መድን ፈንድ እስከ 200 ሺሕ ብር ለሚሆን የባንክ ተቀማጭ ገንዘብ የዋስትና ሽፋን እንደሚሰጥ ተገለጸ

በባንኮች እና በማይክሮ ፋይናንስ ተቋማት ገንዘብ አስቀማጮች ዋስትና ለመስጠት የተቋቋመው የተቀማጭ ገንዘብ መድን ፈንድ እስከ 200 ሺሕ ብር ተቀማጭ ገንዘብ ላላቸው ዋስትና እንደሚሰጥ ተገለጸ፡፡

ባንኮች እና የማክሮ ፋይናንስ ተቋማት በየዓመቱ ከተቀማጭ ገንዘባቸው 0.2 በመቶ ለፈንዱ ገቢ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል ተብሏል፡፡

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ምክትል ገዥ አቶ ሰለሞን ደስታ ለሪፖርተር ጋዜጣ ተከታዩን ብለዋል ፦

” በየባንኩ ለእያንዳንዱ አስቀማጭ እስከ 200 ሺሕ ብር ለሚሆን ተቀማጭ ገንዘብ የዋስትና ሽፋን ይሰጣል፡፡

የመድን ሽፋኑ መጠን እስከ 200 ሺሕ ብር ለሚሆነው ተቀማጭ ገንዘብ የዋስትና ሽፋኑ እንዲሰጥ የተወሰነው፣ 96 በመቶ ያህል አስቀማጮች የተቀማጭ ገንዘባቸው መጠን የተጠቀሰውን ያህል ስለሆነ ነው።

በዚህ መሠረት የመድን ሽፋኑ ይሰጣል። ይህ ውሳኔ አብዛኞቹን አስቀማጮች የሚሸፍን ነው።

ባንኮች ለዚህ ዋስትና ሽፋን ተቀማጭ የሚያደርጉት በየዓመቱ ከጠቅላላ ተቀማጭ ገንዘባቸው 0.2 በመቶ የሚሆነውን በማስላት ለፈንዱ ገቢ በማድረግ ተፈጻሚ ይሆናል።

የተቀማጭ ገንዘብ ዋስትና ፈንድ አገልግሎት ሲጀመር ባንኮቹ የሚከፍሉት ክፍያ ይኖራል። የገንዘቡ መጠን ግን ገና አልተወሰነም ። “

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe