የኤርትራ ስደተኞችን ዳባት ወደሚገኘው “አለምዋጭ መጠሊያ ጣብያ” ለማዛወር እተየሰራ ነው- የተመድ ስደተኞች ኤጀንሲ

ኤጀንሲው በማይ ዓይንና ዓዲ ሓሩሽ ለሚገኙ የኤርትራ ስደተኞችን ድጋፍ እያደረገ መሆኑን አስታውቋል

የትግራይ ክልል ግጭት ወደ አጎራባች የአማራ እና አፋር ክልሎች መዝለቁ እንደሚያሳስበውም ኤጀንሲው ገልጿል

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽን በማይ ዓይንና ዓዲ ሐሩሽ መጠሊያ ጣብያወች ለሚገኙ የኤርትራ ስደተኞችን ድጋፍ እያደረገ መሆኑን አስተውቋል።

የኤጀንሲው ቃል አቀባይ ቦሪስ ቼስረኮቭ በሰጡት መግለጫ፤ በትግራይ በተከሰተው ግጭት ምክንያት መንገድ በመዘጋቱ እንደፈረንጆቹ ከሃምሌ 13 2021 ጀምሮ የኤጀንሲው ሰራተኞች እንደፈለጉ መንቀሳቀስ እንደተሳናቸው ገልጸዋል።

ከነሃሴ 5 2021 ወዲህ ግን አስቸኳይ እርዳታ የመስጠት ተግባራት መከናወን ጀምረዋል ያሉት ቃል አቀባዩ፤ እስካሁን በሁለቱም መጠለያ ጣቢያ ለሚገኙ 23 ሺህ ለሚሆኑ ስደተኞች ድጋፍ መደረጉንም አስታውቋል።

ይሁን እንጅ እየተደረገ ያለው ድጋፍ ውስን በመሆኑ እንዲሁም የነበሩት ጤና ጣብያዎች በመውደማቸውን እና ና ንጹህ የመጠጥ ውሃ አለመኖሩ ያለውን ሁኔታ እንዳደረገውም ቃል አቀባዩ ተናግረዋል።

ቼስረኮቭ አክለውም በማይ ዓይኒ እና ዓዲ ሐሩሽ መጠሊያ ጣቢያዎች የሚገኙ ስደተኞችን ዳባት ከተማ ወደሚገኘው አዲሱ “አለምዋጭ መጠሊያ ጣብያ” እንዲዛወሩ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን አንስተው፤ አስተማማኝ መተላለፍያ እንዲበጅም ጠይቀዋል።

የተመድ ስደተኞች ኤጀንሲ ከኢትዮጵያው የስደተኞችና ከስደት ተመላሾች ኤጀንሲ ጋር እና ከአከባቢው ማህበረሰብ ጋር በመተባበር ነው በዳባት የሚገኘውን “አለምዋጭ መጠሊያ ጣብያ” ያቋቀዋሙት።

እስካሁን 126 ስደተኞች ወደ “አለምዋጭ መጠሊያ ጣብያ” ተዛውረው ድጋፍ በማግኘት ላይ መሆናቸውንም ቃል አቀባዩ ቼስረኮቭ ገልጸዋል።

ባለፉት ሳምንታት ብቻ በትግራይ ክልል የሚደረገው ሰብዓዊ እርዳታ የጨመረ ሲሆን፤ አስካሁን የአስቸኳይ እርዳታ የጫኑ 12 የጭነት ተሸከርካሪዎች ወደ መቀሌ መግባታቸው ተነግሯል።

ቃል አቀባዩ ኤጀንሲውና ለጋሽ ድርጅቶች የሚያደርጉትን ሰብዓዊ እርዳታ ለማሳደግ ብሎም በረሃብ አፋፍ ላይ የሚገኙትን ዜጎች ለመታደግ ሁሉም የግጭቱ ተዋናዮች ያልተገደበ እንቅስቃሴ እንዲኖር ኃላፊነታቸው እንዲወጡም ጠይቋል።

በትግራይ የተጀመረው ግጭት አሁን ላይ ወደ አጎራባች የአማራ እና አፋር ክልሎች ዘልቆ በርካቶች መፈናቀላቸው የተመድ ስደተኞች ኤጀንሲ እንደሚያሳስበውም ነው ቃል አቀባዩ ተናግሯል።

የተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤት መረጃ እንደሚመከተው አስካሁን 100 ሺህ የሚሆኑ ዜጎች ከአማራ እንዲሁም 70 ሺህ ዜጎች ከአፋር ክልሎች ተፈናቅለዋል፡፡

በመንግስት በበኩሉ ከአፋር እና ከአማራ ክልል የተፈናቀሉትን ዜጎች ቁጥር 300 ሺህ መድረሱ በመገለጽ ላይ ነው።

Kumneger Media
Kumneger Media
Kumneger Media is a News and Entertainment Website & Channel. Kumneger Media in addition to News and Entertainment it is the hub of Politics, Movies, Drama, Music, Comedy, Documentary and More!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe