እርምጃ ስለተወሰደባቸው ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት

‹የግል ከፍተኛ የትምህተርት ተቋማት ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እያሻቀበ በመምጣቱ ምክንያት የሚስተዋሉ ውስብስብ ችግሮች አሉ› ይላል የከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር በቅርቡ ለፖርላማው ያቀረበው የስድስት ወር እቅድ አፈፃፀም ሪፖርት፤ በሚኒስትሯ በፕሮፌሰር ሂሩት ወ/ማርያም የቀበረው ይህ ሪፖርት በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ላይ የተወሰደ የማገድና ትምህርት የማቋረጥ እርምጃ እስከ በወንጀል መጠየቅ የደረሰ ውሳኔ ማስተላለፉን ይፋ አድርገዋል፤
እናስ? እናማ የሚስተዋሉ ችግሮች ይላሉ ሚኒስትሯ ለፖርላማው ባቀረቡት ሪፖርት ላይ ‹ከሚስተዋሉ ችግሮች መሀከል ፈቃድ ባልተሰጠበት ፕሮግራም ተማሪዎችን መዝግቦ ማስተማር፤ፈቃድ ባልተሰጠበት ካምፖስ ወይም ቅርንጫፍ ማስተማር፤የመግቢያ መስፈርት የማያሟሉ ተማሪዎችን መዝግቦ ማስተማር፤ባልተፈቀደ ስርዓት ትምህርት ማስተማር፤ለአንድ ትምህርት የሚያስፈልገውን የመምህራን ቁጥርና ስብጥር አለማሟላት፤ ለጤና ትምህርት ፕሮግራሞች የላብራቶሪና የማሳያ ክፍሎችን በተገቢው ቁሳቁስ አለማሟላትና አለማደራጀት ከሚጠቀሱ ችግሮች መሀከል ይገኛሉ ብለዋል፤
እናስ? እናማ እርምጃው በግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ላይ ብቻ ሳይሆን ህግን በተላለፉ የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች ላይም ተወስዷል ብለዋል፤ እርምጃው የተወሰደው የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች ከግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ጋር በትብብር ሲሰጧቸው የነበሩ ፕሮግራሞች በሙሉ እንዲቀረፁ መደረጉን ሚኒስትሯ ተናግረዋል፡፡
ለምሳሌ ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ እውቅና ከሌለው ዮም ኢኮኖሚ ልማት ተቋም ጋር፤ ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ እውቅና ከሌለው ናሽናል ኮሌጅ ጋር፤ሀረማያ ዩኒቨርሲቲ ከሌላው እውቅና ከሌለው አዲስ ኮንትኔንታል የጤና ኮሌጅ ጋር፤ጅማ ዩኒቨሰርሲቲ ደግሞ ከኤቢኤች ካምፖስ ጋር ሲሰጥ የነበረው ትምህርት እንዲቆም ተደርጓል ብለዋል፤
በግል ከፍተኛ የትምህር ተቋማት ላይ የተወሰደ እርምጃን ሲጠቅሱ ደግሞ ፓራዳይዝ ኮሌጅ አድዋ ካምፓስ ባልተፈቀደ የትምርት ፕሮግራም ተማሪዎችን ተቀብሎ መዝግቦ ሲያስተምር በመገኘቱ ፤ ኢትዮ ስማርት ኮሌጅ አዳማ ካምፓስ በኤምቢኤ አንድ ፕሮግራም የተሰጠውን ፈቃድ በሰባት የሁለተኛ ዲግሪ ፕሮግራም እውቅና እንደተሰጠው በመግለፅ ተማሪዎችን መዝግቦ ሲያስተምር በመገኘቱ፤ እንዲሁም በጋምቤላ ክልላዊ መንግስት የሚገኙ አምስት ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ማለትም ላክጆር ኮሌጅ፤ሾቢል ኮሌጅ፤ዌስተርን ኮሌጅ፤ሉተራን ትርኒቲ ኮሌጅና ብራይት ኦፍ ጋምቤላ ኮሌጅ የትምህርት እውቅና ፈቃድ ሳይሰጣቸው ሲያስተምሩ በመገኘታቸው ትምህርቱን እንዲያቋጡ በማድረግ በወንጀል ተጠያቂ ለማድረግ እየሰራ ነው ብለዋል፤
ለመሆኑ እነዚህ የትምህርት ተቋማት የግሎቹስ የግል ቢዝነስ ነው የሚሰሩት ተብሎ ሊታስብ ይችላል፤ የመንግስት የትምህርት ተቋማት የዚህ አይነት ትምህርት ሲያስተምሩ መንግስት የት ነበር የሚል ጥያቄ ከህዝብ እንደራሴዎቹ ተነሳ አልክ? አይመስለኝም አልተነሳም፤ የግሎቹስ የዚህ አይነት ፍቃድ ባልተሰጣቸው የትምህር ፕሮግራሞች ተማሪዎችን አስተምረው አስመረቅን ሲሉ የት ሄዳችሁ ነበር ብሎ የጠየቀ የፖርላማ አባልስ ነበር ወይ አልክ? የጠየቀ የለም፤ እንደውም እንድ ወዳጄ ሪፖርቱን ካነበበ በኋላ ምን አለ መሰለህ? የህዝብ እንደራሴዎቹ ራሳቸው የያዙት ዲግሪ ከእነዚሁ ኮሌጆች የተሰጠ ላለመሆኑ ምን ማረጋገጫ አለ? በል ቻዎ…

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe