‘ በደቡብ አፍሪካ የተፈጠረው አመፅ ” የታቀደ” ነበር ‘ ፕሬዝዳንት ራማፎሳ

የደቡብ አፍሪካ የተፈጠረው አመፅ ” የታቀደ” ነበር ሲሉ ሲሪል ራማፎሳ ወቀሱ፡፡

ፕሬዝዳንት ራማፎሳ ትናንት አርብ የአመፁ ዋና ማዕከል ናት የምትባለውን ዋ-ዙሉ-ናታል(KZN) በጎበኙበት ወቅት ነው ይህን ወቀሳ ያሰሙት፡፡

በሀገሪቱ ባለፉት ሳምንታት የነበሩት አመፆችና ዝርፍያዎች ሁሉም በዕቅድ የተመሩ መሆናቸው አሁን ግልፅ እየሆነ መጥቷል ሲሉ ተናግረዋል፡፡

‘ይህን ስርዓት አልበኝነት ማን እንደሚመራው ደርሰንበታል፤ እየተከታተልናቸውም” ያሉት ራማፎሳ ሀገሪቱ ላይ ሁከትና ስርቆት እንዲሰራፋ አንፈቅድላቸውም ሲሉ ዝተዋል፡፡

ባለፈው ረቡዕ 25ሺህ ወታደሮች አመፁን ለመቆጣጠር በስፍራው እንዲሰማሩ መንግስት አዝዟል፡፡

ይህ የወታደሮች ቁጥር አጠቀላይ ሀገሪቱ ካላት 75 በመቶ እንደሚሆን አዣንስ ፍራንስ ፕሬስ በዘገባው አመላክቷል፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe