ሴቶች ወሲብን ለስሜታዊ መቀራረብ የሚጠቀሙበት ሲሆን ወንዶች ደግሞ ፍቅራቸውን ማሳያ ያደርጉታል፡፡ ከሴቷ ጋር የጋራ እርካታ የሚገበዩበት መንገድ፣ የደስታ ማግኛ እና እንደ አፍቃሪ የተሻሉ መሆናቸውን ማስመስከሪያም ያደርጉታል ወሲብን፡፡ ስለዚህ ‹‹ወሲብ ለወንዶች ያለው ጥቅም ምን ያህል ነው?›› የሚለው ጥያቄ ሲነሳ ‹ወሲብ ወንዶች ወደ ፍቅር ግንኙነት የሚገቡበት ዋናውና መሠረታዊው ዓላማ ነው› የሚል መልስ ተከትሎ ይመጣል ማለት ነው፡፡ ወሲብ በትዳር ውስጥ ያለው ከፍተኛ ቦታ እንደተጠበቀ ሆኖ ከሴቶች ጋር ሲነፃፀር ደግሞ ለወንዶች የተለየ ትርጉም ያለው ሆኖ በትዳር አማካሪዎችና የሥነ ልቦና ባለሙያዎች ይነሳል፡፡ ለመሆኑ ወንዶች ለወሲብ ልዩ ትኩረት ያላቸው ለምን ይሆን?
- ጥንካሬያቸውን ማሳያ ነው
በፍቅርም ይሁን በትዳር ውስጥ ሴቶች መደነቅና በቃላት ብቻ እንደሚፈቀሩ መረዳት ይበቃቸዋል፡፡ በተቃራኒው ወንዶች የተግባር ሰዎች ናቸው፡፡ ፍላጎታቸውንም በቀጥታ የመናገር ችግር ስለሌለባቸው በፍቅር ወይም በትዳር ውስጥ ለወሲብ ያላቸውን ፍላጎት ከመግለጽ ወደኋላ አይሉም፡፡ ወንዶች ወሲብን የጥንካሬና የአንድነት መገለጫ አድርገውም ይመለከታሉ፡፡
- የግንኙነት መንገዳቸው ነው
ሴት ልጅ ለወሲብ ምቹ ስትሆንለት ወደ ሌላ ቦታ ከመመልከት የመቆጠብና በትዳር የመዝለቅ ቁርጠኝነቱን ጠብቆ የመቀጠል ዓላማ ይሰንቃል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ከባለቤቱ ወይም ከፍቅረኛው ጋር በጣም ጥብቅ ሆኖ እንዲዘልቅም ትልቅ ምክንያት ይሆነዋል፡፡ በጥንዶች መካከል የትኛውም ዓይነት ግጭት ቢኖር እንኳን ወሲብ አንዱ ማለዘቢያ መንገድ ነው፡፡ ስለዚህ ሴቶች በቤታችሁ የወሲብ ዕጥረት ሲኖር ወንዶች ጤነኝነት እንደማይሰማቸው ልብ ልትሉ ይገባል፡፡
- ከእኔነት ስሜታቸው ጋር ሊያያዝ ይችላል
የወንዶች የ‹እኔ›ነት ስሜት በቀላሉ የሚሠበር ነው፡፡ የመኝታ ቤቱንም ችግር ከግላዊ ማንነታቸው ጋር ሊያይዙት ይችላሉ፡፡ በዚህ ወቅት ተቀራርቦ መነጋገር ይጠቅማል፡፡ ወንዶች ወሲብን የደስታቸው መገኛ ስለሚያደርጉት የወሲብ እጦት ደስታቸውን ይነጥቃል፡፡ ስለዚህ ሌላው ቀርቶ ለወሲብ ሲሉ ብቻ ወሲብን ይሹታል፡፡ በትዳራችሁ ውስጥ ወሲብን ከቀዳሚዎቹ አጀንዳዎቻችሁ መካከል ማስቀመጥ በማንኛውም አጋጣሚ የሚፈጠሩ አለመጣጣሞችና አለመስማማቶችን የማስወገድ አቅሙ ከፍተኛ ነው፡፡
ምንጭ፡- https://www.marriage.com