በአርቲስት ሀጫሉ ሁንዴሳ ግድያ ጥፋኛ የተባለው ጥላሁን ያሚ የእድሜ ልክ ፅኑ እስራት ተፈረደበት

በግድያው ተባብሯል የተባለው 2ኛ ተከሳሽ ከበደ ገመቹ በ18 ዓመት ፅኑ እስራት እንዲቀጣ ተወስኖበታል።

የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 2ኛ የፀረ ሽብርና የህገ መንግስት ጉዳዮች ወንጀል ችሎት ነው የቅጣት ውሳኔውን ያሳለፈው

በግድያው ተባብሯል የተባለው 2ኛ ተከሳሽ ከበደ ገመቹ ደግሞ በ18 አመት ፅኑ እስራት የተቀጣ ሲሆን በወቅቱ ለፀጥታ አካል መረጃ ባለማሳወቅ ጥፋተኛ የተባለው 3ኛ ተከሳሽ አብዲ አለማየሁ በ6 ወር ቀላል እስራት እንዲቀጣ ተወስኖበታል።

የቅጣት ውሳኔውን ያስተላለፈው የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 2ኛ የፀረ ሽብርና የህገ መንግስት ጉዳዮች ወንጀል ችሎት መሆኑን ኤፍ.ቢ.ሲ ዘግቧል።

ዐቃቤ ህግ ጥላሁን ያሚ ከዚህ ቀደም በተለያዩ ወንጀሎች መሳተፉን በመጥቀስ ሶስት የቅጣት ማከበጃዎችን በማቅረብ ተከሳሹ በሞት ይቀጣልኝ ሲል ጠይቆ ነበር።

ፍርድ ቤቱም ከቅጣት አወሳሰን መመሪያ ውጪ በሞት ይቀጣልኝ ሲል ያቀረበውን ጥያቄ ውድቅ በማድረግ እና ሌሎች የዐቃቤ ህግ የቅጣት ማክበጃዎችን በመያዝ ጥላሁን ያሚ በዕድሜ ልክ ፅኑ እስራት እንዲቀጣ ወስኗል።

ተከሳሽ ከበደ ገመቹ ሽጉጥ ገዝቶ ለአንደኛ ተከሳሽ በመስጠቱ እንዲሁም ሀጫሉን ከገደሉ በኋላ ከህግ ሸሽቶ አዳአ ድሬ ላይ መያዙን አቀቤ ህግ አስታውቋል።ተከሳሽ አብዲ አለማየሁን ፍርድ ቤቱ ያመነበትን ቅጣት እንዲጥልበት የጠየቀ ሲሆን፤ ተከሳሾቹ ከዚህ ቀደመ መልካም ባህሪ እንዳላቸው በማቅለያ አቅርበዋል።

አርቲስት ሀጫሉ ሁንዴሳ ሰኔ 21 ቀን 2012 ዓ.ም ከምሽቱ 3፡30 አካባቢ ገላን ኮንዶሚኒየም ተብሎ በሚጠራው ስፍራ በጥይት ተመትቶ ህይወቱ ማለፉም ይታወሳል።

Kumneger Media
Kumneger Media
Kumneger Media is a News and Entertainment Website & Channel. Kumneger Media in addition to News and Entertainment it is the hub of Politics, Movies, Drama, Music, Comedy, Documentary and More!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe