ለኢፌዲሪ ፕሬዚዳንትና ጠ/ሚር በ200 ሚሊዮን ብር የተገነቡት ቪላዎች፤ በጨረታ ገዢ ሳያገኙ ቀሩ

ለመንግስት ባለስልጣናት ተብለው በ200 ሚሊዮን ብር የተገነቡት ቪላዎች፤ በድጋሚ ጨረታ ገዢ ሳያገኙ ቀሩ
ለከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት መኖሪያነት የተገነቡ ስድስት ቪላ ቤቶችን ለመሸጥ፤ ለሁለት ጊዜ ያህል ጨረታ ቢወጣም ገዢ አለመገኘቱን የፌደራል መንግስት ህንጻ ግንባታ ፕሮጀክት ጽህፈት ቤት አስታወቀ። በአዲስ አበባ ከተማ የተገነቡት ቪላ ቤቶቹ፤ 200 ሚሊዮን ብር ገደማ ወጪ ተደርጎባቸዋል ተብሏል።
ገዢ ያጡት የመኖሪያ ቤቶች የተገነቡት “ከፍተኛ የሀገር መሪዎች አገልግሎታቸውን ጨርሰው በክብር ከመደበኛ ስራቸው ሲሸኙ ለእነሱ መኖሪያ ይሆናሉ” ተብለው እንደነበር የፌደራል መንግስት ህንጻ ግንባታ ፕሮጀክት ጽህፈት ቤት ምክትል ስራ አስኪያጅ አቶ ፈጠነ ጌታሁን ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ገልጸዋል። “ቤቶቹ ውስጥ ይገባሉ ተብሎ ታሳቢ የሚደረገው፤ የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት እና ጠቅላይ ሚኒስትር [የነበሩ] ናቸው” ብለዋል።
የፌደራል መንግስት ቪላ ቤቶቹን ለመጀመሪያ ጊዜ ለጨረታ ያቀረበው በጷጉሜ 2012 ነበር። በዚህ ጨረታ፤ 36 ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ ቢገዙም “አንዳቸውም የወሰዱት የጨረታ ሰነድ ላይ የሚገዙበትን ዋጋ ሞልተው አልመለሱም” ሲሉ አቶ ፈጠነ ገልጸዋል።
የመጀመሪያው ጨረታ ከወጣ አንድ ዓመት በኋላ፤ በመስከረም ወር መጨረሻ ቪላ ቤቶቹ በድጋሚ ለሽያጭ የቀረቡ ቢሆንም ተመሳሳይ ውጤት ተከስቷል። መስከረም 29፤ 2014 የወጣው ጨረታ የዋጋ ማስገቢያ ጊዜ የተጠናቀቀው ከሁለት ቀን በፊት ባለፈው ሰኞ ነበር።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe