ሃይንከን ኢትዮጵያ ደራሽ በተሰኘውና 25 ሚሊዮን ብር በፈጀ ፕሮጀክቱ በሐረር ለችግረኛ ወገኖች ቤት አስረከበ!

ሃይንከን ኢትዮጵያ ከሐረር ቢራ 40ኛ ዓመት አከባበር ጋር በተያያዘ ለአቅመ ደካሞች የሚያደርገውን 5ኛውን ዙር የቤት ግንባታ መርሃ ግብሩን አጠናቆ በሐረር ከተማ ለሚገኙ ነዎሪዎች የመኖሪያ ቤቶችን ቁልፍ የክልሉ ርዕሰ መስተዳደር ክቡር አቶ ኦርዲን በድሪ በተገኙበት አስረክቧል።
ደራሽ የተሰኘው ይህ ፕሮጀክት 34 ቤተሰቦችን ከ125 ቤተሰቦቻቸው ጋር ተጠቃሚ ያደረገ ሲሆን፤ በሁለት ወር ጊዜ ተጠናቆ ርክክብ ተደርጓል።
የሃይንከን ኢትዮጵያ የሰስቴይኔቢሊቲ የውጭ እና መንግስታዊ ጉዳዮች ሃላፊ የሆኑት አቶ ፍቃዱ በሻህ እንደገለጹት ግንባታው 25 ሚሊዮን ብር የፈጀ ሲሆን፤ ቤቶቹ ከግማሽ ክፍለ ዘመን በላይ በማስቆጠራቸው የነዋሪዎቹን ህይወት ስጋት ውስጥ የከተቱ ነበሩ።
ሃይንከን ኢትዮጵያ በደራሽ ፕሮጀክቱ ላለፉት ተከታታይ አራት ዓመታት በአዲስ አበባ በከረዩ ሰፈር፣ ቀጨኔ፣ ጨርቆስ እና አቃቂ አካባቢዎች ለሚገኙ ዓቅመ ደካሞች 122 ቤቶች ገንብቶ ማስረከቡ የሚታወስ ነው።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe