ሃይንከን ኢትዮጵያ ለችግረኛ ወገኖች ቤት የሚገነባበትን 4ኛ ዙር ፕሮጀክቱን አስጀመረ

ሃይንከን ኢትዮጵያ “ደራሽ” የተሰኘውን ለችግረኛ ወገኖች ቤት የሚገነባበትን 4ኛ ዙር ፕሮጀክቱን ጀመረ
ሃይንከን ኢትዮጵያ “ደራሽ” የተሰኘውንና በአስቸጋሪ መኖሪያ ቤት ውስጥ ለሚኖሩ ችግረኛ ወገኖች ቤት ገንብቶ የሚያስረክብበትን 4ኛ ዙር ፕሮጀክቱን በዛሬው እለት አስጀምሯል፡፡ ሃይንከን ኢትዮጵያ ፕሮጀክቱን የሚያከናውነው ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር/ አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ጋር በመተባበር ነው፡፡
በዛሬው ዕለት የተከናወነውን የፊርማ መርሐግብር የፈፀሙት በሃይንከን በኩል አቶ ፈቃዱ በሻህ እና አቶ አንዳርጌ ተዋበ የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለከተማ ቤቶች ልማት አስተዳደር ፅ/ቤት ኃላፊ ናቸው።
በዚህ የመግባቢያ ሰነድ ላይ እንደተገለጸው የፕሮጀክት ጠቅላላ ወጪ እስከ 20 ሚሊዮን ብር የሚፈጅ ሲሆን፤ በሶስት ወራት ጊዜ ውስጥም ተጠናቆ በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ አማካኝነት ለነዋሪዎቹ ይተላለፋል፡፡
የሃይኒከን ኢትዮጵያ የሰስቴይነብሊቲ፣ የውጭና መንግስታዊ ጉዳዮችኃላፊ የሆኑት አቶ ፍቃዱ በሻህ እንደገለፁት፤ ሃይንከን ኢትዮጵያ የመጀመሪያውን ደራሽ ፕሮጀክቱን የጀመረው በልደታ ክፍለ ከተማ ከረዩ ሰፈር 53 ደረጃቸውን የጠበቁ መኖርያ ቤቶች ለነዋሪዎች በማስረከብ ነው፡፡ በደራሽ ቁጥር 2 ደግሞ በቀጨኔ ከዕድሜ ብዛት ሊፈርስ በመቃረቡ ምክንያት የነዋሪዎቹን ህይወት አደጋ ላይ ሊጥል የነበረን ከእንጨትና ጭቃ የተሰራ ፎቅና ምድር ህንጻ አፍርሶ በመስራት ለነዋሪቹመልሶ አስረክቧል። ሶስተኛውና ያለፈው ዓመት ፕሮጀክት የተሰራው ቂርቆስ አካባቢ ሲሆን፤ በዚህም 50 ቤቶችን በመስራት ቆርቆሮ በቆርቆሮ በተሰራ ቤት ውስጥ ይኖሩ የነበሩ ወገኖችን ደረጃውን ወደጠበቀ መኖሪያ ቤት አሸጋግሯል፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe