ዓለምፀሐይ “አድርጉ” አላለችንም፤ ራሷ ያሰበችውን በተግባር ፈፅማ አሳይታናለች – አቶ ደመቀ መኮንን

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር “ዓለምፀሐይ “አድርጉ” አላለችንም፤ ራሷ ያሰበችውን በተግባር ፈፅማ አሳይታናለች” ብለዋል፡፡

አቶ ደመቀ ይህንን ያሉት ዛሬ የጣይቱ ባህልና ትምህርት ማዕከል የትውውቅና የገቢ ማሰባሰቢያ መርሃ ግብር በተካሄደበት ወቅት ነው፡፡

ማዕከሉ በአንጋፋዋ ከያኒ ዓለምጸሃይ ወዳጆ የተመሰረተ ሲሆን ላለፉት 20 ዓመታት በሰሜን አሜሪካ በኪነ-ጥበብና በትምህርት ላይ ሲሰራ እንደነበር ይታወቃል።

አቶ ደመቀ በንግግራቸው ማዕከሉ በዋናነት በድፍን ኢትዮጵያ የሚገኙ የባህል፣ የታሪክና የኪነጥበብ ፀጋዎችን ትውልዱ መንዝሮ እንዲጠቀምባቸው በእጅጉ ያግዛል ብለዋል።

በዚህ ዘመን እንደዓለምፀሃይ ታግለው የሚያሸንፉ፤ አሸንፈው ለውጥ የሚያመጡ ጀግኖች በብዛት እንደሚያስፈልጉን ታሪካዊ አጋጣሚው እንደሚያስገነዝብ ገልጸዋል።

ለማዕከሉ ቀጣይነት እና ትርጉም አዘል አገልግሎት ሁላችንም ልንደግፍ እንደሚገባም ተናግረዋል።

ዓለምፀሃይ የዕድሜ ዘመን ደማቅ ኪነጥበባዊ አበርክቶዎቿ ብቻ ሳይሆኑ፤  ለትውልዱ መልካም ሰብዕና ግንባታ በእሷ ስም ወደፊት ለሚጠብቁን ትሩፋቶች አስቀድሜ ያለኝን ታላቅ አድናቆት እና ተስፋ ለመግለፅ እወዳለሁ ሲሉ አቶ ደመቀ በፌስቡክ ገጻቸው ላይ አስፍረዋል፡፡

Kumneger Media
Kumneger Media
Kumneger Media is a News and Entertainment Website & Channel. Kumneger Media in addition to News and Entertainment it is the hub of Politics, Movies, Drama, Music, Comedy, Documentary and More!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe