የቀድሞ ትዳርን መቀበል

ሁላችንም የትዳር ግንኙነታችን የመጀመርያ ቢሆን እንመርጣለን፡፡ ይህ ግን ለሁሉ አይሳካም፡፡ አንዳንዶች ከመጀመርያ አጋራቸው ጋር እስከ ዕድሜያቸው ፍጻሜ ለመኖር ሲታደሉ ሌሎች በተለያዩ ምክንያቶች ለፍቺ ይዳረጋሉ፡፡ ታዲያ ለትዳ አጋርዎ ከእርስዎ ጋር ያለው ኑሮ የሁለተኛ ትዳር ከሆነ በኑሮዎ እንዳይረበሹና ነገሮችን በቀላሉ መቀበል እንዲችሉ ተከታዮቹን ተግባራት ቢያከናውኑ መልካም ነው፡፡

  1. ስሜቶችዎን ይቆጣጠሩ

በተለያዩ አጋጣሚዎች ከባለቤትዎ አንደበት ስለ ቀድሞ ትዳሩ በሚሰሙበት ጊዜ አይጨነቁ፡፡ የነበረና የቆመ መሆኑን ለራስዎ በመንገር ይረጋጉ፡፡ በተለይ ከቀድሞ ትዳሩ ልጆች ያሉት ከሆነ በተለያዩ አጋጣሚዎች ከባለቤቱ ጋር ሊገናኝ ይችላልና ሁኔታውን በንቃት ከመከታተል ውጪ ትዳርዎ ላይ ችግር የሚፈጥሩ ያልተገቡ ንግግሮች ከመናገር ወይም ለመወሰን ከመቸኮል ይቆጠቡ፡፡ በንግግሮቹ የቅናት ስሜት የሚፈጠርብዎ ከሆነም ዳግም መሰል ንግግሮችን ከእርስዎ ጋር እንያደርግ ይንገሩት፡፡ ይህን የማድረግ ድፍረት ካጡ ንግግሮቹን ሲሰሙ ስሜቶችዎ እንዳይለዋወጡ ራስዎን ያለማምዱት፡፡

  1. በግልጽ ተነጋገሩ

የትዳር አጋርዎ ከቀድሞ የትዳር ጓደኛቸው ጋር ያላቸው ግንኙነት ሙሉ በሙሉ ያበቃ መሆኑን ከራሳቸው አንደበት ጠይቀው ያረጋግጡ፡፡ በእርስዎ በኩልም ሁለተኛ ትዳር ውስጥ ያሉ ከሆነ ስለ ቀድሞ ትዳርዎ በግልጽ ያውሯቸው፡፡

  1. የተዘጋ አጀንዳን አያንሱ

ከትዳር አጋርዎ ጋር በቀድሞ ሕይወታቸው ዙሪያ ተነጋግራችሁ የተግባባችሁባቸው ርዕሠ ጉዳዮች ካሉ በድጋሚ አያንሷቸው፡፡ ይቅርታ የተጠየቀባቸውን ሁኔታዎች መልሶ በማንሳት አጋርዎን መውቀስ ላለፈው ትላንትም ሆነ ለያዙት ዛሬ ከሚሰጠው ጥቅም ይልቅ መጪውን ነገ መጉዳቱ ያመዝናል፡፡ ስለዚህ ትናንትን ሊለውጡት አይችሉምና ለዛሬ ሕይወትዎ ብቻ ትኩረት በመስጠት በግንኙነታችሁ ደስተኛ የሚሆኑበትን መንገድ አመቻቹ፡፡

Kumneger Media
Kumneger Media
Kumneger Media is a News and Entertainment Website & Channel. Kumneger Media in addition to News and Entertainment it is the hub of Politics, Movies, Drama, Music, Comedy, Documentary and More!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe