ሶራ የተሰኘ ጽሁፍን ወደ ተንቀሳቃሽ ምስል የሚቀይር የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ መተግበሪያ ይፋ ሆነ

ቻት ጂ.ፒ.ቲን ጨምሮ በርካታ የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ቴክኖሎጂ ውጤቶችን በማበልጸግ የሚታወቀው ኦፕን ኤ.አይ የተባለው የቴክኖሎጂ ተቋም አዲስ የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ቴክኖሎጂ መተግበሪያ ለአገልግሎት አብቅቷል፡፡
ሶራ የሚል ስያሜ የተሰጠው መተግበሪያ ከተገልጋዮች በጽሁፍ የሚቀርብለት መጠይቅ ላይ በመመስረት ተንቀሳቃሽ ምስሎችን በላቀ ጥራትና ፍጥነት ለመስራት ያስችላል፡፡ መተግበሪያው በጽሁፍ ከሚቀርብለት መጠይቅ በተጨማሪ የትዕዛዙን ዐውድ በመረዳትና በመተርጎም ተንቀሳቃሽ ምስልን ይፈጥራል፡፡
ከማይንቀሳቀሱ ምስሎች ላይም ተንቀሳቃሽ ምስልን መፍጠር የሚችለው ይህ መተግበሪያ የነባር ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ርዝማኔ መጨመር ቢያስፈልግ አማራጮችን ይዞ ስለመምጣቱ የኦፕን ኤ.አይ ድረ-ገጽ ያመላክታል፡፡
ከፍተኛ ቋንቋን የመረዳት ክህሎት እንዲኖረው ተደርጎ የተሰራው መተግበሪያ የሚፈጥራቸው ተንቀሳቃሽ ምስሎች ከእውነተኛው ዓለም ጋር እጅግ ተቀራራቢ ስለመሆናቸው ተገልጿል፡፡
በሙከራ ደረጃ ላይ የሚገኘው ሶራ ሙሉ በሙሉ ወደ ስራ ሲገባ በተለይም በመዝናኛው ዘርፍ ትልቅ እመርታ ያመጣል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe