በአሰላ ግጭት ተቀሰቀሰ

በአሰላ ከተማ ከፍተኛ ግጭትና ረብሻ ተቀሰቀሰ!!

አሰላ ላይ ረብሻ እንዳለ የሚጠቁሙ መረጃዎች እየተሰሙ ነው።መረጃዎቹ የሚጠቁሙት አሰላ የማርያም ቤክ ጥምቀት ባህር ወይም የታቦት ማረፊያ ቦታ ላይ መስጊድ መሰራቱን ተከትሎ የማርያም ቤክ ደውል ተደውሎ በትላንትናው ዕለት መስጊዱን አፍርሰውታል። በአሰላ እየተደረገ ያለውን ተግባር በመቃወም ዛሬ ሰልፍ ወጥተው የነበሩት ክርስቲያኖች ጋር አለመግባባት ተከስቶ ከፍተኛ ረብሻ መከሰቱና እንዳልበረደም ተሰምቷል።

መረጃዎቹ የሚጠቁሙት በአሰላ ከተማ 01 ቀበሌ የቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ (አሁን ፖሊ-ቴክኒክ መሰለኝ) አጠገብ አንዲት የበሬ ግንባር የምታክል መሬት አለች። የከተማዋ ነዋሪዎች እንደነገሩ የተወሰኑ ሰዎች በዚህ ክፍት ቦታ መስኪድ እንሰራለን ብለው መንቀሳቀስ ይጀምራሉ።

መስኪዱ የሚሰራው በተለምዶ “ማሪያም ሰፈር” ተብሎ በሚታወቀው ሰፈር ነው። የከተማ መስተዳደሩ ለግንባታው እውቅና እና ፍቃድ ስለመስጠቱ የታወቀ ነገር የለም። ሆኖም ግን በዚህ ምክንያት ዛሬ በአሰላ ከተማ በክርስቲያን እና እስልምና እምነት ተከታዮች መካከል ከፍተኛ ረብሻና ብጥብጥ ተቀስቅሷል።

ጉዳዩ ከከተማ ፖሊስ አቅምና ቁጥጥር ሊወጣ ይችላል። ችግሩ ተባብሶ የሰዎች ህይወትና ንብረት ከመጥፋቱ በፊት የሚመለከታቸው የመንግስት አካላት አፋጣኝ የመፍትሄ እርምጃ ሊወስዱ ይገባል። የከተማዋ ነዋሪዎች ደግሞ በዚህ ምክንያት በሃይማኖት ጎራ ለይተው ፀብና ግጭት ውስጥ ከመግባት ሊቆጠቡ ይገባል። የአከባቢው ሀገር ሽማግሌዎች፣ ቄሶች እና ሼኮች ግጭቱን ለማብረድ መረባረብ ይጠበቅባቸዋል።

Kumneger Media
Kumneger Media
Kumneger Media is a News and Entertainment Website & Channel. Kumneger Media in addition to News and Entertainment it is the hub of Politics, Movies, Drama, Music, Comedy, Documentary and More!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe