ኢትዮጵያ በቶኪዮ ኦሎምፒክ ከዓለም 56ኛ ከአፍሪካ 5ኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቃለች

ኢትዮጵያ ኦሎምፒኩ ላይ በአትሌቲክስ፣ ብስክሌት፣ ውኃ ዋናና በቴኳንዶ ትሳተፋለች።

አሜሪካ በ113 ሜዳሊያዎች ከዓለም 1ኛ ደረጃን የያዘች ሲሆን፤ 93 ሀገራት የሜዳሊያ ሰንጠረዥ ውስጥ መግባት ችለዋል።

ኢትዮጵያ በቶኪዮ ኦሎምፒክ በሜዳሊያ ሰንጠረዥ ከዓለም 56ኛ ከአፍሪካ ደግሞ 5ኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቃለች።

ላለፉት ሁለት ሳምንታት ሲካሄድ የቆየው 32ኛው የ2020 የቶኪዮ ኦሎምፒክ በትናትናው እለት ፍጻሜውን አግኝቷል።

በዘንድሮው የ2020 የቶኪዮ ኦሎምፒክ ላይ ከ205 ሀገራት የተውጣቱ ከ11 ሺህ በላይ አትሌቶች መሳተፋቸው የተገለጸ ሲሆን፤ ኢትዮጵያም በመድረኩ ላይ በውስጡ 65 አትሌቶችንና አስላጣኖችን ያካተተ በአጠቃላይ በ90 ሰዎች ተወክላ ተሳትፋለች።

በቶኪዮ ኦሎምፒክ ላይ 33 አይነት ስፖርታዊ ጨዋታዎች የተካሄዱ ሲሆን፤ ኢትዮጵያም ኦሎምፒኩ ላይ በ4 የስፖርት አይነቶች ማለትም በአትሌቲክስ፣ ብስክሌት፣ ውኃ ዋናና ከቴኳንዶ ትሳተፋለች።

ከእነዚህም በአትሌቲክስ ዘርፍ የሜዳሊያ ሰንጠረዥ ውስጥ መግባት የቻለችው ኢትዮጵያ በአጠቃላይ በመድረኩ 1 የወርቅ፣ 1 የብር እና 2 የነሃስ በድምሩ 4 ሜዳሊያዎችን ይዛ ተመልሳች።

ለኢትዮጵያ ሜዳሊየ ያስገኙ ትሌቶችም

1 አትሌት ሰለሞን ባረጋ በ10000 ሜትር የወርቅ ሜዳሊያ

2 አትሌት ለሜቻ ግርማ በ3000 ሜትር መሰናክል የብር ሜዳሊያ

3 አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ በ5000 ሜትር የነሃስ ሜዳሊያ

4 አትሌት ለተሰንበት ግደይ በ10000 ሜትር የነሃስ ሜዳሊያ

በዚህም መሰረት በሜዳሊያ ሰንጠረዡ ኢትዮጵያ በሰበሰበቸው ሜዳሊያዎች ከዓለም 56ኛ ከአፍሪካ ደግሞ 5ኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቃለች።

የሜዳሊያ ሰኝጠረዡን አሜሪካ በ39 የወርቅ፣ 41 የብር እና 33 የነሃስ በድምሩ በ113 ሜዳሊያዎች ከዓለም 1ኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቃለች።

ቻይና በ38 የወርቅ፣ 32 የብር እና 13 የነሃስ በድምሩ በ88 ሜዳሊያዎች ከዓለም 2ኛ ደረጃን ስትይዝ፤ አሰተናጋጇ ጃፓን ደግሞ በ27 የወርቅ፣ 14 የብር እና 17 የነሃስ በድምሩ በ58 ሜዳሊያዎች ከዓለም 3ኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቃለች።

ብሪታኒያ በ22 የወርቅ፣ 21 የብር እና 22 የነሃስ በድምሩ በ65 ሜዳሊያዎች 4ኛ ደረጃ፤ ሩሲያ በ20 የወርቅ፣ 28 የብር እና 23 የነሃስ በድምሩ በ71 ሜዳሊያዎች ከዓለም 5ኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቀዋ።

በአፍሪካ ደረጃ ደግሞ ኬንያ በ4 የወርቅ፣ 4 የብር እና 2 የነሃስ በድምሩ በ10 ሜዳሊያዎች ከዓለም 19ኛ ከአፍሪካ 1ኛ ደረጃን በመያዝ ማጠናቀቅ ችላለች።

ኡጋንዳ በ2 የወርቅ፣ 1 የብር እና 1 የነሃስ በድምሩ በ4 ሜዳሊያዎች ከዓለም ከዓለም 36ኛ ከአፍሪከ 2ኛ ስትሆን፤ ደቡብ አፍሪካ በ1 የወርቅ እና በ2 የነሃስ ሜዳሊያዎች ከዓለም 52ኛ፤ ከአፍሪካ 3ኛ፣ ግብፅ በ1 የወርቅ፣ 1 የብር እና 4 የነሃስ በድምሩ በ6 ሜዳሊያዎች ከዓለም 54ኛ ከእፍሪካ ደግሞ 4ኛ ደረጃን በመያዝ ማጠናቀቅ ችለዋል።

ኢትዮጵያም በ2020 የቶኪዮ ኦሎምፒክ ላይ በመድረኩ 1 የወርቅ፣ 1 የብር እና 2 የነሃስ በድምሩ 4 ሜዳሊያዎች ከዓለም 56ኛ ከአፍሪካ ደግሞ 5ኛ ደረጃን በመያዝ ማጠናቀቅ ችላለች።

በቶኪዮ 2020 ኦሎምፒክ ላይ 93 ሀገራት የሜዳሊያ ሰንጠረዥ ውስጥ መግባት እንደቻሉም ከስፍራው ያገኘው መረጃ ያመለክታል።

በቶኪዮ ኦሎምፒክ ላይ 33 አይነት ስፖርታው ጨዋታዎች የተካሄዱ ሲሆን፤ በውድድሩ ላሸነፉ አትሌቶችም 5 ሺህ ሜዳሊያዎች ለሽልማት ተዘጋጅተዋል።

Kumneger Media
Kumneger Media
Kumneger Media is a News and Entertainment Website & Channel. Kumneger Media in addition to News and Entertainment it is the hub of Politics, Movies, Drama, Music, Comedy, Documentary and More!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe