የኢትዮጵያ አየር መንገድ  ለበረራ አስተናጋጆች ለመስጠት የወሰነው  የቋንቋ ፈተና ተቃውሞ ገጠመው

አዲስ አበባ፤ግንቦት14፤ 2012 (ቁም ነገር ሚዲያ)የኢትዮጵያ አየር መንገድ  802 ለመደርሱ ቋሚና ጊዜያዊ የበረራ አስተናጋጆች በግዳጅ ለመስጠት የወሰነበት የእንግለሊዝኛ ቋንቋ ፈተና የስራ ዋስትና ያሳጣናል በሚል በሠራተኞቹ መሀከል ስጋት መፍጠሩ ታውቋል፡፡

ስማቸው እንዲየጠቀስ ያልፈለጉ የአየር መንገዱ የበረራ አስተናጋጆች አየር መንገዱን የተቀላቀሉት የቋንሻ  ትምሀርትን ጨምሮ በቂ የተባለ ስልጠና ወሰደደው እንደሆነ አስታውሰው አሁን አየር መንገዱ 90 መቶ የሚሆነውን በረራ በኮረና ቫይረስ ሳቢያ  ባቋረጠበት ወቅት የቋንቋ ፈተና ካልወሰዳችሁ በሚል ግዴታ ላይ የሚጥል ትዕዛዝ መምጣቱ ስጋት ላይ ጥሎናል ብለዋል፡፡

Read also:ፈረንሣይ በ50 ሚሊዮን ዩሮ ወጪ ለኢትዮጵያ   የሳተላይት ማምረቻና መገጣጠሚያ ማዕከል ልትገነባ…

የበረራ አስተናጋጆች ጨምረው እንደተናገሩት የቋንቋ ችሎት በስራ ሂደት እየዳበረ የሚሄድ እንደሆነ ጠቅሰው ለመግባባት በቂ የሚባል የቋንቋ ችሎታ ይዘው ወደ ስራ መግባታቻውን አስታውሰው የቋንቋ ችሎታቸውን ማሻሻል ያለባቸው ሠራተኞች ካሉ እንኳ በሌሎች ሙያዎች ላይ እንደተለመደው የስራ ላይ ስልጠና መስጠት እየተቻለ ይህንን የቋንቋ ፈተና ለሁሉም ሰራተኞች እንዲወስዱ መደረጉ የማያልፉ ሰራተኞች ላይ ምን አይነት እርምጃ ለመውሰድ እንደታሰበ እንዳማያውቁና የስራ ዋስትናቸውን  ሊያሳጣቸው እንደሚችል ስጋታቸውን ገልፀዋል፡፡

Read also:በዩኔስኮ ጊዜያዊ መዝገብ ላይ የተመዘገበው የባሌ ተራራሮች ብሔራዊ ፖርክ አደጋ ላይ…

ጉዳዩን በተመለከተ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የበረራ አስተናጋጆች ማህበርና አየር መንገዱን አስተዳደር  ማብራሪያ  እንዲሰጡ ቢጠየቅም ምላሽ ለመስጠት ፈቃደኞች አልሆኑም፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe