‹እጃችን ሲያጥር› እንዲህ ብናደርግስ?

ኢኮኖሚክስ ማለት እንደ ገንዘብ እና ጊዜ ያሉ ሀብቶቻችንን በሚገባ ሁኔታ ተጠቅመን እንዴት ውጤታማ መኾን የሚያስችል ሳይንስ ነው፡፡ ‹‹ምንም ዓይነት ነፃ ምሳ የለም›› እንደሚባለው ምሳውንም በአግባቡ ለመጠቀም ራሱን የቻለ ብልሐት ይጠይቃል፡፡ በኑሯችን ውስጥ የሚፈጠር ማንኛውም እጥረት በዓይን የሚታይና አካላዊ ብቻ ሳይኾን ከአስተሳሰብና ከስሜት ጋር የሚገናኝም ነው፡፡ ስለዚህ በእንዲህ ዓይነት እጥረት ወቅት ኑሯችንን መምራት የሚያስችሉ መፍትሔዎች መጠቀም ተገቢ ነው፡፡
1. ቅድሚያ መስጠት፡- የነገሮች እጥረት በሚገጥመን ወቅት ማድረግ የሚገባን ዋጋው ከፍ ላለና ጥቅሙ የተሻለ ለሆነ ነገር በቅድሚያ ትኩረት መስጠት ነው፡፡ ከሰዎች ጋር በምናደርገው ቀጠሮ ሰዓታችን ከምናስበው በላይ ያጠረ ከኾነ ጉዳያችን አሳሳቢ ለኾነ ሰዎች ቅድሚያ እንስጥ፡፡
2. ነፃ የሚገኙ ላይ ትኩረት ማድረግ፡- እጥረት ሲኖር ከገንዘብ ይልቅ ገንዘብ የማያስወጡ ነገሮች ላይ ትኩረት ማድረግ ተገቢ ነው፡፡ ወይም ዋጋቸው አነስተኛ ለኾነ ነገሮች ቅድሚያ ለመስጠት ይሞክሩ፡፡
3. ፍላጎትን መቀነስ፡- እጥረት ከፍላጎት ጋር የሚኖረው ግንኙነት መታየት አለበት፡፡ ‹ሁለት እግር አለኝ ተብሎ ሁለት ዛፍ ላይ አይወጣም› እንዲሉ የቱንም ያህል መጠን ያለው ገንዘብ ቢኖረን የፈለግነውን ነገር ሁሉ መግዛት አንችልም፡፡ ስለዚህ ፍላጎታችንን በልክ እናድርገው፡፡ ይህን የማድረጊያው አንዱ መንገድ አቅማችን መግዛት የማይችላቸው ነገሮች ባሉበት አካባቢ አዘውትሮ አለመገኘት ነው፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ የማንፈልጋቸውን ነገሮች በግልጽ እንደማንፈልጋቸው በድፍረት መናገር መቻል ያስፈልጋል፡፡ በይሉኝታ ወይም ከሰው እኩል ለመኾን አቅማችን የማይችለውን ነገር ምንም ዓይነት ዕዳ ውስጥ ላለመግባት ቆፍጠን ማለት ይኖርናል፡፡
4. በእጅ ላለው ማድላት፡- ዛሬን መኖር ካቻልን ስለነገ ማሰብ አንችልም፡፡ እጃችን እንዳጠረ ስናስብ ደግሞ ይበልጥ ማድላት ያለብን ለዛሬ ሁኔታችን ነው፡፡ ዛሬን ሰስተን ሕክምና ከመውሰድ ይልቅ ገንዘቡን ለነገ ማስቀመጥ ነገን በሕይወት ኖሮ ገንዘቡን ለሌላ ነገር መጠቀም እንዳንችልም ያደርገናልና በእጃችን ላለችው ዛሬ እናድላ፡፡
5. ቅንጦት መቀነስ፡- በዙሪያችን ያሉትን ነገሮች ልብ ብለን እንመልከት፡፡ የትኛው መሠረታዊ፣ የትኛው ትርፍ መኾኑን እንመርምር፡፡ በእጥረት ወቅት ለመሠረታዊ ነገሮች ትኩረት በመስጠት በዙሪያችን ያሉ ትርፍ ነገሮችንና በተለይም የገንዘብ፣ የጊዜ እና የጉልበት ወጪ የሚጠይቁትን እንቀንስ፡፡

መነሻ ምንጭ፡- psychologytoday.com

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe