በቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ በአንዲት መንገደኛ ላይ ሙስና እና እንግልት የፈፀሙት የጉምሩክ ኮሚሽን ሰራተኞች ናቸው ተባለ

በቅርቡ በቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ በአንዲት መንገደኛ ላይ ተፈፅሟል የተባለውን ሙስና እና እንግልት የፈፀሙት የጉምሩክ ኮሚሽን ሰራተኞች መሆናቸውን የኢትዮጵያ አየር መንገድ ገለጸ፡፡
ድርጊቱን የፈፀሙት የኮሚሽኑ ሠራተኞችም በቁጥጥር ስር መዋላቸው ነው የተገለጸው፡፡
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ መስፍን ጣሰው በሰሞነኛና በአየር መንገዱ እንቅስቃሴ ላይ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል።
በመግለጫቸውም፥ በቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ ውስጥ ለሚፈፀሙ ወንጀሎች አየር መንገዱን ሙሉ በሙሉ ተጠያቂ ማድረግ ተቀባይነት የለውም ብለዋል።
በአውሮፕላን ማረፊያ ውስጥ ከአየር መንገዱ በተጨማሪ የኢሚግሬሽን፣ የጉምሩክ፣ የብሄራዊ መረጃና ደህንነት እንዲሁም የፌደራል ፖሊስ የራሳቸው ድርሻ እንዳላቸው አስረድተዋል።

አለሙ ስሜ
በቅርቡ በቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ በአንዲት መንገደኛ ላይ ተፈፅሟል የተባለውን ሙስና እና እንግልት የፈፀሙት የጉምሩክ ኮሚሽን ሰራተኞች እንጅ የአየር መንገዱ ሰራተኞች አይደሉም ነው ያሉት፡፡
በአውሮፕላን ማረፊያ ውስጥ መሰል ድርጊቶች እንዳይፈፀሙ ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅርበት እንደሚሰራም ተናግረዋል።
በቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ ውስጥ ከ3 ሺህ በላይ የደህንነት ካሜራዎች እንዳሉም ነው የገለፁት።
አሁን ላይ 145 አውሮፕላኖች አገልግሎት እየሰጡ መሆኑን አንስተው፥ በቅርቡ የአዳዲስ አውሮፕላኖች ግዥ ትዕዛዝ መሰጠቱንም ጠቁመዋል።
ኢትዮጵያ በአየር ትራንስፖርት ዘርፍ እያሳየች ያለው የላቀ ውጤትና እመርታ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ማረጋገጣቸውን ኤፍቢሲ ዘግቧል፡፡
በቅርቡ የትራንስፖርት ሚኒስትሩ አለሙ ስሜ(ዶ/ር) የቀረበውን አቤቱታ አሉባልታ ስለማለታቸው ፋና ዘግቦ ነበር፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe