ወልድያ ከተማ አስተዳደር የ”መቀመጭት ተራራን” በአቡነ ኤርሚያስ ስም መሰየሙን አስታወቀ፤

ወልድያ ከተማ አስተዳደር የ”መቀመጭት ተራራን” “አቡነ ኤርሚያስ ተራራ” ብሎ የሰየመው አቡነ ኤርሚያስ ያደረጉትን ውለታ በማሰብ እና ለአቡኑ ተያያዥ የልማት የቤት ሥራዎች ለመስጠት መሆኑን ገልጿል።

“አቡነ ኤርሚያስ ተራራ” የዕፅዋት ሳይንስ መድኃኒት ቅመማ ጋር ተያይዞ ለምርምር የሚሆኑ ሀገር በቀል ዕፅዋቶች በስፋት የሚገኙበት ተራራ በመሆኑ የጥንት መጻሕፍትን በመተርጎም የሚመራመሩ ሊቃውንትን በተራራው በማሰማራት የምርምር ማዕከል እንደሚያደርጉት ታላቅ ተስፋ ስለተጣለባቸው ስያሜው የተሰጠበት አንደኛው ምክንያት እንደኾነ ተገልጿል።

ከከተማዋ መስፋፋት ጋር ተያይዞ እየተስፈፋ የመጣን የደን መራቆት ለመግታት ተራራው በርሳቸው ስም መሰየሙ ደኑ ይበልጥ ተከብሮ እንዲቀጥል ትልቅ አቅም ይሆናል ብሏል የከተማ አስተዳደሩ የገለፀው።

ብፁዕነታቸው ሕወሃት በክልሉ ወረራ በፈፀመበት ወቅት ዘርና ሀይማኖት  ሳይለዩ በማፅናናትና በመልሶ ግንባታ ያደረጉትን  መልካም ሥራ ሁየጠቀሰው አስተዳደሩ ይህህኑ ተግባር  አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ሙሉ እምነት በማሳደር “አቡነ ኤርሚያስ ተራራ” በማለት ተራራው በስማቸው መሠየሙ ተጠቁሟል።

ተራራው ከፍ ያለ ዕይታ ባላቸው አባት ስም መሰየሙ ክብሩ ለተሰየመለት ሰው ብቻ ሳይሆን የብፁዕነታቸውን አገልግሎት ለቀመሰው እና ላጣጣመው ለመላው የወልድያና አካባቢው ሕዝብ እና ከተማ አስተዳደሩ ጭምር ነው ሲል ወልድያ ከተማ ኮሙኒኬሽን አስታውቋል።

አቡነ ኤርሚያስ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የሰሜን ወሎ፣ የደቡብ ወሎና በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የኦሮሞ ብሔረስብ አስተዳደር ሊቀ ጳጳስ ናቸው።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe