የትኛው ቬሎ ይስማማሻል?

የሠርግ ሥነ-ሥርዓት የተቃናና የደመቀ እንዲሆን አስቀድሞ መዘጋጀት ወሳኝ ነው፡፡ አስቀድሞ የታሰበበት ሠርግ የተሳካና ያማረ ለመሆን አያጠራጥርም፡፡ የሠርግ ነገር ሲታሰብ ቅድሚያ ከሚሰጣቸው ነገሮች አንዱ የሙሽሪት ቬሎ ነው፡፡ ሙሽሪት ቬሎዋ ከሠርጓ ስድስት ወር አስቀድማ መምረጥ ይኖርባታል፡፡ ከሠርጓ ሁለት ሳምንት በፊትም በእጇ ልታስገባ ይገባታል፡፡
ሙሽሪት ቬሎዋን ከመግዛቷ ወይም ከመከራየቷ በፊት የትኛው እንደሚስማማት እንደሚማርካት መወሰን ይገባታል፡፡ በየቬሎ ቤቱ በመሄድ በርካታ ምርጫዎች ልትመለከት ትችላለች፡፡ ምርጫዋን ከያዘች በኋላ ምን ማድረግ ይገባታል?
በመጀመሪያ የሠርጓ ሥነ-ሥርዓት በምን መልኩ እንደሚከናወን ልታወቅ ይገባል፡፡ ምክንያቱም የቬሎ መግዢያ ወይም መከራያ ዋጋ ውድ በመሆኑ ለፕሮግራሙ የሚስማማውን የቬሎ አይነት ልትወስን ይገባታል፡፡ ለምሳሌ የሠርግ ሥ-ሥርዓቷ በቤተክርስቲያን የሚከናወን ከሆነ እጃቸው ጉርድና ግልጥ ቬሎዎች ተቀባይነት ላይኖራቸው ይችላል፡፡የሠርጓ ሥ-ሥርዓት ቀለል ያለ እንዲሆን ከፈለገች የምትመርጠው የቬሎ አይነት የተለየ ይሆናል፡፡
የሠርጓ ዕለት በየትኛው ወር እንደሚከናወን ማወቁ አስቀድሞ ከግምት ውስጥ ሊገባ ይገባዋል፡፡ በአገራችን የሚያዝያ ወር የሠርግ ወቅት ቢሆንም የበልግ ዝናብ የሚኖርበት በመሆኑ ሙሽሪት አጥያና ተጎታች የሌለው ወይም ተጎታቹ የሚነቀል ቬሎ ልታደርግ ይገባታል፡፡ ይህም ቬሎዋ በጭቃ እንዳይበላሽ ይረዳታል፡፡ እንዲሁም ከጀርባቸው በጣም ከፍት የሆኑ ቬሎዎች በዝናብ ወቅት ለብርድ ያጋልጣሉ፡፡
ቬሎን በመምረጥ ሂደት ሌላው ወሳኝ ነገር የሙሽሪት የአካል ሁኔታ ነው፡፡ ርዝመት፣ እጥረት፣ ውፍረትና ቅጥነት ቬሎን ለመምረጥ ወሳኝነት አላቸው፡፡ ከሰውነት ጋር የሚሄድ ቬሎ ለሙሽሪት ድምቀትን ይሰጣል፡፡ የቬሎ አይነቶች ቅርፅ፣ ቡፍያለና ክብ ባለተጎታች በመባል ይታወቃሉ፡፡ ኤ ቅርፅ ያለው ቬሎ ለማንኛዋም ሴት የሚሰማማ ነው፡፡ ቡፍና ክብ ያለው ሙሽሪት ጎላ ረዘም ብላ እንድትታ ያደርጋታል፡፡
ለአጭር ሴት
አጭር ሴት አንገቱ በጣም ክፍት ያልሆነ፣ ወገቡ ያወረደና አጭር እጅጌ ወይም ባካውት የሆኑ ቬሎዎች ይሰማሟታል፡፡ ተጎታች ያለው ቬሎ ለአጭር ሴት አይመከርም፡፡ እንዲሁም አጭር ሻሽ ልታደርግ ይገባታል፡፡ በጣም ቡፍ ያለ ቬሎዎች አጭር ሴትን ይበልጥ አጥራ አንድትታይ ሰስሚያደርጋት ምርጫዋ ባይሆኑ ይመረጣል፡፡ ረዘም ብለው ጠበብ ያሉ ቬሎዎች ለአጭር ሴት ተመራጭ ነው፡፡
ለረጅም ሴት
ረጅም ሴት አጠር ብላ አንድትታይ ወገቡ ወረድ ያሉና ቡፍ ያሉ ቬሎ ልትመርጥ ይገባታል፡፡ ሰፊ ቬሎ ሙሽሪት ወደጎን ሰፋ ብላ እንድትታይ ስለሚያደርጋት ቁመቷን ይከተዋል፡፡ አንገቱ ከፍያለና ፒትልስ ቬሎዎች ለረጅም ሴት አይመከርም፡፡ ባካውትና ማንገቻ የሌላቸው ቬሎዎች ለረጅም ሴት ተመራጭ ናቸው፡፡ እጀሙሉ ቬሎዎችም እንዲሁ ለረጀም ሴት ተስማሚ ናቸው፡፡ ረዘም ያሉ ሻሾችም ለረጅም ሴት ይስማማል፡፡
ለመካከለኛ ቁመትና ውፍረት
መካከለኛ ቁመትና ውፍረት ያላት ሙሽራ የትኛውም አይነት ቬሎ ይስማማታል፡፡ ፋሽን ሆኖ የመጣውን ቬሎ ብትለብስ ደምቃና አምራ ልትታይ ትችላለች፡፡ በቬሎ ምርጫዋ ላይ ምንም ተፅዕኖ አይኖርባትም፡፡
ለወፍራም ሴት
ወፍራም ሴቶች በተለይ ጡታቸው በጣም ትልቅና አንገታቸው አጭር ከሆነ ግልጥና ባካውት ቬሎዎችን ሊያደርጉ አይገባም፡፡ እንዲሁም ቡፍ ያሉ ቬሎዎች ወፍራም ሴት ይበልጥ ወፍራ እንድትታይ ያደርጋታል፡፡ ወፍራም ሴት በሳተን የተሰሩና ጠበቅ ያሉ ቬሎዎች ምርጫዋ ልታደርግ ይገባታል፡፡ የትከሻዋን ውፍረት ለመሸፈንም ትንሽ እጅጌ ያላቸው ቬሎዎች ብታደርግ ጥሩ ይሆናል፡፡ አንገቷ ወጣ ብሎ አንዲታይ አንገታቸው ገለጥ ያሉ ቬሎዎች ብትመርጥ መልካም ነው፡፡
ቀጭን ሴት
እንደ መካከለኛ ቁመት ውፍረት ያላት ሴት ሁሉ ቀጭን ሴትን በርካታ የቬሎ ምርጫ አላት፡፡ እንደፓሪ ያሉና ጥብቅ ያሉ ቬሎዎች ቀጨን ሴትን የበለጠ ስለሚያከሷት ብዙም አይመረጡም፡፡ በቲውል የሚሰሩና ቡፍ የሚሉ ቬሎዎች ቀጭን ሴትን ውበት ያላብሷታል፡፡
እንግዲህ ሙሽሪት እነዚህን ሁሉ ነገሮች ከግምት ካስገባች በኋላ መሆን አለበት የቬሎ ምርጫዋ ማከናወን ያለባት፡፡ ከዚህ በኋላ የሠርጓ ዕለት አምራና ደምቃ ትታያለች፡፡
ኤሮቢክስ
እድሜ እየገፉ ሲሄድ ጡንቻ የቀድሞ ጥንካሬንም ያጣል፡፡ ለዚህ ደግሞ መፍትሔው የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ነው፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ ባተስተካከለ የሰውነት አቋምም ዘወትር ምሬት ያሰሙ ይሆናል፡፡ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ በስብ ክምችት የተጨናነቀን ሠውነት አስወግዶ በምትኩ የጥሩ ቅርፅ ባለቤት ያደርገዎታልና ስጋት ሊያድርብዎ አይገባም፡፡ የሄርመን ጅምናዚየም የኤሮቢክስ ባለሙያ አቶ አለማየሁ ካብዬ ሠውነትን ለማጠንከር በሚሰሩ ስፖርታዊ አንቅስቃሴዎች ዙሪያ የሚነግረን አለ፡፡
አስፈላጊ የስብ ክምችትን ለማቃጠል፤ ጥሩ የአተነፋፈስ ስርአትና የተስተካከለ የደም ዝውውር እንዲኖረን አካላዊ እንቅስቃሴ አስፈላጊ ነው፡፡ ይህም እንቅስቃሴ ኤሮቢክስ በመባል ይታወቃል፡፡ ኤሮቢክስ ኦክስጅን በማስገባት እና ካርቦንዳኦክሳይድ በማስወጣት በሙዚቃ በመታገዝ የሚሰራ ሲሆን ገመድ ዝላይ፣ ሩጫ፣ ብስክሌት መንዳት እና የመሳሰሉት እንቅስቃሴዎችን ያጠቃልላል፡፡ ይህን እንቅስፈቃሴ ከ20 እስከ 40 ደቂቃ በመስራት አስፈላጊው የስብ ከምችት ማስወገድ ይቻላል፡፡ ከዚህ በተጓዳኝ ተጨማሪ የጥንካሬ ስፖርቶች መስራት ያስፈልጋል፡፡ ምክንያቱም የስብ ክምችቱ ከነበረበት ቦታ በሚቀንስበት ጊዜ ሠውነት በጣም ይላላል፡፡ በመሆኑም ስፖርታዊ አንቅስቃሴው ተገቢውን ውጤት እንዲያስገኝ ሠውነትን ሊያጠነክር የሚችል ስፖርት መስራቱ ይመከራል፡፡ በተለይም በጣም ከሚላላው የሰውነት ክፍል ውስጥ የእጅ ጡንቻ እና የሆድ ጡንቻ ይጠቀሳል፡፡
የእጅ ጡንቻ
ከእጅ ጡንቻ በራሱ የተለያዩ ከፍሎች አሉት፡፡
የውጭ የእጅ ክፍል (Triceps Muscle):- ይህንን የእጅ ክፍል ለማጠንከር ወንበር ላይ በመቀመጥ ሁለት እግርን በመዘርጋት ከመቀመጫ በእጅ ተደገፎ በመነሣት፤ እጅን በማጠፍ እና በመዘርጋት ከፍ ዝቅ ማለት፡፡ እንቅስቃሴው በአስር ድግግሞሽ ሶስት ዙር መስራት፡፡ በየዙሩ መካከል ለሰላሳ ሰከንድ እያረፉ መስራት፡፡
የውስጠኛው የእጅ ክፍል (Bicep muscle) ይህንን ክፍል ለማጠንከር መጠነኛ የሆነ ክብደት ያለው የክብደት የስፖርት መስሪ ብረት (Dumbel) በሁለት እጅ በመያዝ እጅን ተራ በተራ ወደ ውስጥ ውጭም ወይም ማጠፍ፡፡ ብረቱ ከሌለ የሚለጠጥ ፕላስቲክ ጎማ በቀለበት መልክ መስራት፡፡ ከዚያም ወንበር ላይ በመቀመጥና ላስቲኩን በእግር በመርገጥና በእጅ ወደላይ በማጠፍ እየደጋገሙ መስራት፡፡ አሠራሩ ከመጀመሪያው የድግግሞሽ ጊዜ ጋር ተመሳሳይ ይሆናል፡፡
የላይኛው የእጅ ክፍል ወይም ትከሻ (Deltod Muscle)
ይህን የእጅ ክፍል ለማጠንከር መጠነኛ ክብደት ያለው የስፖርት መስሪያ ብረት በሁለት እጅ በመያዝ ወደ ጎን በማንሣት በመመለስ ወይም ያለ ክብደት አንድ ዓይነት እንቅስቃሴ ማድረግ ነው፡፡ አሰራሩም እንደመጀመሪያዎቹ የድግግሞሽ መጠን ተመሳሳይ ነው፡፡ እነዚህ እንቅስቃሴዎችን ሴቶችና ወንዶች እንዲሁም በእድሜ የገፉ ሠዎችን ጨምሮ ሊሠሩት የሚችሉት ነው፡፡ ስፖርታዊ እንቅስቃሴው ብዙ ጉልበትና ትንፋሽ የማይጠይቅ በመሆኑ ጤንነት ላይ ተፅዕኖ አያስከትልም፤ነገር ግን የተለያየ ህመም ያለባቸው ማንኛውንም እንቅስቃሴ ከማድረጋቸው በፊት ለህክምና ባለሙያ ሊያማክሩ ይገባል፡፡
በማኝኛውም የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ወቅት ውሃ መጠጣት በላብ አማካኝነት የወጣን የሰውነት ፈሳሽ ይተካል፡፡ ስለዚህ ውሃ ያወፍራል የሚል የተሳሳተ ግንዛቤ አስወግደው በእንቅስቃሴ መሃል ውሃ ሊጠጡ ይገባል፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ በእስፖርታዊ እንቅስቃሴ ወቅት ሠውነት ካሎሪን ማቃጠል ይለምዳል፡፡ ስፖርት መስራት ሲያቆሙ የሰውነት መለጠጥ ያመጣል፡፡ ካሎሪን ማቃጠል ይለምዳል፡፡ ስፖርት መስራት ሲቆሙ የሰውነት መለጠጥ ይመጣል፡፡ ካሎሪ ከማቃጠል ልይቅ ለመከማቸት በመጀመር ወደፕሮቲን ይለወጣል፡፡ በዚህ ምክንያት ሠውነት መልሶ ክብደት ይጨምራል፡፡ ስለዚህ ከስፖርት በኋላ ሊከሰት የሚችል ውፍረት የአመጋገብ ስርአትን በማስተካከል ሊቆጣጠሩት ይገባል፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe