሮቹ የሚቀዱትን ሙዚቃ ለመስራት
በሚገናኙበት ጊዜ የሙዚቃ ዘይቤ እና ባህል ልውውጥ በማድረግ ይማማራሉ፡፡ ዝግጅቱም ተመልካቾችን ወደ ስቱድዮ በመውሰድ የተለያዩ
አርቲስቶች በስቱዲዮ ውስጥ ሲሰሩ ያለውን ሂደት ያሳያል፡፡ የኮክ ስቱድዮ አፍሪካ 2019 ዋና አጋሮች መካከል ሳንካራ ሆቴል፤ ፔስ አፍሪካ፤ ያሎ እና ሆም 254 ናቸዉ፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe