የአርቲስቶቻችን ተስፋና ስጋት?

የሙዚቃ አልበም ወደ ዲጂታል  አለም

ከ300 ሚሊዮን ብር በላይ የሆነ ካፒታል ይዞ የዛሬ ሁለት ዓመት ተኩል ስራ የጀመረው ሰዋሰው መልቲ ሚዲያ የተቀዛቀዘውንና በኮፒ ራይት ሳቢያ የመብት ጥሰት የሚፈፀምበትን ሙያተኛና ተገቢ የሆነ ገቢ ማግኘት ላልቻሉ ሙዚቀኞች ተስፋ የሚያሳድር አሰራር ይዠ መጥቻለሁ እያለ ነው፤ጠቀም ያለ ክፍያ በመክፈል አዳዲስ የሙዚቃ ስራዎችን ለአድማጮች የማቅረብ እቅድ አለው፤ የራሱን መተግበሪያና ድረገፅ አዘጋጅቶ የሙዚቃ ስራዎችን ወደ ዲጂታል ዓለም በማሸጋገር በአሁኑ ወቅት ለአድማጭ እያቀረበ የሚገኘው ሰዋሰው በፈጠራ ስራ ላይ የራሳቸው ተሰጥኦና ችሎታ ያላቸውን ባለሙያዎች የልፋታቸውን ዋጋ በጥሩ ክፍያ ስራዎቻቸውን ለአድማጭና ተመልካች ያቀርባል፤ ካሴትና ሲዲ ታሪክ እየሆኑ ነው፡፡

የሰዋሰው መልቲ ሚዲያ የሙዚቃ ዲፓርትመት ሀላፊ የሆነው ወጣቱ የሙዚቃ ባለሙያ ሀብቱ ነጋሽ ሰዋሰው  ኢትዮጵያ አዲስ የሙዚቃ አብዮት ሊያመጣ የሚችል አሰራሮች ይዞ መምጣቱን ይናገራል፤ ሰዋሰው የሙዚቃ ስራዎችን ሲገዛ ሁለት አይነት አሰራሮችን እንከተላለን የሚለው ሀብቱ ታዋቂና የራሳቸውን ስራ ራሳቸው ወጪውን ችለው ሙሉ አልበም የሚሰሩ ድምጻውያንን ወይም የሚቀርብበት መንገድ አንዱ ሲሆን ሌላው ይህ አቅም የሌላቸው ነገር ግን የሙዚቃው ተሰጥኦና ችሎታው ያላቸውን ወጣት ድምጻውያን ከባለሙያ ጋር በማገናኘትና የግጥምንና ዜማ እንዲሁም ሌሎች ወጪዎችን በመሸፈን ሙሉ አልበም የሚሰሩበትን መንገድ እናመቻቸን ይላል፤

በዚህ መልኩ ከ70 በላይ ታዋቂና ወጣት ድምጻውያን ጋር ውል ፈፅመናል የሚለው ሀብቱ ከአስቴር አወቀ ጀምሮ ቴዲ አፍሮ፤ ፀደንያ ገ/ማርቆስ፤ፀጋዬ እሸቱ፤ አብነት አጎናፍር፤ግርማ ተፈራ ፤ ዘሩባቤል ሞላ፤ ጌቱ ኦማሂሬ፤ቴዎድሮስ ሞሲሳ፤ሄኖክ አበበ፤ ራሄል ጌቱ፤ ብሌን ዮሴፍ፤ ለምለም ኃ/ሚካኤል፤ ጠረፍ ካሳሁን፤ ወዘተ አልበሞቻቸው ለመስራት ውል መፈፀማቸው ተሰምቷል፤

የአዳዲስም ሆኑ የነባር ድምጻውያን የሙዚቃ ስራ በአብአዛኛውን በትብብር ፕሮውዲው እየተደረጉ ያሉት ከሙዚቃ አቀናባሪዎች ጋር በመሆኑም በሀገራች አሉ የተባሉ የሙዚቃ አቀናባሪዎችም የራሳቸውን ድምጻዊ ይዘው ግጥምና ዜማ ገዝተው አልበም ፕሮውዲስ ካደረጉ ሰዋሰው ጠቀም ባለ ክፍያ በመግዛት ለአድማጭ ያደርሳል፤ በዚህም መሰረት ከእነ ካሙዙ ካሳና አቤል ጳውሎስ፤ ታምሩ አለሙ፤ናትናኤል ግርማቸው፤ ከመሳሰሉ ታዋቂ አቀናባሪዎች ጋር ውል ይዟል፤ሰዋሰው፤ ከሙዚቃ አሳታሚ መጥፋት ጋር በተያያዘ ብዙ አርቲስቶች የሰሩትን ሙዚቃ ይዘው በየቤታው ተቀምጠዋል፤ አንዳንዶቹ ከዓመታት በፊት የሰሩትን ሙዚቃ በነጠላ ዜማ መልክ ለአድማጭች ለማቅረብ ሲገደዱ ሌሎች ደግሞች ፊታቸውን በፊልምና በሌሎች የጥብብ ስራዎች ላይ ከማድረግ ባለፈ ዓመት እየጠበቁ የቀድሞ ዘፈኖቻቸውን ለማደግ ተገደዋል፤ ሰዋሰው የሙዚቃ ባለሙያዎችንና ሙያውን በተሻለ አሰራር ለአድማጭ ሲያቀርብ ሙሉ አልበም ለሰሩ ወይም ከአራት ወይም ከአምስት በላይ ዘፈኖችን ለሰሩ ሙያተኞች ቅድሚያ የሚሰጥ ሲሆን ነጠላ ዜማዎችን አናበረታታም ፤ ሙያተኞችንም አቅም ለማሳየት አንድ ዜማ በቂ አይደለም ይላል፤

Ato Habtu Negash

ከእያንዳንዱ ድምጻዊ ጋር የሚደረገው ስምምነት እንደ አርቲስቱ ይለያያል፤ አርቲስቶች ከአልበማቸው ጋር አንድ የሙዚቃ ኮንሰርት እንዲሰሩ ስምምነት የሚያደርጉ ሲሆን ከአልበሙ ላይ ሶስት ዘፈኖችን ክሊፕ መስራት እንደ አንድ መስፈርት ተቀምጧል፤ የክሊፑን ወጪ በሰዋሰው አልያም በአርቲስቱ የሚሸፈን ሲሆን በሰዋሰው የዩቲዩብ ቻናል ላይ ብቻ የሚጫን ነው የሚሆነው፤

የ አ ር ቲ ስ ቶ ቻ ች ን ተስፋና ስጋት/ የቅጂ መብት ጉዳይ

አርቲስቶች አልበማቸው ለሰዋሰው አንዴ ከሸጡ በኋላ ቢያንስ ለአምስት ዓመታት ከገቢው ላይ መብት መጠየቅ አይችሉም፤ ሙሉ ወጪውን ሸፍኖ የገዛ በመሆኑ አርቲስቶቹ በራሳቸው የዩቲዩብ ቻና ላይም ሆነ የሮያሊቲ ክፍያ በሚሰበሰብበት የብሮድካስት ሚዲያ ላይ ስራዎቻቸውን አሳልፈው የመስጠት መብት አይኖራቸውም፤ ሰዋሰው የሙዚቀኞቹን ስራ አድማጭ ጋር ለማድረግ የማስተዋወቅ ስራውን ሙሉ ሀላፊነት ወስዶ የሚሰራ ሲሆን ከቅጂና ተዛማጅ መብቶች ጥበቃ ጋር ተያያዞ በኢትዮጵያ ሙዚቀኞች ማህበር አማካይነት የሚሰበሰበው የሮያሊቲ ክፍያ አዋጁ ለፕሮውዲውሰሩ የሚፈቅደውን መብት ጨምሮ ለ5 ዓመታት ማስተዳደር የሰዋሰው መብት ይሆናል ነው የሚለው ሀብቱ፤ ያም ሆኖ ሙያተኞች እስከ ወራሾች ድረስ ሊያስተላለፉት የሚችሉትን የሮያሊቲ መብት በሽያጭ የማስተላለፋቸው ስምምነት አሁንም ድረስ ጥያቄ ይነሳበታል ይላሉ፤አንዳንድ ውል ያልፈፀሙ አርቲስቶች፤በአንድ ጊዜ ክፍያ የፈጠራ ስራዎቻቸውን አሳልፈው መስጠታቸው የሞራል ጥያቄ ያስነሳል ፤

ለመሆኑ የውጭው ዓለም የሮያሊቲ ክፍያ ልምድ ምን ያሳያል?

የኪነጥበብ ባለሙያዎችን የፈጠራ ሥራ በሽያጭ ከተላለፈ በኋላ መዝግቦ በመያዝ ለሙያተኞች ተገቢ የሆነ ክፍያ በማበጀት በር ከፋች ተደርጋ የምትወስደው አሜሪካ ነች፡፡ በ18ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ማብቂያ ጀምሮ እያደገ የመጣውን የፖፑላር ሙዚቃ ኢንዱስትሪ ፈር ለማስያዝ … የተለያዩ ህጎችን በማውጣት ትታወቃለች፡፡ በአሜሪካ የመጀመሪያ የፌዴራል መንግስት የኮፒራይት copy right Act of 1790 የተባለው የረቀቀና የፀደቀው እ.ኤ.አ በ1790 ነው፡፡

ከዚህ ጊዜ በኋላም  በአሜሪካ ጃዝ ሙዚቃ ራሱን ከቤተክርስቲያን መዝሙር በመለየት የተሻለ ተደማጭ መሆን ችሏል፡፡ የአሜሪካ የኮፒራይት ህግ  በየጊዜው እየተቀያየሩ ከሚወጡት የቴክኖሎጂ ውጤቶች አንፃር የመብት ጥበቃ እየተሻሻለ የሄደ ሲሆን በዋናነት የኮፒራይትና ሮያሊቲ ክፍያው የሚመለከታቸው ወገኖች በግልጽ ተለይተው የተቀመጡበት ነው፡፡

የሙዚቃ ደራሲያን ሮያሊቲ ማንኛውም የሙዚቃ ስራ ከተቀረፀና በሽያጭ ከቀረበ በኋላ ለአድማጭ ወይም ለተመልካች በመድረክ ሲቀርብ ወይም በመገናኛ ብዙሃን አማካይነት ሲሰራጭ ክፍያ ለባለቤቶቹ ይከፈላል፡፡ በዚህ ረገድ ዘፈኑን በተለያየ መልኩ የሚጠቀሙ ወገኖች ይኖራሉ፡ ፡ የመጀመሪዎቹ ዘፈኑን መድረክ ላይ ደግመው የሚጫወቱ ሲሆኑ የመድረክ ክፍያ (performing right) መክፈል ይጠበቅባቸዋል- በተጫወቱት ቁጥር፡፡

ይህም የመጀመሪያዎቹን የስራውን ሀሳብ አመንጪዎች በገቢ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ያደርጋል፤ ለዚሁም ተብሎ ከመድረክ ላይ የሚጫወቱ ሰዎችንና ኮንሰርት የሚያዘጋጁ ድርጅቶችን የሚቆጣጠር የመድረክ ክወና ማህበር (the performing Right Society) የሚባል ማህበር አላቸው፡፡ ማህበሩ ከየኮንሰርቶቹ ላይ ለሚቀርቡ ዘፈኖች ፈቃድ በመስጠት ለቀረበው ዘፈን ክፍያ በመሰብሰብ ለሚመለከታቸው ባለቤቶች ክፍያ ይፈፅማል፡፡ ማህበሩ በዋናነት ከሚከታተላቸው የመድረክ ስራ ማቅረቢያ ቦታዎች መካከል የሙዚቃ አዳራሾች፣ የምሽት ክለቦች፣ ሲኒማ ቤቶች፣ ስታዲየሞች ማንኛውም የመድረክ ሥራ የሚቀርብባቸውን ቦታዎች ይከታተላሉ፡፡

የሬዲዮና የቴሌቪዢን ጣቢያዎችም በቀጥታ የሙዚቃ ስርጭት በሚያቀርቡበት ወቅት ለማህበሩ የመክፈል ግዴታ አለባቸው፡፡ ማህበሩ አስቀድመው የኮንሰርቱ አዘጋጆች ለመጫወት ፈቃድ የጠየቀባቸውን ሙዚቃ ዝርዝር መሰረት ማቅረባቸውን የቀረፃ መብት ጥበቃ ማህበር (The Mechanical Copy right Protection Socity) ነው፡፡

ይህ ማህበር አንድን ወጥ የሙዚቃ ስራ በተለያዩ መንገዶች በማባዛት ለህብረተሰቡ ከሚያደርሱ ድርጅቶች ላይ ተሰብስቦ ለአሳታሚዎች የሚከፋፈል ነው፡፡ይህ የፈጠራ ስራዎችም የመጠቀም መብት ተግባራዊ ለማድረግ የቴክኖሎጂው በየጊዜው መቀያየር አፈፃፀሙን አስቸጋሪና ውስብስብ አድርጎታል፡፡ በተለይም የሶፍትዌሮች መበራከትና ለቁጥጥር እጅግ አስቸጋሪ ሆነው መውጣት ጋር በተያያዘ ብዙ የአውሮፓ ሀገራት የአርቲስቶቻቸው ዘፈኖች መብት ለማስጠበቅ እየተቸገሩ እንደሆነ ይታያል፡፡

በተለያዩ ድረገፆች ላይ ሙዚቃዎችን የሚሞሉና ለአድማጭ ኮፒ እንዲያደርገው ሁሉ የሚፈቅድ የኢንተርኔት መረቦች የቁጥጥር ስራውን ፈታኝ አድርጎታል፡፡ እንግሊዝ ከዛሬ 10 ዓመት በፊት ከድረ ገፆች ጋር በተያያዘ የሚፈፀሙ የመብት ጥሰቶችን ለመቆጣጠር European copyright Directive የተሰኘ ማንዋል ያፀደቀች ቢሆንም አሁንም ድረስ በተለይ በእጅ ስልኮች ላይ የተለያዩ ሙዚቃዎችን ከማባዛት ማቆም አልተቻለም፡፡ ይሄ የቴክኖሎጂ ውስብስብነት በአፍሪካም ለቁጥጥር አስቸጋሪ መሆኑ እየታየ ነው፡፡ ሁኔታው የአርቲስቶችን ስራዎች ሙሉ

ክፍያ ከፍለው ፕሮውዲስ ላደረጉ አሳታሚዎችና ግዢ ፈፅመው ለአድማጭ ተመልካች ላቀረቡ የዩቲብ ቻናል ፕሮዲውሰሮችም አስቸጋሪ እየሆነ የመጣ ሲሆን ዘመኑንና ቴክኖሎጂውን የዋጀ አሰራር እስካልመጣ ድረስ ብዙ ተደክሞባቸው የሚሰሩ የሙዚቃ ስራዎች አትራፊ የመሆናቸው ጉዳይ ጥያቄ ውስጥ ከገባ ሰነባብቷል፤

ሙዚቃና ሚደያዎቻችን

አልበሞች ለህዝብ ሲቀርቡ እንደከዚህ ቀደሙ ሚዲያዎች ከገበያ ላይ ገዝተው ለህዝብ የማሰማት አሰራር ላይ ገደብ ሊኖር ይችላል፤ ሰዋሰው እንደሚለው ሙሉ የማስታወቂያ ስራዎች ስለሚሰሩ ራዲዮና ቴሌቪዥን ጣቢያዎችም እንደማንኛውም ደንበኛ የደንበኝነት ክፍያ ከፍለው አዳዲስ ስራዎችን ለአድማጭ ተመልካች የሚያቀርቡ ነው የሚሆነው፤ እርግጥ በተወሰነ ስምምነት የተወሰኑ ዘፈኖችን በነፃ መጠቀም የሚችሉበት አሰራርም ከሬዲዮ ወይም ከቴሌቪዢን ላይ በመቅዳት ይከታተላቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘ የፊልምና የቪዲዮ ካምፓኒዎችም ዘፈኖችን በፊልማቸው ውስጥ መጠቀም ከፈለጉ ከማህበሩ ፈቃድ የማግኘት ግዴታ ተጥሎባቸዋል፡፡ ይህ በፊልም ውስጥ የሙዚቃ ሥራን የማቅረብ መብት የጥምረት መብት (Synchronisation right) ተብሎ ይታወቃል፡፡

ሁለተኛው የመብት አይነት የቀረፃ መብትን (Mechanical right) ይባላል፡ ፡ ምንግዜም ሙዚቃ ተደማጭ ሊሆን የሚችለው በቀረፃ ባለሙያዎች አማካይነት ተገቢውን ጥራት ጠብቆ ሲቀርብ በመሆኑ ይህንኑ ሥራ በሚሰሩና በማብዛት ሙያ ላይ ከተሰማሩ ሰዎች የሚሰበሰብ ክፍያ አለ፡፡ ይህንን ክፍያ የሚሰበስበው ደግሞ ይኖራል ነው የሚለው ሀብቱ፤ በአሁኑ ወቅት የተለያዩ ድምጻውያን ስራዎች የተጫኑበትን መተግበሪያ ከአፕ ስቶርና ከፕሌይ ስቶር ላይ በማውረድ ደንበኞች በነጻ ሙዚቃዎችን እንዲያዳምጡ የሙከራ ጊዜ መጀመሩን የሚገልፀው ሀብቱ ከተወሰኑ ጊዜያት በኋላ ግን አዳዲስ አልበሞችን ስናወጣ ደንበኞች በቋሚ ደንበኝነት ወይም በአንድ ጊዜ ክፍያ ሙዚቃዎችን ማግኘት የሚችሉበት አሰራር ይጀመራል ይላል፤ ክፍያውን በቴሌ ብር አልያም በእናት ባንክ በኩል መፈፀም እንደሚቻልና እናት ባንክ የዚህ ፕሮጀክት አጋር ነው ፤የውጭ ሀገር አድማጮች በውጭ ምንዛሪ መክፈልየሚችሉበት አሰራርም ተዘርጋቷል፤ የደንበኞችን ክፍያ ከወዲሁ ይህን ያህል ነው ተብሎ የተወሰነ ባይሆንም በወር ከሁለት ማኪያቶ ዋጋ በታች ይሆናል የሚል እቅድ ተይዟል ይላል ሀብቱ፤ በወር ቢያንስ ስድስት አልበሞችን ለአድማጭ ለማቅረብ እቅድ የተያዘ ሲሆን የሙዚቃ አድማጩ በርካታ አማራጮች ይኖራቸዋል ተብሎ ይታሰባል፤

አዳዲስ አልበሞች ከዚህ በፊት በሲዲ ወይም በካሴት ሲወጣ ስለዘፋኙና ስለ ስራዎቹ ዝርዝር መረጃዎች ከሲዲው ጋር አብሮ ተዘጋጅቶ ለገበያ ይወርብ ነበር፤ አሁንስ ? ሀብቱ እንደሚለው አዳዲስ አልበሞች ሲወጡ በመተግበሪያው ላይ ከዚህ በፊት የነበሩ ስለ ስራዎችና ስለ አርቲስቱ የሚገልጹ መረጃዎች አብረው የሚቀርቡ ሲሆን ማንም ሰው ያንን መረጃ ድረ ገፁ ላይና በመተግበሪያው ላይ ማግኘት ይችላል፤ ከዚህ በተጨማሪዎች አርቲስቱ ከ3 እስከ 5 ደቂቃ የሚሆን መረጃ ተቀርጾ አብሮ የሚለቀቅ ይሆናል፤

ሙዚቃውን ማን ይመርጣል?

ሰዋሰው መልቲ ሚዲያ ወደ ዚህ ስራ ሲገባ ከሙዚቃ ባለሙያዎች ጋር በጥምረት እንደሚሰራ ይገልፃል፤ የተለያዩ ሙዚቃ የሚያውቁ ሙዚቃ አቀናባሪዎችና አርቲስቶች እንዲሁም ፕሮውዲውሰሮች ዘፈኖችን እንደሚያዳምጡና እንደሚመርጡ ይናገራል፤በተለይም በልዩ ልዩ ቋንቋዎች የሚዜሙ ዘፈኖችን በተመለከተ ቋንቋውን የሚያውቁ ሙያተኞች መዘጋጀታቸው ታውቋል፤

ለሙያተኞች እንደስራቸው ነው ክፍያ የምንፈፅመው የሚለው ሀብቱ ትንሹ ክፍያ አንድ ሚሊየን ብር ነው፤ የሙዚቃ ስራ በገንዘብ የሚተመን ባይሆንም በተወሰነ ደረጃ ተጠቃሚ ሊያደርጋቸው የሚችል ክፍያ እንከፍላለን ይላል፤ ከፍተኛው ክፍያ ግን በአርቲስቶቹ እንጂ በእኛ በኩል ይፋ አይሆንም ሲል ያክላል፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe