የኤሌትሪክ ተሽከርካሪዎች ተግዳሮትና የነዳጅ አውቶሞቢሎች እጣ ፈንታ

ሰሞኑን ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሪፖርት ያቀረቡተ የትራንስፖርትና ሎጀስቲክ ሚኒስትሩ ዶ/ር አለሙ ስሜ በነዳጅ የሚሰሩ አውቶሞቢሎች በተመለከተ የሰጡት መግለጫ ከገንዘብ ሚኒስቴር ጋር አጋጭተቸዋል፤ ሁሉቱ ሚኒስትር መ/ቤቶች እርስ በእርሱ የሚጋጭ መግለጫ መስጠታቸው አነጋጋሪ ብቻ ሳይሆን የመንግስትን ተናቦ የመስራት ፖሊሲ ጥያቄ ምልክት ውስጥ የሚጥል ነው፤
የገንዘብ ሚኒስቴር ሚኒስትሩ መስሪያ ቤታቸውም በነዳጅ የሚሰሩ የቤት አውቶሞቢሎች ወደ ሀገር ውስጥ እንዳይገቡ በተባለው አግባብ ብቻ እንደሚሰራ ለፓርላማው አስረድተዋል፡፡ማንኛውም የቤት አውቶሞቢል የኤሌክትሪክ ካልሆነ ወደ ኢትዮጵያ እንዳይገባ መንግስት ቀደም ሲል ውሳኔ ማሳለፉን ሚኒስትሩ ዓለሙ አንስተዋል፡፡

በነዳጅ የሚሰሩ አውቶሞቢሎችን ወደ ሀገር ውስጥ እንዳይገቡ መከልከሉን አልሰማንም ያሉ ሰዎች ገዝተው እያመጡ መሆኑን የትራንስፖርት እና ሎጀስቲክስ ሚኒስትሩ ዓለሙ ስሜ ቢናገሩም በሌላ በኩል በነዳጅ የሚሠሩ ተሽከርካሪዎች እንዳይገቡ ሙሉ በሙሉ አለመከልከሉን ገንዘብ ሚኒስቴር አስታውቀል፤

ሚኒስትሩ ይህን ያሉት በህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት የመስሪያ ቤታቸውን የ6 ወር እቅድ አፈፃፀም ለከተማ፣ መሰረተ ልማትና ትራንስፖርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ባቀረቡበት ወቅት ነው፡፡

ለተሽከርካሪዎች ነዳጅ የሚወጣው የውጭ ምንዛሬ ከፍተኛ መሆኑ፣ በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ በስፋት መመረቱ እና ከነዳጅ ጋር ሲነፃፀር ርካሽ መሆኑ እንዲሁም ኢትዮጵያ የአረንጓዴ ልማት ደጋፊ መሆኗ በነዳጅ የሚሰሩ የቤት አውቶሞቢሎችን ወደ ሀገር ውስጥ እንዳይገቡ ክልከላ ለመጣል ምክንያት ከሆኑት መካከል ይገኙበታል ሲሉ ሚኒስትሩ አስረድተዋል፡፡

በኤሌክትሪክ የሚሰሩ ተሽከርካሪዎች በአለም ላይ በስፋት እየተመረቱ መሆኑንን የጠቀሱት ሚኒስትሩ ዓለሙ ስሜ በሀገር ውስጥም ለሀይል መሙያ (ቻርጅ ማድረጊያ) ቦታዎችን በቶሎ ማዳረስ ይቻላል ብለዋል፡፡

ማንኛውም የግል መገልገያ አውቶሞቢል ወደ ሀገር ውስጥ ማስገባት የሚቻለው የኤሌክትሪክ ከሆነ ብቻ መሆኑንን ያሰመሩበት ሚኒስትር ዓለሙ ሰሞኑንን ይህን አልሰማንም በሚል በነዳጅ የሚሰሩ አውቶሞቢሎችን ገዝተው ያመጡ መኖራቸውን አስድተዋል፡፡

EV car

በሌላ በኩል በነዳጅ የሚሠሩ ተሽከርካሪዎች እንዳይገቡ ሙሉ በሙሉ አለመከልከሉን ገንዘብ ሚኒስቴር ያስታወቀው ከሚኒስትሩ ሪፖርት ብዙም ሳይዘገይ ነው፤በነዳጅ የሚሠሩ ተሽከርካሪዎች ወደ አገር ውስጥ እንዳይገቡ ሙሉ በሙሉ አለመከልከሉን የገለጹት የገንዘብ ሚኒስቴር ከፍተኛ ኃላፊ ናቸው።

የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስትሩ ዓለሙ ስሜ (ዶ/ር) በቅርቡ ለፓርላማው የከተማ መሠረተ ልማትና ትራንስፖርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የስድስት ወራት የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት ሲያቀርቡ፣ በነዳጅ የሚንቀሳቀሱ አውቶሞቢሎች ወደ አገር ውስጥ እንዳይገቡ ውሳኔ መተላለፉን ተናግረዋል።

የገንዘብ ሚኒስቴር ከፍተኛ የሕግ አማካሪ አቶ ዋሲሁን አባተ ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ በነዳጅ የሚሠሩ ተሽከርካሪዎች አገር ውስጥ እንዳደይገቡ በመከልከል የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ብቻ እንዲገቡ የሚፈቅድ ምንም ዓይነት መመሪያም ሆነ ውሳኔ የለም፡፡

በገንዘብ ሚኒስቴር በኩል እየተከናወነ ያለው ሥራ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች እንዲገቡ ለማበረታታትና በነዳጅ የሚሠሩት ደግሞ በብዛት እንዳይገቡ ተስፋ ለማስቆረጥ፣ የኤክሳይስ ታክስ አዋጅ የተደነገገበት ሁኔታ መኖሩን አቶ ዋሲሁን ተናግረዋል፡፡

ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን ማገድ በዓለም የንግድ ድርጅት ሕግ መሠረት የማይቻል በመሆኑ፣ የአገሪቱን የቀረጥ ሥርዓት በመጠቀም ኢኮኖሚ ለማሳደግ የሚጠቅሙትን ማበረታት፣ ጎጂ የሆኑትን ደግሞ እንዳይስፋፉ የማድረግ ሥራ እየተከናወነ ነው ብለዋል፡፡

የኤሌትሪክ ተሽከረካሪዎች ፍላጎት በአለም ዙሪያ

የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች በኢኮኖሚ ልማት እና የአካባቢ ጥበቃ ላይ ስጋት ባለማድረሳቸው ተፋልጊ እየሆኑ ነው። ከዚህም በላይ በሚቀጥሉት ትውልዶች በዙ ሀገራት እንደ ቻይናና ህንድ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎችን ለማምረት ወደፊት ጉዞ ጀምረዋል፤

የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ ምንድን ነው?
የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ (ኢቪ) ከውስጥ ከሚቀጣጠል ሞተር ሳይኖረው በኤሌክትሪክ የሚሰራ ሲሆን ይህም ነዳጅ እና ጋዞችን በማቃጠል ኃይል ከመፍጠር ይልቅ በኤሌትሪክ ሀይል ወደ ፊት የሚጓዝ ተሽከርካሪ ነው፤ በዚህም ምክንያት እየጨመረ የመጣውን የአካባቢ ብክለት፣ የአለም ሙቀት መጨመር፣ የተፈጥሮ ሃብቶችን መቀነስ እና የመሳሰሉትን ችግሮች ለመቅረፍ እንዲህ አይነት ተሽከርካሪ ለአሁኑ ትውልድ መኪኖች ምትክ ሊሆን ይችላል ተብሏል። የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ጽንሰ–ሐሳብ ከረጅም ጊዜ በፊት የነበረ ቢሆንም, በቅርብ አሥርተ ዓመታት ውስጥ እየጨመረ በመጣው የካርበን ብክለት እና ሌሎች በነዳጅ ላይ የተመሰረቱ ተሽከርካሪዎች በአካባቢያዊ ተጽእኖዎች ምክንያት ከፍተኛ ትኩረትን አግኝቷል፡፡ ኢ–ተሽከርካሪዎች በአለም ላይ ጠቃሚ ወይም ጎጂ ናቸው በሚለው ላይ የሚደረገው ውይይት ብዙ መደምደሚያዎችን ላይ አልደረሰም።
እውነታው ምንድነው
ከአለም አስር በጣም የተበከሉ ከተሞች ስድስቱ ያሉት ህንድ ውስጥ ነው፤ የዚህ የብክለት እድገት ዋነኛው መንስኤ የቅሪተ አካል ነዳጆችን መጠቀም ነው፤ በህንድ ውስጥ ያሉ ሁሉም ማለት ይቻላል ተሽከርካሪዎች፣ ባለ ሁለት ጎማ፣ ባለአራት ጎማ፣ እና ባቡሮች በአንዳንድ ቦታዎች ላይ የሚሰሩት በቅሪተ አካል ዝቃጭ ነዳጅ ነው። የህንድ ዘይት አስመጪ ይፋ እንዳደረገው አጠቃላይ የህንድ ድፍድፍ ዘይት ወደ ሀገር ውስጥ የምታስገባው 86% ነው፣ ይህም ሀገሪቱ የራሷን የኃይል ፍላጎት 14% ብቻ ያሟላል ማለት ነው። የቀረው ከውጭ ነው የሚመጣው። ነገር ግን፣ እነዚህ ከውጭ የሚገቡ ምርቶች የአሜሪካን ዶላር መጠቀም ያስፈልጋቸዋል፣ በዚህም ምክንያት የህንድ የውጭ ምንዛሪ መጠን /ፎሬክስ ሪዘርቭ/ ቅናሽ አድርጓል። ዓለም አቀፍ የአየር ንብረት ለውጥ፣ የሙቀት ልቀቶች፣ የፓሪስ የአየር ንብረት ስምምነት፣ እና የተራቀቀ አርቲፊሻል ቴክኖሎጂ ያለ አሽከረካሪ የሚነዱ መኪናዎች መብዛት የሚያሳድረው ተጽዕኖ ሁሉም ፊቱን ወደ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች እንዲያዞር እያደረገ ነው።
ኢ–ተሽከርካሪዎች በእርግጠኝነት ቀጣዩ የአለም ህዝብ የመጓጓዣ አብዮት ይፈጥራል፤ በመሆኑም እነዚህ ሁሉ ታሳቢዎች ከቅሪተ አካል ነዳጅ ወደ ኤሌክትሪክ መኪናዎች የሚደረገውን ሽግግር ይደግፋሉ፤ ሁሉም ያደጉ አገሮች ወደ ኤሌክትሪክ መኪናዎች እየተሸጋገሩ ነው። የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች የባትሪ ተግዳሮት የሊቲየም–አዮን ባትሪዎች ዋጋ በአለም አቀፍ ደረጃ $2500/kW ነው፣ ይህም በባትሪ ዋጋ ብቻ ወደ መቶ ሺ ብር ይደርሳል። በአሁኑ ጊዜ የሊቲየም–አዮን ባትሪዎች ለኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ ዋጋ ግማሹን ይሸፍናሉ,፤ይህም ከተለመደው ተሽከርካሪዎች የበለጠ ውድ ያደርጋቸዋል፤ ለ Li-ion ባትሪዎች ቻርጅ መሙላት በብዙ ሀገራት ውስጥ ላሉ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ትልቅ እንቅፋት ነው፣ የኃይል መሙያ ጣቢያዎች እጥረትም ሊታሰብበት የሚገባ ነው፣ ይህም በቻርጅ ረዥም ርቀት ጉዞዎችን በእጅጉ ያነሰ ያደርጋቸዋል። በብዙ የሰለጠኑ ሀገራት የነዳጅ ማደያ በየ 5-6 ኪሎሜትር ሊገኝ የሚችሉ ሲሆን የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ ቻርጅ ማድረጊያም በተመሳሳይ ርቀት ላይ መገንባት ይኖርባቸዋል፤ አለበለዚያ የኤሌክትሪክ መኪና የሚነዳ ሰው በእንደዚህ ዓይነት ሁኔታ አስቸጋሪ ጉዞ ይኖረዋል ማለት ነው፡፡
EV car
ምድርን ከካርቦን ልቀትና ካርቦን ዳይኦክሳይድ ነፃ ለማውጣት እየተሰራ ባለበት በአሁኑ ወቅት፣ ህንድን ቻይና የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎችን በማምረት ግንባር ቀደም በመሆን አረንጓዴ እና ንፁህ የስነ–ምህዳር ባለቤት ለማድረግ እየሰሩ ነው። የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ የዋጋ ንረት ከፍተኛ ነው፣ ይህም ወደ ኢ–ተሽከርካሪዎች የሚደረግ ሽግግር አስቸጋሪ የሚያደርገው ሲሆን ዘላቂነት ያለው ሊሆን የሚችለው ርካሽ ከሆነ ብቻ ነው። የኢትዮጵያ መንግሥት ይህንን ችግር ለመፍታት እርምጃዎችን መውሰድ ያለበት ቢሆንም ፍጥነቱ አዝጋሚ ነው። ዝቅተኛ ታክስ በማስከፈል ተሽከርካሪ ወደ ሀገር ውስጥ እንዲገባ ቢፈቅድም ዋጋው የሚቀመስ አለመሆኑን ሸማቾች ይናገራሉ፡፡

በኢትዮጵያ ስለኤሌክትሪክ መኪኖች ብዙ ይወራል። ቢበላሹ የሚጠግናቸው ባለሙያ የለም፣ ባትሪያቸው ኪስ ያራቁታል፣ ዕድሜውም አጭር ነው፣ ቻርጅ ማድረግ ፈተና ነው፣ ወኪል የላቸውም፣ መለዋወጫቸውም ውድ ነው ይባላል።

በተጨማሪም ይጓዙበታል የሚባሉትን ያህል ኪሎ ሜትር አይጓዙም፣ ለኢትዮጵያ አይሆኑም. . . ሌላም ሌላም ይባላል። እነዚህ ስጋቶች አሉባልታ ወይስ እውነት? ሲል ቢቢሲ አማርኛ ባለሙያዎችን አነጋግራል፤

በኢትዮጵያ የትራንስፖርት ዘርፍ የ10 ዓመት ዕቅድ ውስጥ ታዳሽ ኃይል ቅድሚያ ተሰጥቶታል። በዚህ ዕቅድ በኤሌክትሪክ የሚሰሩ የሕዝብ ማመላለሸ እና አንስተኛ ተሽከርካሪዎች በብዙ ቁጥር ወደ አገር ውስጥ እንዲገቡ ታቅዷል። በኢትዮጵያ የኤክትሪክ መኪና ወደ አገር ውስጥ ለማስገባት የሚጣለው ግብር ዝቅ ተደርጓል።

ታዲያ የመንግሥት ፍላጎት እና የዓለም ጉዞ እንዲህ ከሆነ፣ በኢትዮጵያ ተሽከርካሪዎቹ ላይ ለምን ጥርጣሬ እና ጥያቄ በዛ? እውነታው ምንድን ነው?

የአውቶሞቲቭ ምርቁ ብሩክ አወቀ የትራንስፖርት አማካሪ ነው።

ሚኪ አወቀ በሚል ስም በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ ከተሽከርካሪዎች ጋር በተያያዘ በሚሠጠው መረጃ ይታወቃል። ብሩክ፣ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ለነዳጅ የሚወጣ ወጪን በመቀነስ እንዲሁም ከባቢ አየርን ለመጠበቅ ጠቃሚ እንደሆኑ ያነሳል።

እንደ አገር ለነዳጅ የሚወጣውን ወጪ ለመቀነስ እና የውጪ ምንዛሬን ለማዳንም እንዲሁ።ይህንን ሀሳብ ኢክራም ኢድሪስም ትስማማበታለች።

ኢክራም የመኪና አካል ጥገና ባለሙያ ስትሆን፣ በዚህ ሙያ ላይ ለዓመታት ቆይታለች።

አውቶሞቲቭን የተመለከተ የቴሌቪዥን ፕሮግራም ያላት ኢክራም በኢትዮጵያ መኪና ነክ ጉዳዮችን በትኩረት ትከታተላች።

“ካርበን የሚለቁ አሮጌ መኪኖች የሚነዱበት ከተሞች ነው ያሉን” የምትለው ኢክራም የኤሌክትሪክ መኪኖች ይህንን ሁኔታ ለመቀየር ጠቃሚ እንደሆነ ታስረዳለች።

ኮረንቲ ሞተርስ ላለፉት አምስት ዓመታት ገደማ የኤለክትሪክ ተሽከርካሪዎችን ወደ ኢትዮጵያ ያስገባል። የድርጅቱ ሥራ አስኪያጅ እና ባለቤት አቶ ሚካኤል ከአራት ዓመታት በላይ ኤሌክትሪክ መኪና ነድተዋል። እሳቸው ኤሌክሪክ መኪና ከሚጠቀስለት ጥቅሞች አንዱ ድምጽ አልባ መሆኑ ነው ይላሉ። ብሩክ እና ኢክራም ኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት ለኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ምቹ መሆኗ ያጠራጥራቸዋል። አቶ ሚካኤል ደግሞ ብዙ ተስፋዎች ይታያቸዋል።

ጥገና እና ባለሙያዎች

ኢክራም እነዚህ ተሽከርካሪዎች በየጊዜው ‘ሰርቪስ’ የሚደረጉበት እና ችግር ሲያጋጥማቸው የሚጠገኑበት ማዕከላት አሉ ወይ? የሚል ጥያቄ ታነሳለች። በቂ ባለሙያዎችስ?

“መኪኖቹ በብዛት እየገቡ የመሆናቸውን ያህል ባለሙያዎች ላይ ምን ያህል ተሠርቷል? ቀጣይ የሚመረቁ የአውቶሞቲቭ ተማሪዎች የኤሌክትሪክ መኪናን በተመለከተ እየተማሩ ነው ወይ?” የሚል ጥያቄም አስከትላለች።

ቀጥላም እራሳቸውን በራሳቸው ያስተማሩ ግን ያላቸው እውቀት ያልተረጋገጠ ‘ባለሙያዎች’ በአሁኑ ወቅት “ትንሽ መፍትሄ እየሰጡ ነው” ትላለች።

ወደ ኢትዮጵያ የሚገቡ ተሽከርካሪዎች እነዚህ ‘ባለሙያዎች’ ላይ የተመረኮዙ ይሆናል።

ብሩክ፣ “በማንበብ በራሳቸው ተነሳሽነት ሥራ የጀመሩ ባለሙያዎች አሉ። አነሱም ቢሆን በቂ ናቸው የሚል እምነት የለኝም” ሲል ይገልጻል።

በተጨማሪም በኤሌክትሪክ መኪና ላይ ያተኮሩ በቂ የጥገና ማዕከላት አለመኖር ተጠቃሚዎች ላይ ስጋት ሊያጭር እንደሚችል ባለሙያዎቹ ያነሳሉ።

አቶ ሚካኤልም፣ በቂ የጥገና ማዕከላት እና ባለሙያዎች የሉም በሚለው ሐሳብ ይስማማሉ።

መልካሙ ነገር ግን፣ የእነዚህን ተሽከርካሪዎች ችግር መለየት ቀላል መሆኑ ነው ይላሉ። እንደእሳቸው ገለጻ፣ ችግሩን በቀላሉ በመለየት መቀየር ወይም መስተካክል ያለበትን ነገር የሚጠቁሙ ቴክኖሎጂዎች አሉ።

ለአብት፣ ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ የኤሌክትሪክ መኪኖች ተገቢ ባልሆነ የኃይል ምንጭ (ቻርጅ) አሞላል ምክንያት ማገናኛቸው (ቻርጀር ፖርት) ላይ ተደጋግሞ ችግር እንደሚከሰት ገልጸው፤ ቴክኖሎጂው ይህንን በፍጥነት እንደሚለይ አስረድተዋል።

ይህ መሆኑ በፍጥነት መፍትሔ ለመስጠት እንደሚያግዝ ጠቅሰዋል።

በተጨማሪም በናፍጣ እና ቤንዚን እንደሚሠሩ መኪኖች ዘይት፣ ‘ፊልትሮ’ እና መሰል ነገሮች እንደማይጠቀሙ ገልጸው፣ ይህም ለጥገና ቀላል ያደርጋቸዋል ሲሉ ያስረዳሉ።

ባትሪ ዋጋ እና የሚያገለግልበት ዕድሜ

ወደ አገር ውስጥ ለሚገቡ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ግልጽ የሆነ የባትሪ መስፈረት አልተቀመጠም የሚለው ብሩክ ነው። “ይህ መኪኖቹ ምን ያህል ያገለግላሉ የሚለውን ጥያቄ ውስጥ የሚጥል ነው” ካለ በኋላ “አንድ ምስሌ ለማንሳት፣ አገር ውስጥ የሚገጣጠሙ መኪኖች ‘ስገዛው እስከ 400 ኪሎ ሜትር [ቻርጁ ሙሉ ሆኖ] ይሄዳሉ ተብሎ ነበር፤ አዲስ የገዛሁት ወደ 120 ኪሎ ሜትር ወርዶብኛል’ የሚሉ ቅሬታዎችን እንደ ባለሙያ እሰማለሁ” ይላል።

በኢትዮጵያ አብዛኞቹ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች የሚጠቀሙት ሊቲየም ባትሪ ነው። ይህ ባትሪ በጊዜ ሂደት አቅሙ ያሽቆለቁላል። የሚሰጠው ዋስትና ደግሞ፣ እስከ 10 ዓመት ድረስ ከ80 በመቶ ዝቅ አይለም የሚል ነው።

“አሁን መሬት ላይ ያለውን ሲታይ ግን ዓመት ከስድስት ወር ተጠቅመው ከ50 ፐርሰንት በታች የወረደባቸው አሉ። ከዚህ አንጻር የአስተማማኝነታቸው ጉዳይ ጥያቄ ውስጥ የሚገባ ነው” ሲል ይገልጻል።

የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ባትሪ እጅግ ውድ ነው የሚል መረጃ እንዳላት ኢክራም ትናገራለች። “ባትሪው ከመኪናው ዋጋ እኩል ነው ይባላል” ትላለች።

እዚህ ጋር የአቶ ሚካኤል ሐሳብ ግን የተለየ ነው፤ እሳቸው በዓለም አቀፍ ደረጃ የኤሌክሪክ ተሽከርካሪዎች ዋጋ እየቀነሰ ነው ይላሉ። ከ10 ዓመታት በኋላ ደግሞ ከዚህም በበለጠ እየቀነሰ እንደሚሄድም ያምናሉ።

ምክንያታቸውን ሲገልጹ፣ አሁን ላይ የሚመረቱት ባትሪዎች በዓይነት እና በብዛት ሰፋ ያሉ መሆናቸውን ነው። በሌላ በኩል እሳቸው ይህንን ሥራ ከጀመሩ በኋላ ባሉት ዓመታት፣ አንድም ባትሪው አገልግሎት ያቆመ ወይም የተበላሸ ተሽከርካሪ ገጥሟቸው እንደማያውቅ ምስክርነታቸውን ይሰጣሉ።

ቻርጅ ማድረግ እና ተያያዥ ጉዳዮች

የኤሌክትሪክ ኃይል ፍሰት ‘በአምፔር’ ይለካል። የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ኃይል መሙያ ደግሞ በ8፣ በ16 እና በ32 አምፔር ይመረታሉ። ብሩክ ወደ አገር ውስጥ የሚገቡት ተሽከርካሪዎች በፈጣን ቻርጅ ማድረጊያ ከ30 እስከ 40 ደቂቃ ሙሉ ኃይል ሊይዙ እንደሚችሉ ያነሳል። ችግሩ፣ በአዲስ አበባ የፈጣን ኃይል መሙያዎች አለመኖሩ ነው።

በዚህም ምክንያት ገዢዎች ቤት ውስጥ በሚዘረጋ ነጠላ ‘ፌዝ’ ቻርጅ ለማድረግ ይገደዳሉ።

ለምሳሌ 8 አምፔር ኃይል መሙያ ያለው ተሽከርካሪ ቤት ውስጥ በሚገኝ መደበኛ ኃይል (በ7 ኪሎዋት) ከዜሮ እስከ 100 ‘ቻርጅ’ ለማድረስ ከ12 እስከ 40 ሰዓት ሊፈጅ እንደሚችል ይጠቅሳል። በትልቁ ኃይል፣ 32 አምፔር ብናሰላው ደግሞ እስከ 8 ሰዓት ሊያስፈልገው ይችላል።

ሆኖም በተመሳሳይ ሰዓት እንደ ምጣድ ያሉ የቤት ውስጥ ቁሶች ጥቅም ላይ ከዋሉ ቆጣሪ ሊመልስ ይችላል። አቶ ሚካኤልም በዚህ ችግር ይስማሙበታል። በቂ ቻርጅ ማደርጊያ ቦታዎች አለመኖርም አንስተው ድርጅታቸው እዚህ ላይ የመሥራት ፍላጎት እንዳለው ተናግረዋል። የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ 100 ‘ፐርሰንት’ የኃይል ከሞላ በኋላ ከሳምንት እስከ 10 ቀን በማገለግል ሊቆይ የሚችል ነው ይላሉ።

ባትሪው፣ ከ20 እስከ 80 ፐርሰንት ለመሙላት በአንጸራዊነት ጊዜ አይወስድም። ከዜሮ እስከ ሃያ እና ከ80 እሰከ 100 ለመድረስ ተጨማሪ የመሙያ ጊዜ ይፈልጋል። ባትሪው ከዜሮ ተነስቶ 100 ለማድረስ እስከ 12 ሰዓት ሲፈጅ፣ ከ 20 እስከ 80 ግን ከ7 እስከ 8 ሰዓት ይወስዳል።

ወኪል አለመኖር እና የመለዋወጫ ዋጋ

ኢክራም በአንድ ወቀት የሆነውን ስታስታውስ “አንድ ሰው የኤሌክትሪክ መርሴዲስ ወደ ኦርቢስ [በኢትዮጵያ የመርሴዲስ ወኪል] ለሰርቪስ ወስዶ ‘ይህ መኪና በኢትዮጵያ ስታንዳርድ አልተመረተም። እኛ ይህንን የመጠገን ፍቃድ የለንም” ብለው መመለሳቸውን ታስታውሳለች።

በዚህም ሳቢያ የኤሌክትሪክ መኪኖች አሁን ባለው ሁኔታ “ልክ እንደተለመዱት መኪና ሲበላሹ ቶሎ ሰርቪር አግኝቶ የሚመለሱበት አይደሉም” ትላለች።

ወኪሎች ሲኖሩ መኪናው ዋስትና እንዲኖው እና ችግር ሲያግጥም በአምራቹ ኪሳራ እንዲጠገኑ እንሚያደርግ የሚያነሳው ደግሞ ብሩክ ነው።

ኢክራምም “የወኪሎች ጉዳይ በቀላሉ የሚታይ አይደለም” ትለለች።

በቅርቡ ያጋጠማትን ሌላ ጉዳይ ስታነሳ፣ ቮልክስ ዋገን አይዲ 6 መኪና ቁልፉ ጠፍቶ ለብዙ ችግር መዳረጓን ታነሳለች።

“ቁልፉን ለማግኘት እየተሰቃየን ጉዳዩ ወደ መኪና አምራቹ ሄዶ ቁልፍ እንዲያትም ሲጠየቅ የመጀመሪያ ገዢው ካልመጣ” እንደማይሰጥ ማሳወቁን ትነገራለች። “ነጋዴ ከነጋዴ ተቀባበብሎ ነው መኪናው [ኢትዮጵያ ውስጥ] ባለቤቱ ጋ የደረሰው። ይኼ ነገር ሳይመቻች ኤሌክትሪክ መኪና ብንል እንደተጠቃሚ ችግሮች ይገጥማሉ” ካለች በኋላ ቁልፉ “በደላሎቹ” በመቶ ሺዎች እንደተጠየቀበት ገልጻለች።

እንደ ስፖኪዮ ያሉ መለዋወጫዎችም በመቶ ሺዎች እንደሚጠየቅባቸው አስረድታለች። በኢትዮጵያ በተደጋጋሚ ለመለዋወጫ ፍላጎት እየዳረገ ያለው ስርቆት ነው የሚሉት አቶ ሚካኤል፣ ዋጋቸው እጅግ የተጋነነ ነው በመባሉ አይስማሙም።

ለዚህ መፍትሔ ይሆናል የሚሉት ደግሞ፣ የሚኖረውን ፍላጎት እየተከተለ አቅርቦት ሲጨምር ዋጋቸው ከሌሎቹ መኪኖች መለዋወጫ ጋር ሊቀራረብ ይችላል ብለው ያምናሉ። ሆኖም አንዳንድ የመኪና ንግድ ውስጥ ያሉ “ደላሎች” በሚፈጥሩት “ወሬ” ገበያው እንደሚታወክ አንስተዋል።

ከመደበኛው መኪና የተለየ ጎማ ለማይጠቀመው የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ “ጎማ እስከ 80 ሺህ ብር እንደተሸጠ” ያስታውሳሉ።

በሌላ በኩል አቶ ሚካኤል እንደሚሉት ቁልፍን የመሰሉ የመኪና ቁሶች ለማግኘት መቸግር ለኤሌክትሪክ መኪና ብቻ ሳይሆን ለዘመናዊ የነዳጅ መኪኖችም እንደሚሠራ ነው። ይህ ማለት በወኪል አማካኝነት ያልተገዛ እና በነዳጅ የሚሠራ የዘመኑ ተሽከርካሪም ቁልፍ ቢጠፋ ተመሳሳይ ዕጣ ይገጥመዋል። አቶ ሚካኤል የወኪሎች መኖር የመኪናውን ዋስትና ለማረጋገጥ ያለውን ጥቅም ይስማሙበታል። ሆኖም ወኪል አለመኖሩ የሚያጎድለው ትልቅ ነገር የለም ይላሉ።

እሳቸው በኢትዮጵያ የሚጋጥመው አብዛኛው ችግር ከቻርጅ ጋር የተያያዘ ያልተገባ አጠቀቀም እንደሆነ ነው። በዚያ ሳቢያም ኢትዮጵያ ውስጥ ወኪል ቢኖር እንኳን ለዚህ ችግር ዋስትና ሊሰጥ አይችልም ይላሉ።

“ስለዚህ ወኪል ካለመጣቸው መኪኖቹ [ወደ ኢትዮጵያ] መምጣት የለባቸወም ወደሚል ደምዳሜ መሄድ የለብንም” ብለዋል።

ተሽከርካሪዎቹ በወኪል አማካኝነት ሲመጡ ቁጥጥሩ ሊጠብቅ ስለሚችል የምርት እጥረት በመፍጠር ዋጋቸውን እጅግ ሊያሻቅበው እንደሚችል ይጠቅሳሉ።

በሚጓዙት ኪሎ ሜትር ላይ ያለ ልዩነት

ከኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ጋር በተያያዘ ደጋግሞ የሚነሳው ጥያቄ ‘100 ፐርሰንት ቻርጅ ተደርገው’ ምን ያህል ይጓዛሉ የሚል ነው።

አምራቹ ወይም ሻጩ ይህንን ያህል ይላል። ብሩክ ‘ይህንን ቁጥር አምነን በአንድ ጉዞ በመቶ ኪሎ ሜትሮች እንጓዝ ብንል ጉድ እንሆናለን’ ሲል ይጠቅሳል።

“መኪኖቹ 500 ወይም 600 ኪሎ ሜትር በፉል ቻርጅ ይጓዛሉ ይባላል እንጂ በአንዱ ጉዞ ያለማቋረጥ ‘እንደልብ’ ከተነዱ” ከ300 ኪሎ ሜትር በላይ መሻገር እንደሚሳናቸው ይገልጻል።

የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች የኃይል መሰጫ ‘ፔዳላቸው’ ሳይረገጥ የሚቆይ ከሆነ ራሳቸውን በራሳቸው ኃይል የሚሞሉበት ሥርዓት አላቸው።

“እንደልብ” ሲነዱ ግን ሙሉ በሙሉ ያላቸውን ኃይል ያሟጥጣሉ።

በተጨማሪም፣ ፍጥነትን በሰዓት ከ80 ኪሎ ሜትር በታች ማድረግ እንዲሁም አየር መቆጣጠሪያን (AC) ማጥፋት የግድ ይሆናል። ያ ካልሆነ ተሽከርካሪዎቹ ከተነገረላቸው ርቀት እጅግ ቀድመው ኃይል ይጨርሳሉ። በተቃራኒው “የነዳጅ መኪኖች ከከተማ ውጪ ሲነዱ የሚጠቀሙት ነዳጅ ይቀንሳል።”

ይህንን ሐሳብ የሚቀበሉት አቶ ሚካኤልም፣ የአየር መቆጣጠሪያ ረጅም ሰዓት ተከፍቶ በሚሽከረከርበት ጊዜ የባትሪውን ኃይል ሊጋራ እንደሚችል ያነሳሉ።

ሆኖም መኪናው የፍጥነት ፔዳሉ ሳይነካ በሚነዳበት ጊዜ ራሱን በራሱ ኃይል መሙላት መቻሉ በቀላሉ የማይታይ ትልቅ ጥቅም መሆኑን ያስረዳሉ።

ለኢትዮጵያ አይሆኑም?

ወደ ኢትዮጵያ የሚገቡት ተሽከርካሪዎች ለኢትዮጵያ የማይሆኑ ናቸው የሚለው ብሩክ፣ አብዛኞቹ መኪኖች የቻይናን ገበያ ታሳቢ ያደረጉ እንደሆኑ ያነሳል።

ለአብነት ‘ዳሽቦርዱን’ እንኳን ብናይ በቻይንኛ ቋንቋ የተጻፈ ነው ይላል።

ኢክራምም እንዲሁ መኪኖች ለኢትዮጵያ የሚመቹ መሆናቸው ላይ ጥያቄ አላት።

አቶ ሚካኤል፣ የኤሌክትሪክ መኪኖች በነዳጅ ኃይል እንደሚንቀሳቀሳቀሱት “ለአፍሪካ፣ ለመካከለኛው ምሥራቅ ወይም ለአውሮፓ ተብለው የሚሠሩበት መነሻ የለም” ይላሉ።

ምክንያት ሲጠቅሱ ይህ የምርት ክፍፍል የሚመጣው ከነዳጅ ጥራት ጋር የተያያዘ መሆኑ ነው።

ሆኖም፣ እጅግ ከፍተኛ ሙቀት ወይም የቅዝቃዜ መጠን ላላቸው አካባቢዎች የተለየ ባትሪ ሊገጠም እንደሚችል በመጥቀስ፣ “ስለዚህ ለቻይና ተብሎ የተሠራ የኤሌክትሪክ መኪና መኖሩን እኔ በግሌ አለውቅም” ይላሉ።

ቀጥለው፣ ‘ውማ’ ከሚሰኘው የኤሌክትሪክ መኪና ውጪ መሠረታዊ ቋንቋው ቻይንኛ ብቻ የሆነ ተሽከርካሪ እንደማያውቁ ይናገራሉ።

ወደ ኢትዮጵያ በስፍት እየገቡ ያሉት ቮልክስ ዋገን፣ ቶዮታ እና ቮለቮን ጨምሮ እንግሊዝኛ እና ሌሎች አማራጮች ያላቸው ናቸው ብለዋል።

ሁሉም ባለሙያዎችን በኢትዮጵያ ለኤሌክትሪክ መኪና የተሰጠው ትኩረት ተገቢነት ቢያስማማቸውም ለእነዚህ ተሽከርካሪዎች የሚያስፈልጉ ግብዓቶች አቅርቦትን መሟላት እንደሚያስፈልግ ይጠቅሳሉ።

ቻርጅ ማድረጊያ ጣቢያዎችን ጨምሮ በቂ መሠረተ ልማቶችን መዘረጋት፣ ወደ አገር ውስጥ የሚገቡበትን አሠራር ቀላል ማድረግ፣ የተጠና፣ ፍርሃት እና ጥርጣሬን የማይፈጥሩ ውሳኔዎችን ማሰለፍን በዋናነት አስፈላጊ ናቸው ይላሉ።

 ማጠቃለያ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች የወደፊት ዕጣ ብሩህ እና ብሩህ ነው! የማምረቻ ንግዶች ከባህላዊ አውቶሞቢሎች ወደ ኤሌክትሪክ ተሸከርካሪዎች ለመሸጋገር የበለጠ ጥረት እያደረጉ ነው። በተገቢው የተግባር ደረጃ እና መሠረተ ልማት ያለው የኤሌክትሪክ መኪና ባለቤት ለመሆን በርካታ ጥቅሞች አሉት፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe