በአትሌት ደራርቱ ቱሉ ምስል የታተመው ቴምብር ይፋ ሆነ

የኢትዮጵያ ፖስታ በረዳት ኮሚሽነር አትሌት ደራርቱ ቱሉ ምስል ያሳተመውን ቴምብር ይፋ አድርጓል።
አትሌቷ ለሀገር የዋለችውን ውለታ ታሪክ የማይረሳው መሆኑን ተከትሎ በስሟ ቴምብር መታተሙ ተገልጿል።
የኢትዮጵያ ፖስታ ሀገሪቱ ያላትን ተፈጥሮአዊና ሰው ሰራሽ ሀብቶች በቴምብር በማሳተም ሲያስተዋውቅ ቆይቷል።
ሴቶች ለሀገር ግንባታ ያላቸውን ጉልህ ተሳትፎ እውቅና መስጠት እንደሚያስፈልግም ያነሳው የኢትዮጵያ ፖስታ፤ የኢትዮጵያ ኩራት የሆነችውን አትሌቷንም በቴምብር ምልክቱ አኑሯታል።
የኢትዮጵያ ፖስታ፤ ረዳት ኮሚሽነር አትሌት ደራርቱ መጀመሪያ ካሸነፈችበት ኦሎምፒክ አሁን እስካለችበት ኃላፊነት ድረስ የሚገልፁ ምስሎች በቴምብር አሳትሟል።
የኢትዮጵያ ፖስታ ዓለም አቀፍ የሴቶችን ቀንን በድምቀት አክብሯል።
የሴቶች ቀንን ከማክበር ባለፈም፤ እኩልነት እና ሴቶች ያደረጉትን ተጋድሎ እና የሀገር ውለታ መዘከር ያስፈልጋልም ተብሏል።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe