መልሶ ማልማቱ አብያተ ክርስቲያናት ጓሮ ገብቶ ታሪክ ዋጋ እያጣ ነው፡፡

በተለያዩ የሙያ መስኮች ተሰማርተው የሀገር ባለውለታ የነበሩ ሰዎች ታመው በእርዳታ ማሳከም፤ ሲሞቱም በመዋጮ መቅበር የተለመደ ‹ባህል› እየሆነ ከመጣ ውሎ አድሯል፡፡ ጀግኖቻችንን በህይወት እያሉ ውለታቸውን መመለስ ቢያቅተን እንኳ ካረፉ በኋላ በሰላም ከነታሪካቸው እንዲያንቀላፉ መፍቀድ እየተሳነን ነው፡፡
በመልሶ ማልማት ውስጥ ያለችው አዲስ አባባ ካንቀላፉ ዓመታት ያለፋቸው የሀገር ባለውለታዎችን መቃብር ለታሪክ ለማቆየት አልሆንልሽ ያላት ይመስላል፡፡ መልሶ ማልማቱ አብያተ ክርስቲያናት ጓሮ ገብቶ ታሪክ ዋጋ እያጣ ነው፡፡ ከተቀበሩ ዓመታት ያለፋቸው የሀገር ባለውለታዎች ሳይቀሩ ሐውልታቸው እየፈረሰ አፅማቸውን የሚያነሳ እየጠፋ ለፀፀት የሚዳርጉ ነገሮች እየተፈፀሙ ነው፤ ከዓመታት በፊት የታዋቂውን ባለቅኔና ፀሐፌ ተውኔት ቀኝ ጌታ ዮፍታሔ ንጉሴ አፅም ላይ የተፈፀመውን ጉዳይ በመፅሔታችን ላይ መዘገባችን ይታወሳል፡፡እነዚህን የሀገር ባለውለታዎች ብናከብር ክብሩ ለቋሚው ነው፡፡ እነርሱ ግን እንዲህ ማለታቸው አይቀርም፡፡ ስራቸው ህያው ነውና!
ግርማ ሞገስ ያለው እጅግ የሚያኮራ
በእጅ ያልተቀረፀ በሰው ያልተሰራ
ከእስክንድር ምሶሶሰ በቁመት የላቀ
በአሰራሩም ቢሆን እጅግ የረቀቀ
ሐውልት አቁሜያለሁ ለመታሰቢያዬ
ለሚመጣው ትውልድ ለወደ ኋላዬ
የማይፈርስውና የማይበሰብስው
ረቂቅ መንፈሴ ሥጋ የለበሰው
እንደመሰንቆ ምት ወይ እንደ በገና
ይኖራል ወደፊት ብዙ ዘመን ገና…
(እንዲል አሌክሳንደር ፑሽኪን፤አያልነህ ሙላቱ
እንደተረጎመው)

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe