“የኢትዮጵያን አቋም በዓለም መድረክ በወጉ አንጸባርቀዋል” በሚል እየተወደሱ የሚገኙት ኢ/ር ስ ለሺ በቀለ ማን ናቸው?

ትናንት በጸጥታው ምክር ቤት ኢትዮጵያ በዓባይ ላይ በመገንባት ላይ ያለችውን ግድብ እና የድርድር ሂደቱን በተመለከተ ብዙዎች ያደነቁትን ማብራሪያ ሰጥተዋል

ኢ/ር ስለሺ በቀለ የኢትዮጵያን የውሃ ጉዳዮች “በእውቀት እየመሩ ነው” በሚልም ጥቂት በማይባሉ ኢትዮጵያውያን ይወደሳሉ።

የኢትዮጵያን የውሃ ጉዳዮች “በእውቀት እየመሩ ነው” የሚባልላቸው የውሃ፣ መስኖ እና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ኢ/ር ስለሺ በቀለ (ዶ/ር) ከታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ጉዳይ ጋር በተያያዘ ቀድመው ከሚጠቀሱ ሰዎች መካከል አንዱ ናቸው፡፡

ኢትዮጵያ በአባይ ወንዝ ላይ ያላትን ጥቅም ለማስጠበቅ ከሚታተሩ ኢትዮጵያውያን መካከልም አንዱ ናቸው፡፡

ኢ/ር ስለሺ በቀድሞው ጠ/ሚ ኃይለማርያም ደሳለኝ በውሃ፣ መስኖ እና ኢነርጂ ሚኒስትርነት ከተሾሙበት ከ2009 ዓ/ም ጀምሮም ኢትዮጵያ ያሏትን ያልተነኩ የውሃ ሃብቶች አልምታ እንድትጠቀም ለማድረግ ብዙ ሰርተዋል፣ መርተዋል፡፡ አሁንም እየሰሩ፤ እየመሩም ይገኛሉ፡፡

ኢትዮጵያ በራሷ ሉዓላዊ ግዛትና ውሃ ላይ የምትገነባው ግድብ በታሰበለት ዓላማ እና ግብ ልክ፤ በአሳሪና አስገዳጅ ስምምነቶች ሳይታሰር እንዲጠናቀቅ ለማድረግም ከሌሎች የዘርፉ ሙያተኞችና ባልደረቦቻቸው ጋር በመሆን በመትጋት ላይ ናቸው፡፡

ላለፉት 30 ዓመታት በአመራር፣ ምርምር፣ ማስተማር እና ማማከር የዳበረ ልምድን ስለማካበታቸው የሚነገርላቸው ኢ/ርስለሺ በሚሰጡት እውቀት አገዝ አመራርም በብዙዎች ዘንድ ይወደሳሉ፡፡

የካበተ የውሃ ዘርፍ ልምድን ያዳበሩት ኢ/ር ስለሺ በሚኒስትርነት ከተሾሙበት ከጥቅምት 2009 ዓ.ም አንስቶ ኢትዮጵያ በዓባይ ውሃ ሊኖራት የሚገባትን ጥቅም ለማስጠበቅ ብዙ መታተራቸው ይነገራል፡፡

የግብጽን ኢ-ፍትሀዊ አካሄድ በሶስትዮሽ፣አህጉር አቀፍና ዓለም አቀፍ መድረኮች የሞገቱና እየሞገቱ ያሉ መሪ ናቸው በሚል ብዙዎች ሲናገሩላቸውም ይደመጣሉ፡፡

ኢ/ር ስለሺ ከሰሞኑ አሜሪካ ኒውዮርክ ናቸው፡፡ ኒውዮርክ የመሆናቸው ሚስጥር ደግሞ ግድቡን በተመለከተ የኢትዮጵያን አቋም ለጸጥታው ምክር ቤት በወጉ ለማስረዳትና ለማንጸባረቅ ነው፡፡

ይህንንም ለዛሬ አጥቢያ ሌሊቱን በነበረው የምክር ቤቱ ስብሰባ ላይ አድርገው አሳይተዋል፡፡

ይህን ተከትሎም “ግብጽ እና ሱዳን በምክር ቤቱ በኩል ለማሳካት አቅደው የነበሩትን ሴራ በማክሸፍ የኢትዮጵያን አቋም በዓለም መድረክ ያንጸባረቁ ድንቅ መሪ” የሚል አድናቆት ከብዙሃኑ ኢትዮጵያውያን እየጎረፈላቸው ይገኛል፡፡

Kumneger Media
Kumneger Media
Kumneger Media is a News and Entertainment Website & Channel. Kumneger Media in addition to News and Entertainment it is the hub of Politics, Movies, Drama, Music, Comedy, Documentary and More!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe