በፕሪሚየር ሊጉ ፋሲል ከነማ ሐዋሳ ከተማን 2ለ1 አሸነፈ

በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ወንዶች ፕሪሚየር ሊግ የ12ኛ ሳምንት መርሐ ግብር ፋሲል ከነማ ሐዋሳ ከተማን 2ለ1 በሆነ ውጤት አሸንፏል።
ለፋሲል ከነማ በረከት ደስታ በ11ኛው ደቂቃ እንዲሁም አምሳሉ_ጥላሁን በ43ኛው ደቂቃ ጎሎችን አስቆጥረዋል።
ለሐዋሳ ከተማ የማስተዛዘኛዋን ጎል ወንድማገኝ ሀይሉ በ70ኛው ደቂቃ አስቆጥሯል።
ፋሲል ከነማ በ28 ነጥብ መሪነቱን አጠናክሮ ሲቀጥል ሐዋሳ ከተማ በ15 ነጥብ ሰባተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።
በባህርዳር ከተማ እየተካሄደ በሚገኘው የሊጉ 12ኛ ሳምንት መርሐ ግብር የዛሬ ረፋድ 4 ሰዓት ጨዋታ ጅማ አባጅፋር ሲዳማ ቡናን 1ለ0 ማሸነፉ ይታወሳል።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe