ነፍሰጡርዋን ያዋለደው የአውሮፕላን አብራሪ

በቅርቡ አንድ የታይላንድ አውሮፕላን ድርጅት ተሳፋሪዎችን ይዞ ከታይዋን ወደ ባንኮክ መብረር ይጀምራል፡፡
ከተሳፋሪዎች መካከል አንዲት ነብሰጡር ሴት መውለጃ ጊዜዋ ደርሷልና በረራ ላይ እያለች ምጥ ይጀምራታል፡፡
በአውሮፕላኑ ውስጥ ምጥ የያዛትን ሴት ለመርዳት አንድም የጤና ባለሙያ አልነበረም። አብራሪው እና የበረራ አስተናጋጆቹ ተጨነቁ፡፡ አውሮፕላኑም በመዳረሻው ለማረፍ ሰዓታት ይቀሩት ነበር፡፡ ምጥ በያዛት ሴት ጩሀት ተሳፋሪዎች ጭንቀት ውስጥ ገብተዋል፡፡
የአውሮፕላኑ አብራሪ የነበረው ጃካሪን ሳራርንራ ካስኩል ላለፉት 18 ዓመታት በአውሮፕላን አብራሪነት ልምድ ያለው ቢሆንም ከመሰረታዊ የቀይ መስቀል የህክምና ዕውቀት በስተቀር ስለማዋለድ የሚያውቀው ነገር አልነበረም፡፡
ይሁን እንጂ ምጥ ውስጥ ያለችውን ሴት በሚችለው አቅም በድፍረት ለመርዳት ወሰነ፡፡
የዋና አብራሪነት ኃላፊነቱን ለረዳት አብራሪው አስረከበ፡፡ ከዛም ምጥ ላይ ያለችውን ነብሰጡር ተሳፋሪን ከመሬት በላይ በሺዎች ማይል ርቀት ላይ ወንድ ልጅ በሰላም አንድትገላገል ማድረግ ችሏል፡፡
የአውሮፕላኑ የበረራ ሰራተኞች አዲስ የተወለደውን ወንድ ልጅ ህፃን “ስካይ” ወይም ሰማዩ የሚል ስም አውጥተውለታል፡፡
አውሮፕላኑ እንዳረፈ ፈጣን ድጋፍ እንድታገኝም ደውሎ የጤና ባለሙያዎች እንዲዘጋጁ በማድረግ የሠራው ስራ በበርካቶች አየተሞካሸ ይገኛል ሲል የዘገበው ኒውስ ናሽናል ነው፡፡
Source(EBC)

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe