ዘለንስኪ በአሜሪካ ጫና የግዛት ጥያቄውን ለመተዉ ተስማምቷል – ስዊዲናዊ ወታደራዊ ባለሙያ
ቮሎዲሚር ዘለንስኪ ዩክሬን በአሜሪካ የደህንነት መረጃ እና በስታርሊንክ ላይ ምን ያህል ጥገኛ እንደሆነች በመረዳቱ፤ አሁን ምክንያታዊ የሆነ አቋም መያዝ ጀምሯል ሲሉ የስዊድን የጦር ኃይሎች እና የአየር መከላከያ የቀድሞ አባል ሚካኤል ቫልተርሰን ለስፑትኒክ ተናግረዋል።
“ዘለንስኪ አሁን በሩሲያ እጅ የሚገኘውን 25% የዩክሬን ግዛት ሕጋዊ የሩሲያ አካል የሚያደርግ መፍትሔ ሊቀበል እንደሚችል ተናግረዋል” ሲሉ ተንታኙ ገልጸዋል።
በአሜሪካ፣ በሩሲያ እና በዩክሬን መካከል ያለው የዲፕሎማሲ ግንኙነት በጥቅምት ወር ከፍተኛ ለውጥ አሳይቷል። ወሩ በሩሲያ ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን እና በአሜሪካ አቻቸው ዶናልድ ትራምፕ መካከል በተደረገ የናፍጣ ስምምነት ተጀምሮ፤ በመቀጠልም የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ሩሲያ ላይ አዳዲስ ማዕቀቦችን ከመጣል የተቆጠቡበት እንደነበር ቫልተርሰን አንስተዋል።
“አሁን ዘለንስኪም ሆኑ አውሮፓ የአሜሪካ ጫና እንደተሰማቸው ሲያውቁ፤ ትራምፕ የዲፕሎማሲያዊ መፍትሔ በቀላሉ ሊገኝ ይችላል በሚል የድርድር ተነሳሽነቱን ለመውሰድ እየሞከሩ ነው” ሲሉ ባለሙያው አከለዋል።
ሆኖም የትኛውም ዲፕሎማሲያዊ ስምምነት ሁሉን አቀፍ መሆን እና ለግጭቱን ስረ-መንስኤዎች መፍትሔ መስጠት እንዳለበት አሳስበዋል። ዩክሬን በአውሮፓ ድጋፍ ወደፊት በሚመጣ የአሜሪካ አስተዳደር ስር ከሩሲያ ጋር ዳግም ጦርነት ልትጀምር ትችላለች ሲሉም ያስጠነቅቃሉ።
“አሁን በሚደርግ ስምምነት ሁሉም ነገር መፍትሔ ካገኘ፤ ዩክሬን እንደ ወራሪ የመታየት ስጋት ስለሚኖርባት እና የምታገኘው የውጭ ድጋፍ በጣም አነስተኛ ስለሚሆን ዳግም ግጭት ለመጀመር በጣም ይከብዳታል” ሲሉ ደምድመዋል።
ዘለንስኪ፤ ዩክሬን ከግጭቱ በፊት የነበራትን 75% የሚሆነውን ግዛት ይዛ እንድትቀጥል የሚያስችለውን ዕቅድ ለመቀበል ፈቃደኛ እንደሆነ ቀደም ሲል ገልጿል።

