የሚኒስትሮች ምክር ቤት የጦር መሳሪያ ቁጥጥር ረቂቅ አዋጅ ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳለፈ

የሚኒስትሮች ምክር ቤት በዛሬው እለት ባካሄደው 67ኛ መደበኛ ስብሰባው የጦር መሳሪያ ቁጥጥር ረቂቅ አዋጅ ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳለፈ።
 
ረቂቅ አዋጁ የጦር መሳሪያ ቁጥጥር የሀገርንና የህዝብን ሰላምና ፀጥታ ለማስጠበቅ እንዲሁም የዜጎችን እና የህዝቦችን መብትና ደህንነት ለማስከበር አስፈላጊ መሆኑን በመገንዘብ እንዲሁም ግለሰቦች የታጠቋቸውን የጦር መሳሪያዎች የህብረተሰቡን ሰላምና ፀጥታ ለማስጠበቅ ተግባር ሊውሉ የሚችሉበትን እድል መፍጠር አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ መዘጋጀቱ ተገልጿል።
 
በስራ ላይ ባሉ ህጎችና አሰራሮች ያልተፈተሹ ጉዳዮችን በዝርዝር ህግ መደንገግ እና ወጥነት ያለው ስርዓት መፍጠር በማስፈለጉ እንዲሁም ሀገሪቱ ያፀደቀቻቸውን ህገ ወጥ የጦር መሳሪያ ቁጥጥርን የሚመለከቱ ዓለም አቀፍ ስምምነቶችን ለማስፈፀምና ዓለም አቀፍ ትብብር ለማድረግ የሚያስችል ስነ ስርዓት መዘርጋት አስፈላጊ በመሆኑ ነው ጠቅላይ አቃቤ ህግ የጦር መሳሪያ አስተዳደርና ቁጥጥር ረቂቅ አዋጅ ያዘጋጀው።
 
የሚኒስትሮች ምክር ቤትም በቀረበለት ረቂቅ አዋጅ ላይ ከተወያየ በኋላ አንዳንድ ማስተካከያዎችን በማከል ተቀብሎ ያፀድቀው ዘንድ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መላኩን ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
SourceFANA
Kumneger Media
Kumneger Media
Kumneger Media is a News and Entertainment Website & Channel. Kumneger Media in addition to News and Entertainment it is the hub of Politics, Movies, Drama, Music, Comedy, Documentary and More!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe