‹‹የዓመቱ ሰዎች››

ቴዲ አፍሮ
በ2011 ቴዲ አፍሮ ለመጀመሪያ ጊዜ በሚሊኒየም አዳራሽ የሙዚቃ ኮንሰርቱን በድምቀት ያካሄደበት ዓመት ነው፡፡ በአዲስ ዓመት ዋዜማና በሚሊኒም አዳራሽ ለማካሄድ ዕቅድ ተይዞለት የነበረው የቴዲ ኮንሰር በሀገሪቱ በተፈጠረው የፀጥታ ስጋት ጋር በተያያዘ ለወራት ሲንከባለል ቆይቶ በህዳር ወር አጋማሽ ተካሂዷል፡፡
የቴዲ አፍሮ ኮንሰርት ደረጃውን የጠበቀ የመዝናኛ ዝግጅት የነበረ ሲሆን ከ20 ሺ በላይ ታዳሚን ተገኝተው ተዝናንተውበታል፤ከ20 በላይ ዘፈኖችን የተጫወተው ቴዲ አፍሮ ደረጃውን በጠበቁ ካሜራዎች የተቀረፀው ኮንሰርቱ በያዝነው ዓመት አጋማሽ ላይ ለህዝብ እይታ ቀርቧል፡፡
ቴዲ አፍሮ ወደ አሜሪካ ባቀናበት ወቅትም ለአፍሪካውያን ወጣቶች ባሳየው አርአያነት ባለው ተግባሩ እውቅና ለመስጠት በዋሽንግተን ዲሲ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ፅ/ቤት ከኖቫ ኮኔክሽ ጋር በመተባባር ባዘጋጀው የታላቁ የአፍሪካ ሩጫ ውድድር ዋዜማ የእውቅና ሽልማት ሰጥቶታል፡፡ ቴዲ በዕለቱ ከአፍሪካ ህብረት ከሰጠው የእውቅና ሽልማት በተጨማሪ የዋሽንግተን ዲሲ ከተማ ከንቲባም የእውቅና ሰርተፍኬት ተቀብሏል፤የሜሪላንድ ከተማ ነዋሪ ኢትዮጵያውያንም ለቴዲ ልዩ ስጦታ አበርክተዋል፤ ቴዲ አፍሮ በወቅቱ ሽልማቱን ከተቀበለ በኋላ የሚከተለውን ንግግር አድርጓል፡፡
‹መቼም ስለ አፍሪካ ህብረት ሲነሳ ስለ አፄ ሀይለስላሴ እና ስለወቅቱ አጋሮቻቸው ስለእነ ንዋሚ ንኩሩማ አለማንሳት አይቻልም፤ በወቅቱ እነዚህ ሰዎች ያሰቡትን ሀሳብ አፍሪካውያንን አንድ የማድረግ ህልም እውን ለማድረግ ብዙ ደክመዋል፡፡ ጊዜው ወጣቶች እንደመሆኑ መጠን አሁን ተሰጠኝን ሽልማት ለኢትዮጵያውያንና ለአፍሪካውን ወጣቶች መታሰቢያ አድርጌ እወስዋለሁ፤ ይህንን ሽልማት ከደራርቱ ቱሉ ጋር አንድ ላይ መቀበል በመቻሌ ደስ ይለኛል፤ ደራርቱ የአፍሪካውያን ተምሳሌት የሆነች ጀግና በመሆኗ እንኳን ደስ ያለሽ ለማለት እወዳለሁ፡፡ እንግዲህ ታላቅነት የሚወለደው ከትጋት ውስጥ ነው ይባላል፡፡ አፍሪካ ከብዙ መከራና ችግሯ ወደ አዲስ ዓለምና የተስፋ አየር የምትወጣበት ጊዜ እየመጣ ነው ለማለት እችላለሁ፡፡ ስለሽልማቱ ሁሉንም ወገኖች አመሰግናለሁ፡፡›

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe