በአሜሪካ ብቸኛዉና ግዙፉ የኤሮስፔስ አምራች ኩባንያ በሆነዉ በቦይንግ ላይ በተደጋጋሚ እያጋጠሙ ይገኛሉ የተባሉት የጥራት ችግሮች ያልተለመዱ መሆናቸውን የገለፀው አየር መንገዱ ነገር ግን በዚህ ተደናግጦ ከኩባንያው ጋር አብሮ መስራቱን እንደሚያቆም አስታውቋል ።
የኢትዮጵያ የአየር መንገድ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ መስፍን ጣሰዉ እንደተናገሩት ” የቦይንግ አዉሮፕላኖችን ስንጠቀም ከ 64 ዓመታት በላይ ሆኖናል” ነገር ግን በእነዚህ ዓመታት ዉስጥ በኩባንያው ላይ የጥራት ችግር አጋጥሞት አያዉቅም ሲሉ አስታዉሰዋል።
“ይህን ተከትሎ አሁን ላይ አጋጠሙ በሚባሉ ችግሮች ተደናግጠን ወደ ሌላ የምንሄድበት አይደለም” ብለዋል ዋና ስራ አስፈፃሚዉ ።
አየር መንገዱ አሁን ላይ ካለዉ 110 የአዉሮፕላን ጀቶች ዉስጥ 90 የሚሆኑት የቦይንግ ስሪቶች ሲሆኑ ቀሪዉ 20 ደግሞ የኤርባስ ናቸዉ።
ቦይንግ አዳዲስ አዉሮፕላኖች በሚሰራበት ጊዜ የነበራቸው የዲዛይን እና የምርት ሂደቱ ላይ የሚፈጠርባቸው ችግሮች ለመፍታት አቅም እንዳለዉ የመሰከሩት አቶ መስፍን ጣሰዉ ይህን ለመፍታት ያላቸዉ የገንዘብ ፣ የቴክኖሎጂ እና የሰዉ አቅሙ ለዚህ ማሳያ ነዉ ብለዋል።
የደህንነት እና የጥራት ቁጥጥር ጉዳዮችን ተከትሎ በቦይንግ 737 ማክስ አዉሮፕላኖች ላይ ስጋቶች እየጨመሩ መጥተዋል። ከ737 ማክስ ዲዛይነር ጋር በጥቅምት በ 2018 በኢንዶኔዥያ እና በመጋቢት በ 2019 በኢትዮጵያ ለሞት በሚዳርጉ አደጋዎች ተጠያቂ ነው መሆኑ ይታወቃል ።

