የፀጉርሽን እንክብካቤ ስትጠብቂ ልታደርጊ የሚገቡሽ ጥንቃቄዎች

  • ደረቅ ፀጉር ካለሽ በየጊዜው በሻምፖ አትታጠቢ፡፡ የፀጉር ቅባት ፀጉር ጎጂ በሆኑ ባክቴሪያዎች እንዳይጎዳ ስለሚረዳ እጅግ አዘውትረሽ በሻምፖ የምትታጠቢ ከሆነ ለቆዳ ድርቀት ልትዳረጊ ትችያለሽ፡፡
  • ፀጉርሽን በምታበጥሪበት ጊዜ ወደታች ከሚሆን ወደላይ አበጥሪ፡፡
  • ፀጉርሽን በእርጥቡ ለማበጠር አትታገይ፡፡ ምክንያቱም ፀጉር ሲርስ ከደረቁ ይልቅ በሶስት እጥፍ ስለሚሳሳ በቀላሉ ይበጣጠሳል፡፡ ፀጉርሽን መጀመሪያ በፎጣ ካደረቅሽ በኋላ በሰፊ ሚዶ አበጥሪው፡፡
  • ባረጀ የፀጉር ማስሪያ ወይም የእጅ ላስቲክ ፀጉርሽን አትሰሪ፡፡ በተለይ የእጅ ላስቲክ ፀጉርን በከፍተኛ ደረጃ ይበጣጥሳል፡፡

የፀጉርሽን ንፅህና መጠበቅ ለፀጉርሽ ውበትና ጤንነት ወደር የማይገኝለት ዘዴ ሲሆን ይበልጥ ውበቱን ለማጉላትና በፈለግሽው አይነት ቅርፅ ለማስያዝ ተጨማሪ ማስዋቢያዎች ያስፈልጉሻል፡፡ የከተማው ሴቶች ፀጉር ልስላሴ አስቀንቶሽ ‹‹ምነው የሴቱ ፀጉር እንዲህ አሳም?›› አሰኝቶሽ ይሆን? በሚገባ እንደሚያሰኝሽ ነው፡፡ ሁሉም ሴት ግን ለስላሳ ፀጉርን ተፈጥሮ ችራት እንዳይመስልሽ፡፡ ሪላክሰር ውሎ ይግባና የሉጫዋን ከቁርንድዷ፣የለስላሳዋን ከከርዳዳዋ አመሳስሎታል፡፡ ያ የጎመጀሽበት ፀጉር ባለቤት ለመሆን የሚያግድሽ አንድም ነገር አይኖርም፡፡ ሁሉ በእጅሽ ነውና፡፡ ልብ በይ ሪላክሰርን መጠቀምሽ ፀጉርሽ እንዲለሰልስ ያደርገዋል፡፡

ፀጉርን ሪላክሰር ወይም ቀለም መቀባት ጥንቃቄን የሚፈልግ ስራ በመሆኑ ራስሽን በራስሽ መቀባቱ ለአደጋ ሊያጋልጥሽ ይችላል፡፡ ሪላክሰር በተለምዶ ፐርም የምንለው ነው፡፡ ፐርምና ሪላክሰር እንደሚለያዩ ነው የፀጉር ባለሙያው የገለፀው፡፡ ‹‹ፐርም ፀጉርን ከርል የሚያደርግና በአገራችን ብዙም የማንጠቀምበት ነው›› ይላል ባለሙያው፡፡ ሪላክሰር ፀጉርን እንዲፍታታና እንዲዝናና የሚያደርግ ነው፡፡ ለፀጉርሽ ሪላክሰርን በምትጠቀሚ ጊዜ በባለሙያ ካልሆነ ፀጉርሽ ኬሚካሉን መሸከም ካልቻለ ሊጎመድ ይችላል፡፡ ጉዳቱ በዚህ አያበቃም፡፡ ጭንቅላትሽንም ያቆስላል፡፡ እንደ አቶ ጎልያድ ገለፃ ከሆነ ሪላክሰርን መጠቀም ‹‹ለፀጉር ኬሚካልን መስጠት፣የሚፈለገው ቅርፅን ከያዘ በኋላም ከሜካሉን ማውጣት›› ማለት ነው፡፡

ሪላክሰርን ለመጠቀም መጀመሪያ ፀጉርን ማቆሸሽ ያስፈልጋል፡፡ ይህም ቆዳሽ እንዳይጎዳ ይረዳል፡፡ ሪላክሰሩን ስትጠቀሚ የመጀመሪያሽ ከሆነ ከቆዳሽ ሦስት አራት ኢንች ከፍ አድርገሽ ጀምረሽ እስከ ጫፍ ቀቢው፡፡ ልብ አድርጊ! አንዴ ከተቀባሽ በኋላ ለመድገም ግን ሙሉ ፀጉርሽን መቀባት አይገባሽም፡፡ ምክንያቱም ኬሚካሉ ፀጉርሽን ይጎዳዋልና፡፡ ያደገውንና የሻከረውን ብቻ ቀቢው፡፡

ሪላክሰርን ለማድረግ የፀጉርሽ አይነት ለስላሳ ለሆነ ‹‹ሬጉላር›› የሚለው አይነት ተስማሚሽ ነው፡፡ ነገር ግን ፀጉርሽን አይበገሬ ከሆነ ‹‹ሱፐር›› የማያጠራጥር ምርጫሽ ነው፡፡ በሁለቱ ሪላክሰሮች መካከል ያለው ልዩነት ቢኖር የኬሚካል መጠኑ መለያየት ነው፡፡ አንዳንድ ባለሙያዎችም ሬጉላሩን ረዘም ላለ ስዓት በመጠቀም ከርዳዳ ፀጉርን ለማለስለስ ይጠቀሙበታል፡፡

ሪላክሰርን ስትጠቀሚ ልታደርጊያቸው የሚገቡ ጥንቃቄዎች

  • ባልቆሸሽ ፀጉር ላይ ሪላክሰርን አትጠቀሚ
  • በየጊዜው ሪላክሰርን አትጠቀሚ
  • ሪላክሰሩን ተቀብተሸ ከተገቢው ስዓት በላይ አታቆይ
  • እንደቀለም ያሉ ኬሚካልነት ያላቸውን ነገሮች ከተጠቀምሽ ከወር በፊት ሪላክሰር አትቀቢ
  • ሪላክሰሩ ፀጉርሽን ከጎዳው ለትንሽ ጊዜ ፀጉርሽን ከኬሚካል ነገሮች አሳርፊው
  • በየጊዜው በተለይ ባላበሽ ቁጥር ልትታጠቢ ትገደጃለሽ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe