“በአንዳንድ ቦታዎችና ምርጫ ጣቢያዎች ከታየው እንግልትና ወከባ፤የቁሳቁስ እጥረት ከፈጠረው ጫና ውጭ ምርጫው ሰላማዊ ነበር”-የአፍሪካ ህብረት ታዛቢ ቡድን

ቡድኑ የትዝብቱን የተጠቃለለ ሪፖርት ከ2 ወራት በኋላ ይፋ እንደሚያደርግ አስታውቋል፡፡

ቡድኑ ምርጫውን የተመለከተ ቀዳሚ የሪፖርት መግለጫ እየሰጠ ነው፡፡

በቀድሞው የናይጄሪያ ፕሬዝዳንት ኦሊሴንጎ ኦባሳንጆ የሚመራው የአፍሪካ ኅብረት ምርጫ ታዛቢ ቡድን ምርጫውንና የድምጽ አሰጣጥ ሂደቱን የተመለከተ ቀዳሚ የሪፖርት መግለጫ እየሰጠ ነው፡፡

ቡድኑ የትዝብቱን የተጠቃለለ ሪፖርት ከ2 ወራት በኋላ ይፋ እንደሚያደርግ በመግለጫው አስታውቋል፡፡

የተመረጡ ጣቢያዎች ላይ ምልከታ አድርገናል ያሉት ኦሊሴንጎ ኦባሳንጆ ምርጫውን ተዘዋውረን በተመለከትንበት፣ የምርጫ ቦርድን ተቋማዊ ጥንካሬ ተመልክተናል፣ መንግስት ምርጫው ሰላማዊ እንዲሆን አስፈላጊ የጸጥታ እርምጃ ተግባራዊ አድርጓል ብለዋል።

ምርጫው ከሞላ ጎደል ሰላማዊ በሆነ መልኩ ነው የተካሄደው ያሉም ሲሆን አንዳንድ ቦታዎች ላይ በተለይም በኦሮሚያ እና በአማራ ክልሎች ከጸጥታ ጋር ተያይዞ ስጋቶች እና በአንዳንድ ምርጫ ጣቢያዎች የተቃዋሚ ፓርቲ ወኪሎችን የማዋከብ እና የማንገላታት ችግሮች እንደነበሩ ገልጸዋል።

በምርጫው እለት የምርጫ አስፈጻሚዎች፣ መንግስት እና የጸጥታ አካላት ስራቸውን በአግባቡ መስራታቸውንም ነው የቁሳቁስ እጥረትና የመራጮች ብዛት በድምጽ አሰጣጡና በቆጠራው ሂደት ላይ ጫናን ፈጥሯል ያሉት ኦባሳንጆ የተናገሩት።

የሲቪክ ማህበረሰብ አካላት በምርጫው የሚያደርጉትን ተሳትፎ መቀጠልና ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ የኢትዮጵያ የዴሞክራሲ ተቋማትን፣ በተለይም ለምርጫ ቢርድ የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናከሮ እንዲቀጥልም ነው የጠየቁት፡፡

ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ በኢትዮጵያ የሚያደርገው ሰብዓዊ ድጋፍ ተጠናክሮ እንዲቀጥልም ጠይቀዋል፡፡

የምርጫ ውጤቱ በሚመለከተው አካል ይፋ እስኪሆን ድረስ ሁሉም ባለድርሻ አካላት በትእግስት ሊጠባበቁ ይገባልም ነው ኦባሳንጆ ያሉት።

ቡድኑ በ5 ክልሎች እና 2 ከተሞች ታዛቢ ልኮ ምርጫውን መታዘቡን አስታውቋል፡፡

ድምጽ ሰጪዎች በምርጫው ደስተኛ መሆናቸውንና የፈለጉትን በነጻነት መምረጣታቸውን ነግረውኛል ያለም ሲሆን የመራጮቹ ትዕግስት አስገራሚ ነበርም ብሏል።

ምርጫውን በ4 ክልሎችና በሁለት ከተማ አስተዳደሮች በ190 የምርጫ ጣቢያዎች ተገኝቶ መታዘቡን የገለጸው የምስራቅ አፍሪካ ተጠባባቂ ኃይል የምርጫ ታዛቢ ቡድን ምርጫው የተረጋጋና ሰላማዊ ነው ማለቱ የሚታወስ ነው፡፡

Kumneger Media
Kumneger Media
Kumneger Media is a News and Entertainment Website & Channel. Kumneger Media in addition to News and Entertainment it is the hub of Politics, Movies, Drama, Music, Comedy, Documentary and More!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe