ቴክኖ ሞባይል አዲሱን ካሞን 30 ፕሮ 5G ሞዴል በይፋ በኢትዮጲያ አስተዋወቀ

ቴክኖ አዲሱን እና በቅርቡ በባርሴሎናው አመታዊ የቴክኖሎጂ ኤግዚቢሽን ይፋ ያደረገውን ካሞን 30 ፕሮ 5G ሞዴል በይፋ በኢትዮጲያ አስተዋወቀ። የሞባይል ቴክኖሎጂን ጨምሮ የተለያዩ የኤሌክትሮኒክስ ብራንድ  አምራች የሆነው እና ከ70 በላይ ሀገራት ምርቶቹን በስፋት የሚያቀርበው ቴክኖ አዲስ የሞባይል ቴክኖሎጂ ውጤት የሆነውን ካሞን 30 ፕሮ 5G ሞዴል በአዲስ አበባ ሸራተን አዲስ ሆቴል የተለያዩ ሀገራት አምባሳደሮች፣ ከፍተኛ ባለስልጣናት፣ እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት አስተዋወቀ። አዲሱ ካሞን 30 ፕሮ 5G የሶኒ(SONY) የካሜራ ሴንሰር ቴክኖሎጂን ጨምሮ የተለያዩ የቴክኖ ምርምር ውጤት የሆኑ የቴክኖሎጂ ግብዓቶችን አካቶ የተመረተ ሞዴል ነው።

ቴክኖ በቅርቡ በስፔን ባርሴሎና በተካሄደው አንጋፍው እና አመታዊው የቴክኖሎጂ ኤግዚቢሽን (Mobile World Congress) ላይ ይህን አዲስ ካሞን 30 ፕሮ 5G ሞዴልን ጨምሮ የተለያዩ አዳዲስ የቴክኖሎጂ ምርቶቹን በይፋ እንዳስተዋቀ የሚታወቅ ነው፣ በዚሁ የቴክኖሎጂ ኤግዚቢሽን ይፋ የሆነው ቴክኖ ካሞን 30 ፕሮ 5G ሞዴል በማንኛውም አይነት ሁኔታ እና የብርሃን መጠን ሳይገድበው ቁልጭ ያሉ ፎቶዎችን የማንሳት አቅም እንዲኖረው በማሰብ በካሜራ ቴክኖሎጂ አንጋፋው ሶኒ (SONY) ምርት የሆነውን ዘመናዊ ሴንሰር (Sony IMX890) የተገጠመለት መሆኑ ለየት ሲያደርገው በኢንዱስትሪው የመጀመሪያ ነው የተባለለትን ‘PolarAce’ ፖላርኤስ ቴክኖሎጂ በመጠቀም የቪድዮ ኢሜጂንግ ሲስተሙን በማዳበር እና እንከን የለሽ በማድረግ የካሜራ ቴክኖሎጂውን ሁለቱ ኩባንያዎች ወደ ላቀ ደረጃ አድርሰውታል።

ከዚህም በተጨማሪ ፍጥነት እና እንከን የለሽ አገልግሎት እንዲሰጥ የሚያደርገው የፕሮሰሰር አቅም፣ ለረጅም ጊዜ አገልግሎት እየሰጠ መቆየት የሚችል ባትሪ፣ ማራኪ ቅርጽ እና ውበት ያለው የመጨረሻው የቴክኖሎጂ ውጤት የሆኑ የሞባይል ስልክ ግብዓቶችን አካቶ የያዘ ነው። በተለያዩ ዘርፎች ከፍተኛ ተፈላጊነት ያላቸውን አዳዲስ የቴክኖሎጂ ውጤቶችን ከአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ጋር በማቀናጀት ለተለያዩ ግልጋሎቶች የሚውሉ የፈጠራ ውጤቶችን በትኩረት እየሰራ የሚገኘው ቴክኖ ብራንድ የሚያመርታቸው ምርቶች በጥራት እና ዘመናዊነት ተወዳዳሪ እንዲሆኑ በኢንዱስትሪው አንቱታን ካተረፉ የተለያዩ አለም አቀፍ ኩባንያዎች ጋር በመተባበር ስራዎችን በመስራት ላይ ይገኛል።

የቴክኖ ሞባይል ኢትዮጲያ ብራንድ ማናጀር የሆኑት ሚስተር አሌክ ሁዋንግ "ቴክኖ ውድ ለሆኑ ተጠቃሚዎቹ ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎችን ለማቅረብ ለሚያደርገው ከፍተኛ ጥረት ምስክር የሆነውን አዲሱን ካሞን 30 ፕሮ 5G (CAMON 30 pro 5G) በማስተዋወቃችን ደስታ ይሰማናል" ያሉ ሲሆን "አዲሱ ስልክ ዘመኑ በደረሰበት ቴክኖሎጂ ውጤቶችን ከኤ. አይ ሲስተም ጋር በማስተሳሰር አዳዲስ ፈጠራዎችን ያቀረበ ሲሆን ይህም ቴክኖ እንደ ብራንድ በኢንደስትሪው ግባርቀደም ለመሆን እየሰራ ለመሆኑ ማሳያ ነው’’ ብለዋል።

የኢትዮ ቴሌኮም ቺፍ ማርኬቲንግ ኦፊሰር የሆኑት አቶ ሰኢድ አራጋው በዝግጅቱ ላይ እንደተናገሩት ‘’ ኢትዮ ቴሌኮም እና ቴክኖ ሞባይል በጋራ በመሆን ዲጂታል ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ ይሰራሉ’’ ያሉ ሲሆን ’’ የ4G እና 5G ስማርትፎን በሀገራችን ለማቅረብ እና ተደራሽ ማረግ ግባችን ሲሆን ከዚህም ጋር ተያየዞ ቴክኖ ሞባይል በግንባር ቀደምትነት አጋራችን በመሆን ላለፉት አምስት አመታት ከ2.4 ሚልዮን በላይ የቴክኖ ሞባይል ስልኮችን ለገበያ አቅርባል።

በዘርፉ ካሉ የስልክ ብራንዶች ጋር በመወዳደር የተለያዩ አለም አቀፍ ሽልማቶችን ያሸነፈው ካሞን ሲሪየስ ሞዴል camon የተራቀቀ የቴክኖሎጂን በመጠቀም እጅግ አስገራሚ በሆነ ዲዛይን ተመርቶ የቀረበ ሲሆን፣ በፋሽኑ ዘርፍ የተለያዩ ዘመናዊ እና ቅንጡ አልባሳት እና ቦርሳዎችን በማምረት ከሚታወቀው ‘LOEWE’ የተሰኝ አለም አቀፍ ብራንድ ጋር በመተባበር በአይነቱ የመጀመሪያ ነው የተባለለትን ‘tech-leather’ ቴክኖሎጂ በመጠቀም ለአያያዝ ምቾትን የሚሰጡ እና ለእይታ ማራኪ የሆነ ንድፍ የተላበሱ ስልኮቹን ለአለም ገበያ አስተዋውቋል።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe