የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር ባልደረባ አድዋ ላይ ተገደለ!

ታጣቂ ሃይሎች ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ ይማፀናል!
………………….
አርብ ጥቅምት 18 ቀን 2015 ዓ.ም፣ የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር የሰሜን ጎንደር ቅርንጫፍ የአምቡላስ ሾፌር በነበሩት በአቶ መንግስት ምንይል ላይ ታጣቂ ሃይሎች ያደረሱባቸውን ግድያ በአፅንዖት ያወግዛል፡፡ ለመላው ቤተሰቦቹ፣ ወዳጅ ዘመዶቹና የስራ ባልደረቦቹ መጽናናትን ይመኛል፡፡
አቶ መንግስት ምኒል በምዕራብ ደንቢያ ሰብዓዊ አገልግሎት በመስጠት ላይ የነበረና በሰብዓዊ ህይወት የማዳን ስራ ወልቃይት አዲ ረመፅ ሆስፒታል ተመድቦ አገልግሎት በመስጠት ላይ ነበር፡፡ አቶ መንግስት አድዋ፣ትግራይ ተሰማርተው በግጭት የተጎዱ ወገኖችን በማገዝ ላይ ከነበሩ ሁለት አምቡላንሶች አንዱን በማሽከርከር ከአድዋ ወደ ወልቃይት አዲ ረመፅ ሆስፒታል ቁስለኞችን ለማድረስ በተንቀሳቀሰበት ወቅት ቁስለኞቹን ጨምሮ በታጣቂ ሃይሎች በተደረገባቸው ጥቃት ተገድለዋል፡፡
የአቶ መንግስት ምኒልን አስከሬን በዛሬው እለት አርብ ጥቅምት 18 ቀን 2015 ዓ.ም. በትውልድ ቀዬአቸው ምዕራብ በለሳ ጎንድ ተክለሃይማኖት ስርአተ ቀብሩ ከዕለቱ ስድስት ሰዓት ላይ ይፈፀማል፡፡
የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር የመጀመሪያ ህክምና እርዳታ አምቡላንስ በማሽከርከር ሰብኣዊ አገልግሎት በመስጠት ላይ በነበረው የ40 ዓመት ጎልማሳ ባደረባውና የሁለት ሴት ልጆች አባት በነበረው አቶ መንግስት ምንይል ህልፈተ ሕይወት የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን ይገልጻል፡፡ ግድያውንም ያወግዛል፡፡
እንደ አቶ መንግስት ምኒል ሁሉ በሰሜኑ የአገራችን አካባቢዎች ከጥቅምት 24/ 2013 ጀምሮ ላለፉት ሁለት አመታት በሰብዓዊነት መንፈስ በጽናት በመቆም መስዋዕትነት እስከ መክፈል ሊደርሱ እና ለህይወታቸው ሳይሳሱ በሰብዓዊነት መርህ ብቻ በመመራት በዱር በገደሉ ለተጎዱ ወገኖቻችን ቤዛ በመሆን አገልግሎት በመስጠት ላይ ለምትገኙ የሥራ ባልደረቦችና በጎፈቃደኞች የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል የአመራር ቦርድና ማኔጅንመንት አባላት፣ መላው ሠራተኞች እና አጋሮቻችን ከልብ የመነጨ አድናቆታቸውን ይገልጻሉ፡፡ የምታከናውኗቸው የላቀ ሰብዓዊ ድርጊት ምንጊዜም በማህበሩ ሰብኣዊነት ማሕደር ከሰብኣዊያን ሰማዕት ጎን ለዘላለም እያንጸባረቀ ይኖራል፡፡
አሁንም በድጋሚ በመላው አገራችን በሰብዓዊ አገልግሎት የተሰማሩ የቀይ መስቀል ማኅበር ሠራተኞችና በጎፈቃደኞችን ሰብዓዊ ተግባራቸውን በገለልተኝነት እና በአለማዳላት መንፈስ በነፃነት ተንቀሳቅሰው መስራት እንዲችሉ፣ እንዲሁም ደህንነታቸው እንዲጠበቅ፣ ታጣቂ ሃይሎች ከእንደዚህ አይነት ጥቃት እንዲቆጠቡ ደግመን ደጋግመን እንማፀናለን፡፡
ለሰብዓዊነት እንኖራለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe