ባለቤትዎ ለአእምሮ ሕመም ሲዳረጉ . . . . . .

አይበለውና ባለቤትዎ ለአእምሮ ሕመም ቢዳረጉ ከመደበኛው የሕክምና ክትትል ባሻገር የእርስዎ አያያዝስ ምን ሊኾን የሚችል ይመስልዎታል? ካትሪን አፖንቴ የተባሉት የሥነ ልቦና ባለሙያ በርዕሰ ጉዳዩ ዙሪያ ለባለትዳሮች ባዘጋጁት ጽሑፍ ተከታዮቹን ምክሮች አጋርተዋል፡፡
– በንግግር ወቅት አያስጨንቋቸው፡- ከእርሳቸው ጋር የሚነጋገሩባቸውን ሁነኛ ጊዜያት ይምረጡ፡፡ አነጋገርዎ በጨዋነትና ክብራቸውን በጠበቀ መንገድ መኾን እንዳለበት አይዘንጉ፡፡ ከምንም በላይ ደግሞ በሕመማቸው ዙሪያ አሉታዊ አመለካከት ወይም ሐሳብ አይሰንዝሩ፡፡
– እንደሚያስፈሉግዎ ያስረዷቸው፡- በንግግርዎ ተገቢ ሰው መኾናቸውን አስገንዝቧቸው፡፡ እያንዳንዱን ስሜት አይደብቋቸው፡፡ ጉዳይዎ ጉዳያቸው መኾኑ እንዲሰማቸው ለማድረግ ይሞክሩ፡፡ በዚህም የ ‹አስፈልጋለሁ› በጎ ስሜት መፍጠር ይችላሉ፡፡
– ችግራቸውን ይረዱ፡- ስሜታቸውን በማይነካ ሁኔታ ስለራሳቸው ይጠይቋቸው፡፡ እያዳንዱ የስሜት መለዋወጥ በሚያሳድርባቸው ተጽዕኖ ዙሪያ ያውሯቸው፡፡ ችግራቸውን ፈቃደኛ ሆነው የሚነግሩዎ ከኾነ ደግሞ ለችግሮቹ መፍትሔ በሚኾኑ ጉዳዮች ላይ ይወያዩ፡፡ በተቃራኒው ችግራቸውን ለመንገር ፈቃደኛ ካኾኑ ደግሞ በፍፁም አያስጨንቋቸው፡፡ ከፍርድ ይልቅ በርሕራሔ ድምጸት በማናገር በራሳቸው ጊዜ ችግራቸውን እንዲያጋሩዎ ብቻ ያድርጉ፡፡
– የሕመሙን ባሕርይ ይገንዘቡ፡- ባለቤትዎ ሙሉ በሙሉ እስኪያገግሙ ድረስ ድጋፍዎን ይሻሉ፡፡ ይህን ማድረግ የሚችሉት ደግሞ የሕመማቸውን ባሕርይ ሲገነዘቡ ነው፡፡ ለዚህም ከንግግራቸው፣ ከሚያደርጓቸው ነገሮች እና ከሚያክሟቸው ሐኪሞች ዕውነታውን ለማወቅ ጥረት ያድርጉ፡፡

ምንጭ፡- psychologytoday.com

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe