ቡና ኢንሹራንስ ከፍተኛ የአረቦን ጭማሪ አስመዝቦ አትራፊ መሆኑን አስታወቀ

ወደ ገበያው ከገባ አምስት ዓመታን ያስቆጠረው ቡና ኢንሹራን አክሲዮን ማህበር ባለፈው የ2017/18 በጀት ዓመት ከፍተኛ የሆነ የአረቦን ጭማሪ በማስመዝገብ ትርፋማ መሆኑን አስታወቀ፡፡

ቡና ኢንሹራን በቅርቡ ባካሄደው የባለአክሲዮኖች ዓመታዊ ጠቅላላ ስብሰባ ላይ የቡና ኢንሹራንስ ዋና ስራ አስፈፃሚ የሆኑት አቶ ዳኛቸው መሀሪ እንዳስታወቁት በሀገራችን የኢንሹራንስ ኢንዱስትሪ ውስጥ የሚሳተፉት የኢንሹራንስ ኩባንያዎች ቁጥር 17 መሆኑን አስታውሰው ከእነዚህ የኢንሹራንስ ኩባንያዎች በተጠናቀቀው የበጀት ዓመት በአጠቃላይ የተሰበሰበው አረቦን 8 ነጥብ 1 ቢሊዮን ሲሆን ቡና ኢንሹራን በኢንዱስትሪው ውስጥ የተመዘገበ የመጨረሻው የኢንሹራንስ ኩባንያ ቢሆንም  በበጀት ዓመቱ 166 ሚሊዮን ብር አረቦን በመሰብሰብ የተሻለ አረፃፀም ማስመዝገቡን አስታውቀዋል፡፡

ዋና ስራ አስረፈፃሚው እንደጠቀሱት የቡና ኢንሹራንስ አፈፃጸም ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ከነበረው 134 ሚሊየን  ጋር ሲነፃፀር የ24 ከመቶ ብልጫ ማስመዝገቡን ጠቅሰው ይህ አሃዝ በኢንዱስትሪው ከተመዘገበው ሁለተኛው ትልቁ ዕድገት እንደሆነና ከኢንዱስትሪው አማካይ ዕድገትም የላቀ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

የእያንዳንዱን የመድን አይነቶች አፈፃፀም ያስረዱት አቶ ዳኛቸው የተሸከርካሪ ህጋዊ ሀላፊነት ኢንሹራንስ 124 ከመቶ፤በባህር በየብስና በአየር የሚጓጓዙ ዕቃዎች ኢንሹራንስ 112 ከመቶ እንዲሁም የጉዞ ዋስትና ኢንሹራንስ 101 ከመቶ ዕድገት ማስመዝገብ መቻሉን ተናግረዋል፡፡

ኩባንያ የተከፈ ካፒታሉን ከ6 ሚሊዮን ብር ወደ 91.9 ሚሊዮን ብር ማሳደግ መቻሉን የጠቀሱት አቶ ዳኛቸው አጠቃላይ ሀብቱንም ወደ 351.5 ሚሊዮን ብር ማድረስ መቻሉን አስረድተዋል፡፡

በቀጣይነትም የአጫጭርና የረዥም ጊዜ ስትራቴጂ በመንደፍ በዚህ ዓመት የተመዘገበውን አመርቂ ውጤት በተሻለ ሁኔታ ለመድገም መላ ሠራተኛው በንቃት እንደሚንቀሳቀስ አስታውቀዋል፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe