የሩሲያ የስነ-ምግብ ባለሙያ ማጨስን ለማቆም ይረዳሉ ያሏቸውን ምግቦች ለይተዋል

ወትት የማጨስ ፍላጎትን ለመቀነስ ይረዳል ብለዋል ተመራማሪው፡፡

ተመራማሪው ወተት መጠጣት የማጨስ ፍላጎት እንዲቀንስ እንደሚያደርግ ገልጸዋል፡፡

የሩሲያ የስነ-ምግብ ተመራማሪ ማጨስን ለማቆም የሚፈልጉ ሰዎች ወተት፣ ፍራፍሬና የፍራፍሬ ጁስና ጁስን ጨምሮ መብላት ያለባቸውን የምግብ አይነቶች ለይተዋል፡፡

ማሪና ማኪሻ የተባለው የሩሲያ ተመራማሪ ለሞስኮው24 የማጨስ ፍላጎትን ስለሚቀንሱ ምግቦች ተናግረዋል፡፡ የሚያጨስ ሰው ተመራማሪው የጠቀሷቸውን ምግች ከበላ፤ ከሌሎች ምግቦች አንጻር ሲታይ የማጨስ ፍላጎት እንደሚቀንስ ገልጸዋል፡፡

“ትንሽ ወተት ከወሰዱ በኋላ ማረፍ፤ አፕል መመገብ፤ የማጨስ ፍላጎቶን መቀነስ ይችላሉ” ይላሉ ተመራማሪው፡፡

ተመራማሪው እንደተናገሩት በወተት ውስጥ ያለው የላክስቶስ ይዘት፣ሰው ለማጨስ ያለውን ፍላጎት ለመቀነስ ይረዳዋል ብለዋል፡፡ ብዙዎች በሚያጨሱ ጊዜ ጣፈጭ ነገር ለመውሰድ ይገፋፋሉ ያሉት ተመራማሪው፣ ጣፋጭ ነገር ከመውስድ ይልቅ ወተት መጠጣት ተመራጭ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

Kumneger Media
Kumneger Media
Kumneger Media is a News and Entertainment Website & Channel. Kumneger Media in addition to News and Entertainment it is the hub of Politics, Movies, Drama, Music, Comedy, Documentary and More!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe