የቶኪዮ ኦሎምፒክ ብቸኛው የወርቅ መዳሊስት አትሌት ሰለሞን ባረጋ   መንግሰት የሰጠው ሽልማት እጁ አለመግባቱ አነጋጋሪ ሆነ

ቀደም ሲል ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳና ታማኝ በየነም ተመሳሳይ ሻሻ መሰራታቸው ተዘግቧል፤

በቶኪዮ ኦሎምፒክ በ10ሺ ሜትር ለኢትዮጵያ ብቸኛውን የወርቅ መዳሊያ ያመጣው አትሌት ሰለሞን ባረጋ ከኦሎምፒክ ድል መልስ ቃል የተገቡለት ሽልማቶች ከስምንት ወር በኋላ እስካሁን እጁ አለመግባታቸው አነጋጋሪ ሆኗል፤

በሀገሪቱ ፕሬዚዳን በወ/ሮ ሳህለ ወርቅ ዘውዴ ከቶኪዮ መልስ ዘመናዊ የቤት መኪና የተሸለመው አትሌቱ እስከዛሬ ድረስ ሽልማቱን እንዳልተሰጠው ታውቋል፤

ሰለሞን ላመጣው ብቸኛ የወርቅ መዳሊያ ከዘመናዊ መኪና በተጨማሪ የደቡብ ክልል ወልቂጤ ከተማ ላይ የሸለመው 10 ሺህ ካ.ሜ. መሬት እስከዛሬ ድረስ እንዳልተሰጠው ተረጋግጧል፤

በወቅቱ አትሌቱ ከመኪና ጋር ፎቶ እንዲነሳ ተደርጎ የነበረ ሲሆን መሬቱም “በፍጥነት” እጁ እንደሚገባ ተገልፆ ነበር።

ስለ ሽልማቶቹ የተጠየቀው አትሌት ሰለሞን  : “የሽልማት መኪናውን የሚያስመጣው ሞኤንኮ እንደነበር ተነግሮኝ ነበር። ይሁንና ከውጭ ምንዛሬ እጥረት ጋር ተያይዞ ድርጅቱ ይህን ማግኘት አልቻለም። አሁን ግን በራሴ ውጭ ምንዛሬ ሌላ አይነት ምርጫዬ የሆነ መኪና ከቀረጥ ነፃ ሆኖ እንዲገባልኝ ለገንዘብ ሚኒስቴር ደብዳቤ አስገብቻለሁ። አሁን እሱን እየተጠባበቅኩ እገኛለሁ።”  ሲል ለኢትዮጵያ ቼክ ተናግሯል፤

በመሬቱ ዙርያም ሲናገር: “በደቡብ ክልል የስፖርት ኮሚሽን የአመራሮች ለውጥ ነበር። መሬቱን በዚህ ሳምንት እንደሚያስረክቡኝ ነግረውኛል። ስራ ስለሚበዛብኝ የመሬቱን ጉዳይ እኔ በግሌ መከታተል አልቻልኩም ነበር፣› ብሏል፤

ለታዋቂ ሰዎች ከዚህ በፊት መኪና መሸለማቸው በህዝብ ፊት ከተገለፀና በመገናኛ ብዙሃን አማካይነት ለህዝብ ከተነገረ በኋላ ሽማልቶቹ የውሃ ሽታ ሆነው የቀሩበት አጋጣሚ እንዳለ የተዘገበ ሲሆን የቀድሞው የኢትዮጵያ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ ለመውጡ ዋዜማ ዘመናዊ ኒሳን መኪና በኦሆዴድ መሸለማቸው ቢገለፅም ሽልማቱን ሳይሰጣቸው ነው ከዚህ አለም በሞት የተለዩት፤

አርቲስትና አክቲቪስት ታማኝ በየነም በለውጡ ማግስት ከ21 ዓመታት የስደት ኑሮ በኋላ ወደ ሀገሩ ሲገባ የአማራ ክልል ባለሃብቶች ዘመናዊ መኪና እንደሸለሙት ቁልፍ ሰጥተውት ፎቶግራፍ እንዲነሳ ካደረጉ በኋላ ሻሻ እንደተሰራ መዘገቡ ይታወሳል፤

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe