አሐዱ ባንክ የአባላቱን የፊርማ ስርዓት አከናወነ፡፡ ስራ ሊጀምር እንደሆነም አስታውቋል፡፡

በርካታ ችግሮችንና ፈተናዎችን ተቋቁሞ ከፍተኛ እንቅስቃሴ ሲያደርግ መቆየቱን የገለጸው አሐዱ ባንክ –  በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ አካባቢ በሚገኘው በሰንሻይን ህንጻ ትላንት ሰኔ 29/2013 ዓ.ም ዕለት የአባላቱን የፊርማ ስርዓት አከናወነ፡፡

በአንድ ዓመት ተኩል ጊዜ ውስጥ ምስረታውን አጠናቆ በትላንትናው እለት የመስራቾች የፊርማ ስነ ስርዓት ያከናወነው የአሐዱ ባንክ አክሲዮን ማኅበር የቦርድ ተወካይ አቶ አንተነህ ሰብስቤ፤ የኮቪድ-19 ወረርሺኝን ተከትሎ የባንኩ ምስረታ ፈታኝ ችግሮች ገጥመውት እንደነበር አስታውሰው አሁን ላይ እንቅስቃሴው ተጠናቆ ወደ ስራ ሊገባ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡

አጠቃላይ መረጃዎች ለብሔራዊ ባንክ ገብቶ በመጽደቁ ቀጣይ ወደሆነው እርምጃ መገባቱን አስረድተዋል፡፡

ባንኩ የሚፈለግበትን 500 ሚሊዮን ብር ካፒታል ጣሪያ አሟልቶ እንዲሁም ከ750 ሚሊዮን በላይ የተፈረመ ካፒታል ይዞ ወደ ቀጣይ ስራ የገባ ሲሆን በቅርቡ ሰንሻይን ህንጻ በሚገኘው ዋና መስሪያ ቤት ስራ እንደሚጀምርም አስታውቀዋል፡፡

የባንክ እና የፋይናንስ ዘርፉ በኢትዮጵያ ገና ጅማሮ ላይ መሆኑን የተናገሩት አቶ አንተነህ ብዙሃኑን ህዝብ ወደ ባንክ አሰራር ለማምጣት፣ አጠቃላይ አሰራሩን ዘመናዊ እና ዲጂታል ለማድረግ እንዲሁም በአንስተኛ የፋይናንስ ተቋማት በኩል ብዙሃኑን ተደራሽ ለማድረግ ያቀደ መሆኑን ለመገናኛ ብዘሃን በሰጡት መግለጫ አሳውቀዋል፡፡

ባንኩ ወደስራ ገብቶ በሚከፈትበት ጊዜ ሃያ አምስት ቅርንጫፎች ሲኖሩት በየዓመቱ መጀመሪያ ላይ አጠቃላይ በኢትዮጵያ ሃምሳ ቅርንጫፎች እንደሚኖሩት ተገልጿል፡፡

አሐዱ ባንክ አ.ማ. ምስረታውን በማጠናቀቅ ስራ ለመጀመር በመቃረቡ የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክቱንም አስተላልፏል።

Kumneger Media
Kumneger Media
Kumneger Media is a News and Entertainment Website & Channel. Kumneger Media in addition to News and Entertainment it is the hub of Politics, Movies, Drama, Music, Comedy, Documentary and More!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe