ለልጆቻችሁ ስትሉ መኖር

በእርስዎና በባለቤትዎ መካከል አንዳች ክፍት ስፍራ አለ፡፡ ይህ ስፍራ ግንኙነታችሁ ነፍስ ዘርቶ የሚኖርበት ስፍራ ነው፡፡ የዚህን ስፍራ መኖር መገንዘብ በማትችሉባቸው ወቅቶች ስፍራውን ታቆሽሹታላችሁ፡፡ ባለመደማመጥ፣ በመረባበሽ፣ ከመመካከር ይልቅ በማጥቃትና በመከላከል ወይም ጨርሶ ነገሮችን በመጠርቀም ታቆሽሹታላችሁ፡፡ በእርስዎና በባለቤትዎ መካከል ያለውን ይህን ክፍት ስፍራ በማታውቋቸው ብዙ ምክንያቶች ልታበላሹት ትችላላችሁ፡፡ ስለዚህ ይህን ክፍት ቦታ ልክ እንደ መሠዊያ ለበጎ ጥቅም ማዋል እንድትችሉ በጥልቀት መተማመን፣ ትሁት እና የተረጋጋ ሆኖ መገኘት እንዲሁም ስለ ልዩነቶቻችሁ አንዳችሁ ሌላችሁ ላይ ከመፍረድ አንዱ የሌላውን የተለየ አስተሳሰብ ለመረዳት መጓጓት አለባችሁ፡፡
ጤናማ የትዳር ግንኙነት ከሁለቱም አካላት መቶ በመቶ የኾነ ጥንቃቄ፣ ኃላፊነት እና ጥረት ይጠይቃል፡፡ በተለይ ልጆች ያሏችሁ ከኾነ፤ ልጆቻችሁ የሚኖሩት በዚህ ክፍት ስፍራ ነውና ስለ ልጆቻችሁ ደስታና ሰላም ስትሉ ክፍቱን ቦታ የቅድስና መስዋዕት ማቅረቢያ፣ ምቹ መኖሪያና ደህንነቱ የተጠበቀ ማድረጉን አትዘንጉ፡፡ በመካከላችሁ ያለው ክፍት ስፍራ የተበላሸ ከኾነ ግን ልጆቻችሁ የተወሳሰበ ስነልቦና ያላቸውና ፍላጎታቸውን ተጭነው ባልተገባ መንገድ የሚያድጉ ሊኾኑ ይችላሉ፡፡
በትዳር ውስጥ መኖር ከባድ የመኾኑን ሐቅ ማንም አይክደውም፡፡ ይሁን እንጂ ችግሩን ተቋቁሞ በአብሮነት መዝለቅ ከተቻለ ጥቅሙ ሁለገብና እጅግ ከፍተኛ ነው፡፡ በተለያዩ ጊዜያት የተደረጉ ጥናቶችም ባለትዳሮች ከወንደላጤዎች ጋር ሲነጻጸሩ የተሻለ ጤና፣ ሀብት፣ ወሲባዊ ሕይወትና ደስተኝነት እንዳላቸው አሳይተዋል፡፡
የጋራ ኑሯችሁ ዕድሜው ሲረዝም ደግሞ ልጆቻችሁ ተጠቃሚ ይኾናሉ፡፡ ወላጆቻቸው የተፋቱ ልጆች ለረጅም ዓመት በትዳር ከቆዩ ባለትዳሮች ልጆች ጋር ሲነጻጸሩ በትምህርት አቅማቸው ዝቅተኛ የኾኑ፣ ጤናቸው የተጎሳቆለ፣ ለአእምሮ ሕመም ተጋላጭ የኾኑ እና ለገንዘብ ችግር የሚዳረጉ መኾናቸውን የተለያዩ ጥናቶች ጠቁመዋል፡፡
ስለዚህ ትዳር የቱንም ያህል አስቸጋሪ ቢኾን ለተሻለ ሕይወትና ለልጆቻችሁ ስትሉ የአብሮነት ኑሯችሁን ቀጥሉ፡፡

መነሻ ምንጭ፡- marriage.com

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe