ዋሽንግተን ለግብፅ F-15 ጄቶች ልታቀርብ ነው!

የመካከለኛው ምስራቅ ከፍተኛ የአሜሪካ ጦር ጄኔራል ዩናይትድ ስቴትስ ለግብፅ ኤፍ-15 አውሮፕላኖችን እንደምትሰጥ መናገራቸውን ሮይተርስ ዘግቧል፡፡የዩናይትድ ስቴትስ የማዕከላዊ ዕዝ ኃላፊ ጄኔራል ፍራንክ ማኬንዚ በኮንግረሱ ላይ ‘‘ረጅም ጠንካራ እና ኢላማውን በአግባቡ የሚመታ F-15 ልንሰጣቸው መሆኑ መልካም ዜና ነው” ማለታቸው ተሰምቷል ፡፡

ማክኬንዚ በምን ያህል ጊዜ ወይም በቁጥር ስንት F-15 አውሮፕላኖች እንደሚሰጡ ዝርዝር መረጃ አልሰጡም።ባለፈው ወር የፕሬዚዳንት ጆ ባይደን አስተዳደር ለሀገሪቱ የሚሰጠውን 130 ሚሊዮን ዶላር በሰብአዊ መብት ስጋት ምክንያት ማቋጡን ማናገሩ የሚታወስ ነው፡፡

ማክኬንዚ በግብፅ ጎብኝት ማድረጋቸው ተከትሉ ግን ለግብፅ “በጣም ጠንካራ” ወታደራዊ እርዳታን እንዲሰጥ አፅንዖት በመስጠት ሲናገሩ ተደምጧል።በሕዝብ ብዛት የምትታወቀው ግብፅ በአረብ ሀገራት ወሳኝ አጋር እና ቁልፍ ድምጽ ነች።የአሜሪካ የጦር መርከቦች በስዊዝ ካናል በኩል እንዲያልፉ እና ለአሜሪካ ወታደራዊ አውሮፕላኖች ያለገደብ በረራ በመስጠትም ግብፅ ሚናዋ ከፍተኛ መሆነን የዋሽንግተን ወታደራዊ ባለስልጣናት ሲናገሩ ቆይተዋል።

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe