የተማሪዎች ስም መቀየር ኩረጃን እያስፋፋና ትውልድን እየገደለ ነው ተባለ

በምስራቅ ጐጃም ዞን የሞጣ ከፍተኛ ትምህርት መሰናዶ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች የስም ይቀየርልን ጥያያቄ ለሁለት እጁ እነሴ ወረዳ ፍርድ ቤት በማቅረብ ስም የመቀየር ተግባሩ ልክ እንደ መደበኛ ተግባር ሆኖ እየተሰራ ነው፡፡
የሁለት እጁ እነሴ ወረዳ ፍትህ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አህመድ ይብሬ እንደገለፁት የተማሪዎች ስም የመቀየር መብት ህገ መንግስታዊ መብት በመሆኑ አሁን ላይ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ባቀረቡት ጥያቄ መሰረት ፍርድ ቤቱ ስም የመቀየር ስራውን እየሰራ ይገኛል፡፡ ይህን
ስም የመቀየር መብታቸውን መጋፋት አይቻልም ለትምህርት ጥራት ግን እንቅፋት ስለሆነ ትምህርት ቤቱ የራሱን እርምጃ መውሰድና የፈተና ስርዓቱን ማዘመን አለበት ብለዋል፡፡
የሞጣ ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ገዳሙ መኮነን መኮራረጅ ለኮራጅ ተማሪዎች ብቻ ሳይሆን ለጐበዝ ተማሪዎችም እንቅፋት ነው፡፡ተማሪዎች በየአመቱ ከጐበዝ ተማሪዎች ጋር ለመቀመጥ ሲሉ ስም እየቀየሩ ነው፡፡ ለማስቀረት ጥረት ብናደርግም ከመብት
አኳያ ስም የማስቀየር ጉዳይ መቆም እንደሌለበት በተሰጠን አቅጣጫ መሰረት አሁን ላይ ተማሪዎች ስማቸውን እያስቀየሩ ይገኛሉ ብለዋል፡፡
ይህ ደግሞ በፈተና ስርዓቱም በጐበዝ ተማሪዎች ላይም ተፅኖ ስለሚፈጠር ከተማሪዎች እና ጉዳዩ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመነጋገር በአፈታተኑ ስርዓት ላይ እርምጃ እንዲወሰድ እናደርጋለን ብለዋል፡፡ የሞጣ ከተማ ከፍተኛ ትምህርት መሰናዶ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ርዕሰ
መምህር አቶ እውነቴ አዲስ አገራዊ የሆነ የትምህርት ስርዓትን በተመለከተ ለለውጥ ሂደቱ እውነተኛ ሚና መጫዎት የሚቻለው ኩረጃን ማስቀረት ስንችል ነው፡፡ ስም መቀየር ትውልድን እየገደለ ነውና መታየት እንዳለበት ገልጸዋል፡፡ሰም መቀየር ያለበት ፎርም ከተሞላ በኋላ ቢሆን
የተሸለ ነው ብለዋል፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe