የአሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ጄፍሪ ፌልትማን ወደ ኢትዮጵያ ሊመጡ መሆኑ ተሰምቷል

ልዩ መልዕክተኛው ጄፍሪ ፌልትማን ከከፍተኛ ባለስልጣናት ጋር እንደሚወያዩ ተጠቅሷል።

ጄፍሪ ፌልትማን ከኢትዮጵያ በተጨማሪም በጅቡቲ እና በተባበሩት አረብ ኢሚሬቶች ጉብኝት ያደርጋሉ

የአሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ጄፍሪ ፌልትማን ወደ ኢትዮጵያ እንደሚጓዙ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።

ልዩ መልዕክተኛ ጄፍሪ ፌልትማን ከኢትዮጵያ በተጨማሪም በጅቡቲ እና በተባበሩት አረብ ኢሚሬቶች ጉብኝት እንደሚያደርጉም ተገልጿል።

ጄፍሪ ፌልትማን ከመጪው እሁድ ሐምሌ 9 ጀምሮ እስከ ሐምሌ 18 ቀን በሶሱቱ ሀገራት ጉብኝት የሚያደርጉ መሆኑንም ነው አል ዐይን ከአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርያገኘው መግለጫ የሚያመለክተው።

ልዩ መልዕክተኛ ጄፍሪ ፌልትማን በሶስቱ ሀገራት ለዘጠኝ ቀናት ያክል በሚያደርጉት ቆይታም ከሀገራቱ ከፍተኛ ባለስልጣናት ጋር እንደሚወያዩ ተጠቅሷል።

ውይይቱም በአፍሪካ ቀንድ ሰላም፣ መረጋጋት እና ብልጽግናን ማምጣት በሚያስችሉ ዕድሎች የተመለከተ እንደሚሆንም ሚኒስቴሩ አስታውቋል።

የአሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ጄፍሪ ፌልትማን ከዚህ ቀደምም በግንቦት ወር ላይ ኢትዮጵያን ጨምሮ በግብፅ፣በኤርትራ እና በሱዳን ጉብኝት አድርገው እንደነበረ ይታወሳል።

በኢትዮጵያ በነበራቸው ቆይታም ከምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ጋር ተገናኝተው የነበረ ሲሆን፤ በህዳሴ ግድብ፣ በኢትዮ-ሱዳን የድንበር ጉዳይ፣ በትግራይ ክልል ወቅታዊ ሁኔታዎች እንዲሁም በ6ኛው ብሔራዊ ምርጫ ላይ ያተኮረ ውይይት አድርገውም ነበረ።

አሜሪካ ኢትዮጵያን ጨምሮ በአፍሪካ ቀንድ ላይ ትኩረት የሚያደርጉ አዲስ ልዩ መልዕክተኛ ጄፍሪ ፌልትማንን ባሳለፍነው ሚያዚያ ወር ላይ መሾሟ ይታወሳል።

አዲሱ የኃላፊነት ስፍራ በፕሬዚዳንት ጆ ባይደን የተፈጠረ ሲሆን፤ በኢትዮጵያ ትግራይ ክልል ያለውን ቀውስ እንዲሁም በታላቁ የሕዳሴ ግድብ ዙሪያ በኢትዮጵያ፣ ሱዳን እና ግብፅ መካከል ያለውን አለመግባባት በቅርበት ለመከታተል ያለመ ነው።

Kumneger Media
Kumneger Media
Kumneger Media is a News and Entertainment Website & Channel. Kumneger Media in addition to News and Entertainment it is the hub of Politics, Movies, Drama, Music, Comedy, Documentary and More!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe