እንግሊዛውያን አብዝተው ወሲብ እየፈጸሙ አይደለም ተባለ

በሀገር አቀፍ ደረጃ የተከናወነ አንድ ጥናት እንግሊዛውያን ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ብዙ ወሲብ እየፈጸሙ እንዳልሆነ አመለከተ።

‘ብሪቲሽ ሜዲካል ጆርናል’ ላይ የሰፈረው ጥናት እንደሚያመላክተው፤ በጥናቱ ከተሳተፉት መካከል ሲሶው ባለፈው አንድ ወር ወሲብ አልፈጸሙም።

በጥናቱ ምላሻቸውን ከሰጡት ከ34,000 ሰዎች መካከል ከ16-44 ዕድሜ የሚገኙ ግማሽ ያህሉ ቢያንስ በሳምንት አንድ ግዜ ወሲብ እንደሚፈጽሙ ተናግረዋል።

እድሜያቸው ከ25 ዓመት በላይ የሆኑ እና አብረው የሚኖሩ ጥንዶች ባለፉት ዓመታት ለተመዘገበው አነስተኛ የወሲብ መጠን ትልቁን ድርሻ አበርክተዋል ተብሏል።

የጥናቱ ውጤት እንደሚያመላክተው፤ 41 በመቶ የሚሆኑ ዕድሜያቸው ከ16-44 የሚሆኑት ተሳታፊዎች ባለፈው አንድ ወር ቢያንስ በሳምንት አንድ ግዜ ወሲብ ፈጽመዋል።

ባለፈው አንድ ወር ወሲብ አልፈጸምኩም የሚሉ ሴቶች ቁጥር በ6 በመቶ የጨመረ ሲሆን የወንዶች ቁጥር ደግሞ በ3 በመቶ ጨምሯል።

ቁጥሩ ለምን ቀነሰ?

ተመራማሪዎች እንደሚሉት እንግሊዛውያን ወሲብ መፈጸም የቀነሱት ድንግል ሆኖ ለመቆየት ካለ ፍላጎት ጋር የሚያያዝ አይደለም።

ይልቁንም ወሲብ የመፈጸም ቁጥር የቀነሰው ከዚህ ቀደም ብዙ ወሲብ ይፈጽሙ በነበሩ ሰዎች ዘንድ ነው። እድሜያቸው ጠና ያለ ባለትዳሮች ወሲብ የሚፈጽሙበት ግዜ እያሽቆለቆለ ነው።

ይህ በእንዲህ እንዳለ በጥናቱ ከተሳተፉ ግማሽ ያህሉ ሴቶች እና ሁለት ሦስተኛ የሚሆኑት ወንዶች አሁን ከሚፈጽሙት በላይ በበለጠ ወሲብ መፈጸም እንፈልጋለን ብለዋል።

ብዙ ግዜ ወሲብ መፈጸም እንደሚፈልጉ የጠቆሙት ደግሞ አብዛኛዎቹ በትዳር ወይም አብረው የሚኖሩ ጥንዶች ናቸው።

ሥራ በዛ? ድካም ወይስ ጭንቀት?

የጥናቱ መሪ የሆኑት ፕሮፌሰር ኬይል ዌሊንግስ ”የሚደንቀው ነገር በዚህ ተጎጂ የሆኑት በመካከለኛ የዕድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ ሰዎች ናቸው። እኚህ ወንድ እና ሴቶች ብዙ ጊዜ በሥራ የሚወጠሩ፣ ልጆቻቸውን እና በእድሜ የገፉ ወላጆቻቸውን የመንከባከብ ኃላፊነት ያለባቸው ሰዎች ናቸው” ይላሉ።

ፕሮፌሰር ኬይል የጥናቱን ውጤት ሲያስረዱ ”ለሰው ልጅ ጤንነት ዋናው ነገር ምን ያህል ግዜ ወሲብ ተፈጸመ የሚለው ሳይሆን ወሲብ መፈጸም ምን ያክል ትርጉም ይሰጣል የሚለው ነው” ይላሉ።

ፕሬፌሰሩ እንደሚሉት፤ በርካቶች በውስጣቸው ሌሎች ሰዎች ከእነሱ በተሻለ መልኩ ብዙ ወሲብ እንደሚፈጽሙ ሊያስቡ ይችላሉ።

“ይህ ጥናት ግን በተመሳሳይ መልኩ በርካቶች ብዙ ወሲብ እንደማይፈጽሙ እና ብቻቸውን እንዳልሆኑ እንዲሰማቸው ያደርጋቸዋል” በማለት ያስረዳሉ።

የወሲብ አማካሪው ፒተር ሳዲንግተን ግን ”ዋናው ጥራት እንጂ ብዛት አይደለም። አንድ ሰው በድርጊቱ ደስተኛ ከነበረ የመድገሙ አጋጣሚ ከፍ ያለ ነው። ይሁን እንጂ ለወሲብ ጊዜ መስጠት ያስፈልጋል። እንደው በድንገት የሚደረግ ነገር አይደለም። ምናልባትም በማስታወሻችን ላይ ቀጠሮ ማኖር ሊረዳን ይችላል” ይላሉ።

ምንጭ፡ ቢቢሲ

Kumneger Media
Kumneger Media
Kumneger Media is a News and Entertainment Website & Channel. Kumneger Media in addition to News and Entertainment it is the hub of Politics, Movies, Drama, Music, Comedy, Documentary and More!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe