የቤልግሬድ 2022 የዓለም የቤት ውስጥ ሻምፒዮናን ኢትዮጵያ ከአለም አንደኛ በመሆን አጠናቀቀች

የቤልግሬድ 2022 የዓለም የቤት ውስጥ ሻምፒዮናን ኢትዮጵያ ከአለም አንደኛ በመሆን አጠናቀቀች

የቤልግሬድ 2022 የዓለም የቤት ውስጥ ሻምፒዮናን ኢትዮጵያ በ9 ሜዳሊያ ከአለም አንደኛ በመሆን ውድድሩን አጠናቃለች፡፡

ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በተለያዩ የሩጫ ዓይነቶች በሁለቱም ፆታ 4 ወርቅ፣ 3 ብር እና 2 ነሃስ በድምሩ 9 ሜዳሊያዎችን ለሀገራቸው ማምጣት ችለዋል፡፡  በ3000 ሜትር ውድድር ሰለሞን ባረጋ እና ለሜቻ ግርማ ተከታትለው በመግባት የወርቅ እና የብር ሜዳሊያ ለኢትዮጵያ አስገኝተዋል።

በሴቶች ምድብ የተደረገው የ1 ሺህ 500 ሜትር ውድድር ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ከአንድ እስከ ሶስት በመውጣት ድል ተቀዳጅተዋል።

በ 1 ሺህ 500 ሜትር ሴቶች የፍጻሜ ውድድር አትሌት ጉዳፍ ጸጋይ 3 ደቂቃ ከ57 ሰከንድ ከ19 ማይክሮ ሰከንድ በርቀቱ የሻምፒዮናውን ክብረ ወሰን በመስበር አሸንፋለች።

አትሌት አክሱማዊት አምባዬ 4 ደቂቃ ከ2 ሰከንድ ከ29 ማይክሮ ሰከንድ ሁለተኛ ስትወጣ ፤አትሌት ሂሩት መሸሻ 4 ደቂቃ ከ3 ሰከንድ ከ39 ሰከንድ ሶስተኛ ደረጃን ይዛለች።

በ3000 ሜትር ሴቶች በአትሌት ለምለም ኃይሉ አማካኝነት የመጀመሪያውን የወርቅ ሜዳሊያ ያገኘች ሲሆን፤አትሌት እጅጋየሁ ታዬ ሶስተኛ በመውጣት የነሐስ ሜዳሊያ ማግኘቷ የሚታወስ ነው።

ይህ ውጤትም የኢትዮጵያ ከፍተኛው የአለም የቤት ውስጥ ውድድር ውጤት ሆኖ መመዝገቡን የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን አስታውቋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ፣ በሰርቢያ-ቤልግሬድ በተካሄደው በ18ኛው የዓለም የቤት ውስጥ ውድድር ኢትዮጵያ በአንደኝነት ማጠናቀቋን ተከትሎ የተሰማቸውን ደስታ ገልጸዋል።

በቤልግሬድ 2022 የዓለም የቤት ውስጥ ሻምፒዮና አሜሪካ እና ስዊዘርላንድ 2ኛ እና 3ኛ ደረጃን ይዘው አጠናቀዋል፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe