አቶ ቴዲ ማንጁስ በ80 ሺሕ ብር ዋስትና እንዲፈቱ ታዟል
የፌዴራል ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ የቀድሞ የሶማሌ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ አብዲ መሐመድን ጨምሮ በ47 የክልሉ የተለያዩ የሥራ ኃላፊዎች ላይ ረቡዕ ጥር 22 ቀን 2011 ዓ.ም. ክስ መሠረተ፡፡ ክሱ የተመሠረተው በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አራተኛ ወንጀል ችሎት ነው፡፡
ተከሳሾቹ ከሐምሌ 26 እስከ 30 ቀን 2010 ዓ.ም. ድረስ በክልሉ ጅግጅጋ ከተማን ጨምሮ በተለያዩ ዞኖችና ወረዳዎች በፈጠሩት ግጭት፣ 59 ሰዎች እንዲገደሉ አድርገዋል ሲል ዓቃቤ ሕግ በክሱ አስፍሯል፡፡
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን የእምነት ተቋማት፣ የመንግሥት ተቋማት፣ የግለሰቦች ቤቶችና የተለያዩ የንግድ ተቋማት ተቃጥለው እንዲወድሙ በማድረግ ከ412 ሚሊዮን ብር በላይ ጉዳት ማድረሳቸውን ዓቃቤ ሕግ ገልጿል፡፡
በክልሉ ውስጥ የሚኖሩ ሌሎች ብሔር ብሔረሰቦች ከአካባቢው ተፈናቅለው እንዲሰደዱ ማድረጋቸው በክሱ ተመልክቷል፡፡
ላለፉት አራት ወራት በእስር ላይ የቆዩት አቶ ቴዎድሮስ አዲሱ (ቴዲ ማንጁስ) በ80 ሺሕ ብር ዋስ እንዲለቀቁ ፍርድ ቤቱ ትዕዛዝ ሰጥቷል፡፡