የኢትዮጵያ መንግሥት ከሕወሃት ጋር የገባበትን ግጭት ለማቆም ለሁለተኛ ጊዜ የተናጥል ተኩስ አቁም ማወጁን አስታወቀ፤

የኢትዮጵያ መንግሥት ከትግራዩ ሕወሃት ጋር የገባበትን ግጭት በማቆም ከዛሬ ጀምሮ ለሁለተኛ ጊዜ የተናጥል ተኩስ አቁም ማወጁን አስታወቀ፤

የመንግሥትኮሚዩኒኬሽን አገልግሎት ጽሕፈት ቤት ዛሬ ባወጣው መግለጫ  በርካታ የትግራይ ክልል ነዋሪዎች የምግብ ዕርዳታ ፍለጋ ወደ አጎራባች ክልሎች እየተፈናቀሉ መሆኑን የጠቀሰው መንግሥት፣ ሕዝቡ ከክልሉ ሳይወጣ ሰብዓዊ ዕርዳታ እንዲያገኝ ለማስቻል እና የዜጎችን ሕይወት ለመታደግ ሲል ግጭት  ማቆሙን ገልጧል።

በአሁኑ ወቅት በሺዎች የሚቆጠሩ የትግራይ ክልል ነዋሪዎች የሰብዓዊ እርዳታን ፍለጋ ወደአጎራባች ክልሎች እየተጓዙ መሆኑ እየተስተዋለ ነው ያለው መግለጫው በዚህም በትግራይ አጎራባች ክልሎች የሚኖሩ ዜጎች ከትግራይ ክልል የሚመጡ የሰብዓዊ እርዳታ ፈላጊ ዜጎችን ተቀብሎ በማስተናገድ እያሳዩ ያለው በጎ ተግባር በህዝቦች መካከል ያለውን የወንድማማችነት እና የአንድነት መንፈስ የሚያሳይ ነው ብሏል።

መንግስት እነዚህ ዜጎች የሰብዓዊ እርዳታው ከቀያቸው ሳፈናቀሉ ባሉበት እንዲርሳቸው ቢደረግ እንግልታቸውን እንድሚቀንስ በማመን የአስቸኳይ የሰብዓዊ አቅርቦቶችን ወደትግራይ ክልል በበቂ ሁኔታ መድረስ የሚችሉበትን ሁኔታ ለማሳካት የተቻለውን ሁሉ ጥረቶች ለማድረግ ቁርጠኛ መሆኑን አብራርቷል።

በዚህም መሠረት በከፍተኛ ችግር ውስጥ የሚገኙ ዜጎችን ህይወት ለመታደግ እና የዜጎችን እንግልት ለመቀነስ ይቻል ዘንድ ከተለመደው የተለዩ እርምጃዎችን መውሰድ አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ መንግስት ይህ ውሳኔ ከወጣበት ሰዓት ጀምሮ ተግባራዊ የሚደረግ ለሰብዓዊነት ሲባል ግጭት የማቆም ውሳኔ አስተላልፏል።

በዚህ አጋጣሚ መንግስት ዓለም ዓቀፉ የለጋሾች ማህበረሰብ እያቀረበ ያለውን ድጋፍ እና እርዳታ በከፍተኛ መጠን እንዲጨምር ጥሪ ያቀረባል ያለው መግለጫው የሰብዓዊ እርዳታ ለሚያስፈልጋቸው ዜጎች የሰብዓዊ ድጋፍ አቅርቦቱ በተሳለጠ ሁኔታ መድረስ እንዲችል ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ተባብሮ ለመስራት ያለውን ቁርጠኝነት በድጋሚ ያረጋግጣል ብሏል።

ይህ የመንግስት ጥረት እና ቁርጠኝነት የሰብዓዊ ሁኔታውን በማሻሻል ረገድ የሚኖረው ስኬት የሚረጋገጠው በሌላኛው ወገን የሚገኘው አካል በተመሳሳይ ለዚህ አላማ በሚኖረው ቁርጠኝነት ልክ መሆኑን መበመጥቀስ ለሰብኣዊነት ግጭት የማቆም ውሳኔ የተፈለገውን ውጤት ማምጣት እንዲችል መንግስት በትግራይ ክልል የሚገኙ አማጺያን ከማንኛውም የጥቃት እንቅስቃሴ እንዲታቀቡ እና  በጉልበት ከያዟቸው የአጎራባች ክልል አካባቢዎችእንዲወጡ ጠይቋል።

የህወሃት ሀይሎች በአፋር ክልል ብቻ አራት ወረዳዎችን እንዲሁም በአማራ ክልል ስድስት ወረዳዎችን መቆጣጠራቸውን መንግስት ቀደም ሲል ባወጣው መግለጫ ያስታወቀ ሲሆን የህወሃት ሀይሎች በበኩላቸው ምዕራባዊ  ትግራይ በሀይል ተይዞብኛል ማለቱ ይታወሳል፤

የአሜሪካ የምስራቅ አፍሪካ ልዩ ልዑክ አምባሳደር አአአ ሰሞኑን ወደ አዲስ አበባ መጥተው ከውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አቶ ደመቀ መኮንን ጋር የተወያዩ ሲሆን ይህ የመንግስት ውሳኔ ከአምባሳደሩ መጥተው መመለስ በኋላ የተወሰደ ስለመሆኑ ይነገራል፤

መንግስት ቀደም ሲል የትግራይ ሀይሎችን‹ አሸባሪ›  ሲል ይጠራቸው የነበረ ሲሆን አሁን በዚህ መግለጫው ላይ  “በትግራይ የሚገኙ አማጺያን” ወደሚል መቀየሩ አነጋጋሪ ሆኗል፤

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe