ሌተናል ጀኔራል ጥጋቡ ካሁን ቀደም በአዛዥነት ሲያገለግሉ የነበሩትን ኡጋንዳዊ ሌተናል ጀኔራል ቢሲጋይ ኦዎዬሲግይሬን በመተካት ነው ቢሮውን የተረከቡት፡፡
ሌተናል ጀኔራሉ በመከላከያ ሰራዊት ለ34 ዓመታት ሰርተዋል፤በኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊትም በተለያዩ ዘርፎች አገልግለዋል፡፡
የአፍሪካ ህብረት ልዩ መልዕክተኛ እና የአሚሶም ሊቀመንበር ፍንሲስኮ ኪታኖ ማዴራ በስነ-ስርዓቱ ላይ ተገኝተዋል፡፡
‹‹ልዩ መልዕክተኛው ሌተናል ጄኔራል ጥጋቡ የተሰጣቸው ኃላፊነት ከፍተኛ መሆኑን ገልጸው በሚገባ እንደሚወጡትም እተማመናለሁ›› ብለዋል፡፡ የቀድሞው አዛዥ ሌተናል ጀኔራል ቢሲጋይ ኦዎዬሲግይሬን ሰላም በማስከበር ተልዕኳቸው ላበረከቱት ከፍተኛ አስተዋጽኦም አመስግነዋል፡፡
ሌተናል ጀኔራል ጥጋቡ ይልማ ‹‹ምንም እንኳን የተሰጠኝ ተልዕኮ ፈታኝ ቢሆንም የተሰለፍኩበትን ዓላማ ለማሳካት እሰራለሁ›› ብለዋል፡፡